ነህምያ 1:1-11

ነህምያ 1:1-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የኬ​ል​ቅያ ልጅ የነ​ህ​ምያ ቃል። በሃ​ያ​ኛው ዓመት በካ​ሴሎ ወር እን​ዲህ ሆነ፤ እኔ በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥ ከወ​ን​ድ​ሞች አንዱ ሐናኒ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሌሎች ሰዎች ከይ​ሁዳ መጡ፤ እኔም የዳ​ኑ​ትን፥ ከም​ር​ኮም የተ​ረ​ፉ​ትን የአ​ይ​ሁ​ድን ነገር፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ነገር ጠየ​ቅ​ኋ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከም​ርኮ የተ​ረ​ፉት ቅሬ​ታ​ዎች በታ​ላቅ መከ​ራና ስድብ አሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ፈር​ሶ​አል፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋል” አሉኝ። ይህ​ንም ቃል በሰ​ማሁ ጊዜ ተቀ​ምጬ አለ​ቀ​ስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰ​ማ​ይም አም​ላክ ፊት እጾ​ምና እጸ​ልይ ነበር፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦ “አቤቱ የሰ​ማይ አም​ላክ ሆይ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ህና ትእ​ዛ​ዝ​ህን ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥ ታላ​ቅና የተ​ፈ​ራህ አም​ላክ ሆይ፥ እኔ ባሪ​ያህ ዛሬ በፊ​ትህ ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሌሊ​ትና ቀን የም​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮ​ዎ​ችህ ያድ​ምጡ፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ይከ​ፈቱ፤ በአ​ንተ ላይም ያደ​ረ​ግ​ነ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ኀጢ​አት ለአ​ንተ እን​ና​ዘ​ዛ​ለን፤ እኔም፥ የአ​ባ​ቴም ቤት በድ​ለ​ናል። እኛም በአ​ንተ ላይ እጅግ ክፉ ሠር​ተ​ናል፤ ለባ​ሪ​ያ​ህም ለሙሴ ያዘ​ዝ​ኸ​ውን ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት፥ ሕጉ​ንም አል​ጠ​በ​ቅ​ንም። “አሁ​ንም ለሙሴ ለባ​ሪ​ያህ እን​ዲህ ስትል ያዘ​ዝ​ሃ​ትን ነገር አስብ። ብት​በ​ድ​ሉም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ። ወደ እኔ ብት​መ​ለሱ ግን፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ብታ​ደ​ር​ጓ​ትም ምንም ከእ​ና​ንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢበ​ተኑ፥ ከዚያ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስሜም ይኖ​ር​በት ዘንድ ወደ መረ​ጥ​ሁት ስፍራ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ። “እነ​ዚ​ህም በታ​ላቅ ኀይ​ል​ህና በብ​ርቱ እጅህ የተ​ቤ​ዥ​ሃ​ቸው ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህና ሕዝ​ብህ ናቸው። ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባ​ሪ​ያ​ህን ጸሎት፥ ስም​ህ​ንም ይፈሩ ዘንድ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ትን የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ጸሎት ያድ​ምጥ፤ ዛሬም ለባ​ሪ​ያህ አከ​ና​ው​ን​ለት፤ በዚ​ህም ሰው ፊት ምሕ​ረ​ትን ስጠው።” እኔም ለን​ጉሡ ጠጅ አሳ​ላፊ ነበ​ርሁ።

ነህምያ 1:1-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል፤ በሃያኛው ዓመት ካሴሉ በተባለው ወር በሱሳ ግንብ ሳለሁ፣ ከወንድሞቼ አንዱ የሆነው አናኒ፣ ከሌሎች ጥቂት ሰዎች ጋራ ከይሁዳ መጣ፤ እኔም ከምርኮ ስለ ተረፉት የአይሁድ ቅሬታዎችና ስለ ኢየሩሳሌም ጠየቅኋቸው። እነርሱም፣ “በሕይወት ተርፈው ከምርኮ ወደ አገራቸው የተመለሱት ሰዎች በታላቅ መከራና ውርደት ላይ ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌም ቅጥር ፈራርሷል፤ በሮቿም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ። ይህን ነገር በሰማሁ ጊዜ አያሌ ቀናት ዐዘንሁ፤ ጾምሁ፤ በሰማይ አምላክም ፊት ጸለይሁ። ከዚያም እንዲህ አልሁ፤ “ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያከብሩ የፍቅርህን ቃል ኪዳን የምትጠብቅ ታላቅና የተፈራህ አምላክ፣ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ባሪያህ ስለ አገልጋዮችህ ስለ እስራኤል ሕዝብ ቀንና ሌሊት በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎት ለመስማት ጆሮህ ይንቃ፤ ዐይንህም ይከፈት። እኔንና የአባቴን ቤት ጨምሮ እኛ እስራኤላውያን አንተን በመበደል የሠራነውን ኀጢአት እናዘዛለሁ። በአንተ ላይ እጅግ ክፉ ሥራ ሠርተናል፤ ለባሪያህም ለሙሴ የሰጠኸውን ትእዛዝ፣ ሥርዐትና ሕግ አልጠበቅንም። “ለባሪያህ ለሙሴ እንዲህ ስትል የሰጠኸውን ቃል ዐስብ፤ ‘ታማኞች ካልሆናችሁ፣ በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ወደ እኔ ብትመለሱና ትእዛዞቼን ብትፈጽሙ፣ የተሰደዱት ወገኖቻችሁ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንኳ ቢበተኑ፣ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፤ ለስሜም ማደሪያ ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።’ “እነዚህም በታላቁ ኀይልህና በብርቱ እጅህ የተቤዠሃቸው ባሪያዎችህና ሕዝብህ ናቸው። ጌታ ሆይ፤ የባሪያህን ጸሎት፣ ስምህን በመፍራት ደስ የሚሰኙትን የባሪያዎችህንም ጸሎት ጆሮህ ታድምጥ። በዚህ ሰው ፊት ሞገስን አድርገህለት ዛሬ ለባሪያህ መከናወንን ስጠው።” በዚያ ጊዜ እኔ የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርሁ።

ነህምያ 1:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል። በሃያኛው ዓመት በካሴሉ ወር እንዲህ ሆነ፤ እኔ በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥ ከወንድሞቼ አንዱ አናኒ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሰዎች ከይሁዳ መጡ፤ እኔም የዳኑትን ከምርኮ የተረፉትን የአይሁድን ነገር የኢየሩሳሌምንም ነገር ጠየቅኋቸው። እነርሱም፦ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፤ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ። ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፤ እንዲህም አልሁ፦ “አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥ እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮህ ያድምጥ፤ ዓይኖችህም ይከፈቱ፤ በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኃጢአት እናዘዝልሃለሁ፤ እኔና የአባቴም ቤት በድለናል። እኛም በአንተ ላይ እጅግ ክፉ ሠርተናል፤ ለባሪያህም ለሙሴ ያዘዝኸውን ትእዛዝና ሥርዓት ሕግም አልጠበቅንም። አሁንም፦ ‘ብትተላለፉ በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ወደ እኔ ብትመለሱ ግን ትእዛዜንም ብትጠብቁ ብታደርጓትም፥ ከእናንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ምንም ቢበተኑ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፤ ስሜም ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ’ ብለህ ለባሪያህ ለሙሴ ያዘዝኸውን ቃል እባክህ አስብ። እነዚህም በታላቅ ኃይልህና በብርቱ እጅህ የተቤዠሃቸው ባሪያዎችህና ሕዝብህ ናቸው። ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባሪያህን ጸሎት፥ ስምህንም ይፈሩ ዘንድ የሚወድዱትን፥ የባሪያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬም ለባሪያህ አከናውንለት፤ በዚህም ሰው ፊት ምሕረትን ስጠው።” እኔም ለንጉሡ ጠጅ አሳላፊው ነበርሁ።

ነህምያ 1:1-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የሐካልያ ልጅ ነህምያ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ አርጤክስስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነ በሃያኛው ዓመት ኪስሌው ተብሎ በሚጠራው ወር እኔ ነህምያ ዋና ከተማ በሆነችው በሱሳ ውስጥ ነበርኩ። ከወንድሞቼ አንዱ ሐናኒ ተብሎ የሚጠራው ሌሎች ሰዎችን አስከትሎ ከይሁዳ ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ስለ ኢየሩሳሌምና ወደ ባቢሎን ተማርከው ከመወሰድ ስለ ተረፉትና በሕይወት ስላሉት አይሁድ ሁኔታ ጠየቅኋቸው። እነርሱም “ተማርከው ወደ ባቢሎን ሳይወሰዱ የቀሩትና በሕይወት ያሉት አይሁድ በታላቅ ችግርና ኀፍረት ላይ ወድቀው ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጽሮች ፈራርሰው ወድቀዋል፤ የቅጽር በሮቹም በእሳት ጋይተዋል” ሲሉ መለሱልኝ። እኔም ይህን ሁሉ በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስኩ። ለብዙ ቀኖችም በጾምና በሐዘን ቈየሁ፤ ወደ እግዚአብሔርም እንዲህ ስል ጸለይኩ፦ “እግዚአብሔር የሰማይ አምላክ ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ እኛም በፍርሃት በፊትህ እንቆማለን፤ አንተ ከሚወዱህና ትእዛዞችህንም ከሚጠብቁ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳንህን ትጠብቃለህ። እግዚአብሔር ሆይ! አገልጋዮችህ ስለ ሆኑት የእስራኤል ሕዝብ ደኅንነት ቀንና ሌሊት የማቀርበውን ጸሎቴን ስማ፤ እኔንም አስበኝ፤ እኛ እስራኤላውያን የሠራነውንም ኃጢአት እናዘዛለሁ፤ በእርግጥም እኔና የቀድሞ አባቶቼ በደል ሠርተናል። በአንተ ላይ በማመፅ ትእዛዞችህን ሁሉ ተላልፈናል፤ በአገልጋይህ በሙሴ አማካይነት የሰጠኸንንም ሕግና ሥርዓት አልጠበቅንም። ‘እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እኔን በእምነት ባትከተሉ በአረማውያን ሕዝቦች መካከል እበትናችኋለሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ ተመልሳችሁ ያዘዝኳችሁን ትእዛዞች ብትፈጽሙ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ የተበታተናችሁ ብትሆኑም እንኳ ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን ወደ መረጥሁት ስፍራ እንደገና በመሰብሰብ መልሼ አመጣችኋለሁ’ ስትል ለሙሴ የተናገርከውን ቃል አስብ። “እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ የአንተ አገልጋዮችና የገዛ ሕዝብህ ናቸው፤ ከዚህ በፊትም በታላቁ ኀይልህና በብርቱ ክንድህ በመታደግ አድነሃቸዋል። እነሆ፥ አሁንም የእኔን ጸሎት ስማ፤ አንተን ማክበር የሚወዱትን የሌሎችንም አገልጋዮችህን ጸሎት አድምጥ፤ ዛሬ ልሠራው ያቀድኩት ይሳካልኝ ዘንድ የንጉሠ ነገሥቱን ልብ በማራራት እርዳኝ።” እነሆ፥ እኔ በዚህ ጊዜ የንጉሠ ነገሥቱ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።

ነህምያ 1:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል። በሃያኛው ዓመት በኪስሌው ወር በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥ እንዲህ ሆነ፤ ከወንድሞቼ አንዱ ሐናኒ ከሌሎች ሰዎች ጋር ከይሁዳ መጡ፥ እኔም ከምርኮ ስለተረፉት የአይሁድ ትሩፋንና ሰለ ኢየሩሳሌም ጠየቅኋቸው። እነርሱም፦ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ትሩፋን በታላቅ መከራና በመሰደብ ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ። እነዚህን ቃላት በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ። ለብዙ ቀኖች አዘንሁ፤ በሰማይ አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥ እንዲህም አልሁ፦ ታላቅና የተፈራ አምላክ፥ ለሚወድዱትና ትእዛዙን ለሚጠብቁ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የሚጠብቅ፥ የሰማይ አምላክ ጌታ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ ዛሬ በፊትህ ስለ አገልጋዮችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ለመስማት ጆሮህ ያድምጥ፥ ዐይኖችህም ይከፈቱ፥ በአንተ ላይ ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኃጢአት እናዘዛለሁ፤ እኔና የአባቴ ቤት ኃጢአት አድርገናል። በአንተ ላይ ታላቅ ክፋት ሠርተናል፤ ለአገልጋይህ ለሙሴ ያዘዝኸውን ሕጎች፥ ትእዛዛትና ፍርድ አልጠበቅንም። ለአገልጋይህ ለሙሴ እንዲህ ብለህ ያዘዝኸውን ቃል እባክህ አስብ። “ታማኞች ካልሆናችሁ በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ ብትመለሱ ትእዛዛቴን ብትጠብቁ ብትፈጽሟቸውም፥ ከእናንተ ውስጥ የሆኑ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ እንኳ ቢበተኑ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፥ ስሜ እንዲኖርበት ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።” እነዚህም በታላቁ ኃይልህና በብርቱ እጅህ የተቤዠሃቸው ባርያዎችህና ሕዝብህ ናቸው። ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባርያህን ጸሎት፥ ስምህን በመፍራት የሚደሰቱትን የባርያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬ ለባርያህ እባክህን አከናውንለት፥ በዚህም ሰው ፊት ሞገስን ስጠው። እኔም የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።