ማርቆስ 4:30-41

ማርቆስ 4:30-41 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የእግዚአብሔርን መንግሥት ከምን ጋር እናነጻጽራታለን? ወይስ በምን ምሳሌ እንገልጻታለን? የሰናፍጭን ዘር ትመስላለች፤ እርስዋ ስትዘራ በምድር ላይ ካለው ዘር ሁሉ ያነሰች ናት። ከተዘራች በኋላ ግን አድጋ ከአትክልት ሁሉ ትበልጣለች፤ የሰማይ ወፎችም በሥርዋ ጎጆ ሠርተው መጠለል እስኪችሉ ድረስ ታላላቅ ቅርንጫፎችን ታወጣለች።” ኢየሱስም ሰዎች ማስተዋል በሚችሉበት መጠን፥ እነዚህን በመሳሰሉ ብዙ ምሳሌዎች ቃሉን ይነግራቸው ነበር። ያለ ምሳሌም አያስተምራቸውም ነበር፤ ብቻቸውን ሲሆኑ ግን ሁሉን ነገር ለደቀ መዛሙርቱ ያስረዳቸው ነበር። በዚያኑ ቀን ማታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው። ከሕዝቡም ተለይተው ተሳፍሮበት በነበረው ጀልባ ኢየሱስን ይዘውት ሄዱ፤ ሌሎችም ጀልባዎች አብረው ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ተነሥቶ ውሃው በጀልባው እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ ጀልባውን ይመታ ጀመር። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ፥ በጀልባው በኋለኛው ክፍል ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ቀሰቀሱትና “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ጸጥ በል!” አለው፤ ነፋሱ ተወ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። ኢየሱስም፦ “እንዲህ የምትፈሩት ለምንድን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም?” አላቸው። እነርሱም በጣም ፈርተው፥ እርስ በርሳቸው “ኧረ ለመሆኑ፥ ነፋስና ባሕር እንኳ የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።

ማርቆስ 4:30-41 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እርሱም አለ “የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እናስመስላታለን? ወይስ በምን ምሳሌ እንመስላታለን? እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ናት፤ እርስዋም በምድር በተዘራች ጊዜ በምድር ካለ ዘር ሁሉ ታንሳለች፤ በተዘራችም ጊዜ ትወጣለች፤ ከአትክልትም ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች፤ የሰማይ ወፎችም በጥላዋ ሊሰፍሩ እስኪችሉ ታላላቅ ቅርንጫፎች ታደርጋለች።” መስማትም በሚችሉበት መጠን እነዚህን በሚመስል በብዙ ምሳሌ ቃሉን ይነግራቸው ነበር፤ ያለ ምሳሌ ግን አልነገራቸውም፤ ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀ መዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር። በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ “ወደ ማዶ እንሻገር፤” አላቸው። ሕዝቡንም ትተው በታንኳዪቱ ውስጥ እንዳለ ወሰዱት፤ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውሃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት። ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ዝም በል፤ ፀጥ በል፤” አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ። “እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም?” አላቸው። እጅግም ፈሩና “እንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።

ማርቆስ 4:30-41 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ደግሞም እንዲህ አለ፤ “የእግዚአብሔርን መንግሥት ከምን ጋራ እናነጻጽራታለን? በምንስ ምሳሌ እንገልጻታለን? በምድር ላይ ከሚዘራው ዘር ሁሉ እጅግ ያነሰችውን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤ ተዘርታ ካደገች በኋላ ግን፣ በአትክልቱ ቦታ ከሚገኙት ዕፀዋት ሁሉ ትበልጣለች፤ የሰማይ ወፎችም በትልልቅ ቅርንጫፎቿ ጥላ ሥር ያርፋሉ።” ኢየሱስም ሰዎች መረዳት በሚችሉበት መጠን፣ እነዚህን በመሳሰሉ ብዙ ምሳሌዎች ነገራቸው። ምንም ነገር ያለ ምሳሌ አይነግራቸውም ነበር። እርሱና ደቀ መዛሙርቱ ብቻ በሚሆኑበት ጊዜ ግን ሁሉንም ነገር በዝርዝር ያስረዳቸው ነበር። ያ ቀን በመሸ ጊዜ፣ “ወደ ማዶ እንሻገር” አላቸው። እነርሱ ሕዝቡን ትተው በጀልባዋ ውስጥ እንዳለ በዚያው ይዘውት ሄዱ፤ ሌሎች ጀልባዎችም ዐብረውት ነበሩ። በዚህ ጊዜ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ተነሣ፤ ማዕበሉም ውሃ እስኪሞላት ድረስ ጀልባዋን ያናውጣት ነበር። ኢየሱስ ግን ትራስ ተንተርሶ ከጀልባዋ በስተኋላ በኩል ተኝቶ ነበር። እነርሱም ቀስቅሰውት፣ “መምህር ሆይ፤ ስንጠፋ አይገድድህምን?” አሉት። እርሱም ተነሥቶ ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም፣ “ጸጥ፣ ረጭ በል!” አለው። ነፋሱም ጸጥ፣ ረጭ አለ፤ ፍጹምም ጸጥታ ሆነ። ደቀ መዛሙርቱንም፣ “ስለ ምን እንዲህ ፈራችሁ? እስከዚህ እምነት የላችሁምን?” አላቸው። እነርሱም በፍርሀት ተውጠው እርስ በርሳቸው፣ “ነፋሱም ሞገዱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።

ማርቆስ 4:30-41 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እርሱም አለ፦ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እናስመስላታለን? ወይስ በምን ምሳሌ እንመስላታለን? እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ናት፥ እርስዋም በምድር በተዘራች ጊዜ በምድር ካለ ዘር ሁሉ ታንሳለች፤ በተዘራችም ጊዜ ትወጣለች ከአትክልትም ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች፥ የሰማይ ወፎችም በጥላዋ ሊሰፍሩ እስኪችሉ ታላላቅ ቅርንጫፎች ታደርጋለች። መስማትም በሚችሉበት መጠን እነዚህን በሚመስል በብዙ ምሳሌ ቃሉን ይነግራቸው ነበር፤ ያለ ምሳሌ ግን አልነገራቸውም፥ ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀ መዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር። በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ፦ ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው። ሕዝቡንም ትተው በታንኳ እንዲያው ወሰዱት፥ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም፦ መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት። ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንም፦ ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ። እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም? አላቸው። እጅግም ፈሩና፦ እንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? ተባባሉ።

ማርቆስ 4:30-41 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የእግዚአብሔርን መንግሥት ከምን ጋር እናነጻጽራታለን? ወይስ በምን ምሳሌ እንገልጻታለን? የሰናፍጭን ዘር ትመስላለች፤ እርስዋ ስትዘራ በምድር ላይ ካለው ዘር ሁሉ ያነሰች ናት። ከተዘራች በኋላ ግን አድጋ ከአትክልት ሁሉ ትበልጣለች፤ የሰማይ ወፎችም በሥርዋ ጎጆ ሠርተው መጠለል እስኪችሉ ድረስ ታላላቅ ቅርንጫፎችን ታወጣለች።” ኢየሱስም ሰዎች ማስተዋል በሚችሉበት መጠን፥ እነዚህን በመሳሰሉ ብዙ ምሳሌዎች ቃሉን ይነግራቸው ነበር። ያለ ምሳሌም አያስተምራቸውም ነበር፤ ብቻቸውን ሲሆኑ ግን ሁሉን ነገር ለደቀ መዛሙርቱ ያስረዳቸው ነበር። በዚያኑ ቀን ማታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው። ከሕዝቡም ተለይተው ተሳፍሮበት በነበረው ጀልባ ኢየሱስን ይዘውት ሄዱ፤ ሌሎችም ጀልባዎች አብረው ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ተነሥቶ ውሃው በጀልባው እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ ጀልባውን ይመታ ጀመር። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ፥ በጀልባው በኋለኛው ክፍል ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ቀሰቀሱትና “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ጸጥ በል!” አለው፤ ነፋሱ ተወ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። ኢየሱስም፦ “እንዲህ የምትፈሩት ለምንድን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም?” አላቸው። እነርሱም በጣም ፈርተው፥ እርስ በርሳቸው “ኧረ ለመሆኑ፥ ነፋስና ባሕር እንኳ የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።

ማርቆስ 4:30-41 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እርሱም እንዲህ አለ፥ “የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እናስመስላታለን? ወይስ በምን ምሳሌ እንመስላታለን? እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ናት፤ እርሷም በምድር በተዘራች ጊዜ በምድር ካለ ዘር ሁሉ ታንሳለች፤ በተዘራችም ጊዜ ትወጣለች፤ ከአትክልትም ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች፤ የሰማይ ወፎችም በጥላዋ ሊሰፍሩ እስኪችሉ ታላላቅ ቅርንጫፎች ታወጣለች።” መስማትም በሚችሉበት መጠን እነዚህን በሚመስል በብዙ ምሳሌ ቃሉን ይነግራቸው ነበር፤ ያለ ምሳሌ ግን አልነገራቸውም፤ ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀመዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር። በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ “ወደ ማዶ እንሻገር፤” አላቸው። ሕዝቡንም ትተው በታንኳዪቱ ውስጥ እንዳለ ወሰዱት፤ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውሃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ ቀስቅሰውትም “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት። ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ዝም በል፤ ፀጥ በል፤” አለው። ነፋሱም ተወ፤ ታላቅ ፀጥታም ሆነ። “እንዲህ የምትፈሩት ስለምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም?” አላቸው። እጅግም ፈሩና “እንዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።