ነህምያ 1:3-6

ነህምያ 1:3-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እነ​ር​ሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከም​ርኮ የተ​ረ​ፉት ቅሬ​ታ​ዎች በታ​ላቅ መከ​ራና ስድብ አሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ፈር​ሶ​አል፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋል” አሉኝ። ይህ​ንም ቃል በሰ​ማሁ ጊዜ ተቀ​ምጬ አለ​ቀ​ስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰ​ማ​ይም አም​ላክ ፊት እጾ​ምና እጸ​ልይ ነበር፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦ “አቤቱ የሰ​ማይ አም​ላክ ሆይ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ህና ትእ​ዛ​ዝ​ህን ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥ ታላ​ቅና የተ​ፈ​ራህ አም​ላክ ሆይ፥ እኔ ባሪ​ያህ ዛሬ በፊ​ትህ ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሌሊ​ትና ቀን የም​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮ​ዎ​ችህ ያድ​ምጡ፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ይከ​ፈቱ፤ በአ​ንተ ላይም ያደ​ረ​ግ​ነ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ኀጢ​አት ለአ​ንተ እን​ና​ዘ​ዛ​ለን፤ እኔም፥ የአ​ባ​ቴም ቤት በድ​ለ​ናል።