ማርቆስ 11:1-26
ማርቆስ 11:1-26 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወደ ኢየሩሳሌም በደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ በማለት ላካቸው፤ “በፊታችሁ ወዳለው መንደር ሂዱ፣ ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ የአህያ ውርንጫ እዚያ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡት፤ ማንም፣ ‘ምን ማድረጋችሁ ነው?’ ቢላችሁ፣ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤ እርሱም ወዲያውኑ መልሶ ይልከዋል’ በሉት።” እነርሱም ሄዱ፤ በአንድ ቤት በራፍ መንገድ ላይ የአህያ ውርንጫ ታስሮ አገኙ፤ ፈቱትም። በዚያ ከቆሙት አንዳንድ ሰዎች፣ “ውርንጫውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ ያላቸውን ለሰዎቹ በነገሯቸው ጊዜ ፈቀዱላቸው። ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አምጥተው ልብሶቻቸውን በጀርባው ላይ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት። ብዙ ሰዎች ልብሶቻቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎች ደግሞ ከሜዳ ቅርንጫፍ እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር። የቀደሙትና የተከተሉትም በታላቅ ድምፅ እንዲህ ይሉ ነበር፤ “ሆሳዕና!” “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!” “የምትመጣው የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት!” “ሆሳዕና በአርያም!” ኢየሱስም ኢየሩሳሌም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ ተመለከተ፤ ቀኑም ስለ መሸ ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ወደ ቢታንያ ወጣ። በማግስቱም ከቢታንያ ሲወጡ ኢየሱስ ተራበ። እርሱም ቅጠል ያላት የበለስ ዛፍ ከሩቅ አየ፤ ምናልባት ፍሬ ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ ወደ እርሷ መጣ፤ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። ከዚያም ዛፏን፣ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ” አላት። ደቀ መዛሙርቱም ይህን ሲናገር ሰሙ። ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ፣ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያስወጣ ጀመር። የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛና የርግብ ሻጮችን መቀመጫ ገለባበጠ፤ ማንም ዕቃ ተሸክሞ በቤተ መቅደሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳያልፍ ከለከለ። ሲያስተምራቸውም፣ “ ‘ቤቴ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ አልተጻፈምን? እናንተ ግን ‘የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት!’” አላቸው። የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም፣ ይህን ሲሰሙ እንዴት እንደሚያጠፉት መንገድ ይፈልጉ ጀመር፤ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ በመገረማቸው ፈርተውታልና። በመሸም ጊዜ ከከተማዪቱ ወጥተው ሄዱ። በማግስቱም ጧት በመንገድ ሲያልፉ፣ በለሲቱ ከነሥሯ ደርቃ አዩ። ጴጥሮስ ነገሩ ትዝ አለውና ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፤ እነሆ፤ የረገምሃት በለስ ደርቃለች!” አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “በእግዚአብሔር እመኑ፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ይህን ተራራ፣ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ቢለውና ይህንም በልቡ ሳይጠራጠር ቢያምን ይሆንለታል። ስለዚህ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ እንደ ተቀበላችሁት አድርጋችሁ እመኑ፤ ይሆንላችሁማል። እንዲሁም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ፣ የሰማዩ አባታችሁ በደላችሁን ይቅር እንዲልላችሁ፣ እናንተም በሰው ላይ ያላችሁን ሁሉ ይቅር በሉ። [ይቅር ባትሉ ግን የሰማዩ አባታችሁ በደላችሁን ይቅር አይላችሁም።”]
ማርቆስ 11:1-26 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ወደ ኢየሩሳሌምም ከደብረ ዘይት አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ ወዲያውም ወደ እርስዋ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ። ማንም፦ ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ? ቢላችሁ፦ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉት፥ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል አላቸው። ሄዱም ውርንጫውንም በመንገድ መተላለፊያ በደጅ ውጭ ታስሮ አገኙት፥ ፈቱትም። በዚያም ከቆሙት አንዳንዶቹ፦ ውርንጫውን የምትፈቱት ምን ልታደርጉት ነው አሉአቸው። እነርሱም ኢየሱስ እንዳዘዘ አሉአቸው፤ ተዉአቸውም። ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፥ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፥ ተቀመጠበትም። ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፥ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር። የሚቀድሙትም የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ፤ ዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላ፥ ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከአሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ። በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ። ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፥ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። መልሶም፦ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ። ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ፤ ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም። አስተማራቸውም፦ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው። የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተው፥ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ። ማታ ማታም ከከተማ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር። ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት። ጴጥሮስም ትዝ ብሎት፦ መምህር ሆይ፥ እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ። እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።
ማርቆስ 11:1-26 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም በቀረቡ ጊዜ በቤተ ፋጌና በቢታንያ አድርገው ወደ ደብረ ዘይት ደረሱ፤ ከዚያም ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፦ “በፊታችሁ ወዳለው መንደር ቀድማችሁ ሂዱ፤ እዚያም እንደ ደረሳችሁ ወዲያውኑ ማንም ሰው ገና ያልተቀመጠበት የአህያ ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፍቱትና ወዲህ አምጡት። ማንም ሰው ‘ለምን ይህን ታደርጋላችሁ?’ ቢላችሁ፥ ‘ጌታ ስለሚያስፈልገው ነው፤ ወዲያውኑ መልሶ ይልከዋል፤’ በሉት።” እነርሱም ሄደው ውርንጫውን በመንገድ ዳር በቤት ደጃፍ ታስሮ አገኙትና ፈቱት። በዚያም ጊዜ እዚያ ቆመው ከነበሩት ሰዎች አንዳንዶቹ፦ “ውርንጫውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። እነርሱም ኢየሱስ ያላቸውን ነገሩአቸው፤ ሰዎቹም ተዉአቸው። ደቀ መዛሙርቱም የአህያውን ውርንጫ ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ ልብሳቸውን በውርንጫው ጀርባ ላይ አድርገው ኢየሱስ ተቀመጠበት። ብዙ ሰዎች ሸማቸውን በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር፤ ሌሎችም ከዱር የዛፍ ዝንጣፊ እየቈረጡ በመንገድ ላይ ይጐዘጒዙ ነበር። ከፊት የቀደሙትና ከኋላ የሚከተሉትም ሁሉ፥ “ሆሳዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! የምትመጣው የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሳዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር። ኢየሱስም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዙሪያውም ያለውን ነገር ሁሉ ተመለከተ፤ ቀኑም መሽቶ ስለ ነበር ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ወደ ቢታንያ ሄደ። በማግስቱም ከቢታንያ ሲመለሱ ኢየሱስ ተራበ። ቅጠልዋ የለመለመ የበለስ ዛፍም በሩቅ አይቶ ምናልባት ፍሬ ይገኝባት እንደ ሆነ በማለት ወደ እርስዋ ሄደ፤ ነገር ግን ወደ እርስዋ በቀረበ ጊዜ በለስ የሚያፈራበት ወራት ስላልነበረ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። ስለዚህ ኢየሱስ የበለስዋን ዛፍ፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ!” አላት። ይህንንም ሲናገር ደቀ መዛሙርቱ ሰሙ። ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በውስጡ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሰዎች ያስወጣ ጀመር፤ የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠ፤ ማንም ሰው ምንም ዕቃ ተሸክሞ በቤተ መቅደሱ ግቢ ውስጥ እንዲተላለፍ አልፈቀደም። እንዲህም ሲል አስተማራቸው፤ “ ‘ቤቴ ለሕዝብ ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል!’ ተብሎ አልተጻፈምን? እናንተ ግን የቀማኞች ዋሻ አደረጋችሁት።” የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ይህን ሲናገር ሰሙት፤ ሕዝቡም ሁሉ በትምህርቱ ይደነቁ ስለ ነበር ፈሩት፤ ስለዚህ እንዴት አድርገው እንደሚያጠፉት ዘዴ ይፈልጉ ነበር። በመሸም ጊዜ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከከተማ ወጡ። በማግስቱ ማለዳ በመንገድ ሲያልፉ የበለሲቱ ዛፍ ከነስርዋ ደርቃ አዩአት። ጴጥሮስም ነገሩ ትዝ ብሎት ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ! እነሆ፥ የረገምሃት ዛፍ ደርቃለች” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ሰው በልቡ ሳይጠራጠር የሚፈልገው ነገር እንደሚፈጸምለት አምኖ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነሥተህ ወደ ባሕር ተወርወር፤’ ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ በጸሎት ማናቸውንም ነገር ብትለምኑ፥ እንደ ተፈጸመላችሁ አድርጋችሁ እመኑ፤ የምትለምኑትም ሁሉ ይሰጣችኋል። በሰማይ ያለው አባታችሁ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲልላችሁ እናንተም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ ሰው በአንዳች ነገር አስቀይሞአችሁ ከሆነ ይቅርታ አድርጉለት። እናንተ የሌሎችን በደል ይቅር ባትሉ ግን በሰማይ ያለው አባታችሁ የእናንተንም ኃጢአት ይቅር አይልላችሁም።”
ማርቆስ 11:1-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወደ ኢየሩሳሌምም ከደብረ ዘይት አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ ወዲያውም ወደ እርስዋ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ። ማንም ‘ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ?’ ቢላችሁ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤’ በሉት፤ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል፤” አላቸው። ሄዱም፤ ውርንጫውንም በመንገድ መተላለፊያ በደጅ ውጭ ታስሮ አገኙት፤ ፈቱትም። በዚያም ከቆሙት አንዳንዶቹ “ውርንጫውን የምትፈቱት ምን ልታደርጉት ነው?” አሉአቸው። እነርሱም ኢየሱስ እንዳዘዘ አሉአቸው፤ ተዉአቸውም። ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፤ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፤ ተቀመጠበትም። ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር። የሚቀድሙትም የሚከተሉትም “ሆሣዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር። ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ፤ ዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላ፥ ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ። በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ። ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፤ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። መልሶም “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ፤” አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ። ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ፤ ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም። አስተማራቸውም “‘ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች፤’ ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት፤” አላቸው። የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተው፥ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ። ማታ ማታም ከከተማ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር። ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት። ጴጥሮስም ትዝ ብሎት “መምህር ሆይ! እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች፤” አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው “በእግዚአብሔር እመኑ። እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር፤’ ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፤ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፤ ይሆንላችሁማል። ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኀጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኀጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።”
ማርቆስ 11:1-26 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወደ ኢየሩሳሌም በደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ በማለት ላካቸው፤ “በፊታችሁ ወዳለው መንደር ሂዱ፣ ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ የአህያ ውርንጫ እዚያ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡት፤ ማንም፣ ‘ምን ማድረጋችሁ ነው?’ ቢላችሁ፣ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤ እርሱም ወዲያውኑ መልሶ ይልከዋል’ በሉት።” እነርሱም ሄዱ፤ በአንድ ቤት በራፍ መንገድ ላይ የአህያ ውርንጫ ታስሮ አገኙ፤ ፈቱትም። በዚያ ከቆሙት አንዳንድ ሰዎች፣ “ውርንጫውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ ያላቸውን ለሰዎቹ በነገሯቸው ጊዜ ፈቀዱላቸው። ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አምጥተው ልብሶቻቸውን በጀርባው ላይ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት። ብዙ ሰዎች ልብሶቻቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎች ደግሞ ከሜዳ ቅርንጫፍ እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር። የቀደሙትና የተከተሉትም በታላቅ ድምፅ እንዲህ ይሉ ነበር፤ “ሆሳዕና!” “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!” “የምትመጣው የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት!” “ሆሳዕና በአርያም!” ኢየሱስም ኢየሩሳሌም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ ተመለከተ፤ ቀኑም ስለ መሸ ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ወደ ቢታንያ ወጣ። በማግስቱም ከቢታንያ ሲወጡ ኢየሱስ ተራበ። እርሱም ቅጠል ያላት የበለስ ዛፍ ከሩቅ አየ፤ ምናልባት ፍሬ ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ ወደ እርሷ መጣ፤ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። ከዚያም ዛፏን፣ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ” አላት። ደቀ መዛሙርቱም ይህን ሲናገር ሰሙ። ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ፣ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያስወጣ ጀመር። የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛና የርግብ ሻጮችን መቀመጫ ገለባበጠ፤ ማንም ዕቃ ተሸክሞ በቤተ መቅደሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳያልፍ ከለከለ። ሲያስተምራቸውም፣ “ ‘ቤቴ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ አልተጻፈምን? እናንተ ግን ‘የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት!’” አላቸው። የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም፣ ይህን ሲሰሙ እንዴት እንደሚያጠፉት መንገድ ይፈልጉ ጀመር፤ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ በመገረማቸው ፈርተውታልና። በመሸም ጊዜ ከከተማዪቱ ወጥተው ሄዱ። በማግስቱም ጧት በመንገድ ሲያልፉ፣ በለሲቱ ከነሥሯ ደርቃ አዩ። ጴጥሮስ ነገሩ ትዝ አለውና ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፤ እነሆ፤ የረገምሃት በለስ ደርቃለች!” አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “በእግዚአብሔር እመኑ፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ይህን ተራራ፣ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ቢለውና ይህንም በልቡ ሳይጠራጠር ቢያምን ይሆንለታል። ስለዚህ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ እንደ ተቀበላችሁት አድርጋችሁ እመኑ፤ ይሆንላችሁማል። እንዲሁም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ፣ የሰማዩ አባታችሁ በደላችሁን ይቅር እንዲልላችሁ፣ እናንተም በሰው ላይ ያላችሁን ሁሉ ይቅር በሉ። [ይቅር ባትሉ ግን የሰማዩ አባታችሁ በደላችሁን ይቅር አይላችሁም።”]
ማርቆስ 11:1-26 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ወደ ኢየሩሳሌምም ከደብረ ዘይት አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ ወዲያውም ወደ እርስዋ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ። ማንም፦ ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ? ቢላችሁ፦ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉት፥ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል አላቸው። ሄዱም ውርንጫውንም በመንገድ መተላለፊያ በደጅ ውጭ ታስሮ አገኙት፥ ፈቱትም። በዚያም ከቆሙት አንዳንዶቹ፦ ውርንጫውን የምትፈቱት ምን ልታደርጉት ነው አሉአቸው። እነርሱም ኢየሱስ እንዳዘዘ አሉአቸው፤ ተዉአቸውም። ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፥ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፥ ተቀመጠበትም። ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፥ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር። የሚቀድሙትም የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ፤ ዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላ፥ ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከአሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ። በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ። ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፥ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። መልሶም፦ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ። ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ፤ ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም። አስተማራቸውም፦ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው። የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተው፥ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ። ማታ ማታም ከከተማ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር። ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት። ጴጥሮስም ትዝ ብሎት፦ መምህር ሆይ፥ እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ። እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።
ማርቆስ 11:1-26 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም በቀረቡ ጊዜ በቤተ ፋጌና በቢታንያ አድርገው ወደ ደብረ ዘይት ደረሱ፤ ከዚያም ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፦ “በፊታችሁ ወዳለው መንደር ቀድማችሁ ሂዱ፤ እዚያም እንደ ደረሳችሁ ወዲያውኑ ማንም ሰው ገና ያልተቀመጠበት የአህያ ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፍቱትና ወዲህ አምጡት። ማንም ሰው ‘ለምን ይህን ታደርጋላችሁ?’ ቢላችሁ፥ ‘ጌታ ስለሚያስፈልገው ነው፤ ወዲያውኑ መልሶ ይልከዋል፤’ በሉት።” እነርሱም ሄደው ውርንጫውን በመንገድ ዳር በቤት ደጃፍ ታስሮ አገኙትና ፈቱት። በዚያም ጊዜ እዚያ ቆመው ከነበሩት ሰዎች አንዳንዶቹ፦ “ውርንጫውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። እነርሱም ኢየሱስ ያላቸውን ነገሩአቸው፤ ሰዎቹም ተዉአቸው። ደቀ መዛሙርቱም የአህያውን ውርንጫ ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ ልብሳቸውን በውርንጫው ጀርባ ላይ አድርገው ኢየሱስ ተቀመጠበት። ብዙ ሰዎች ሸማቸውን በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር፤ ሌሎችም ከዱር የዛፍ ዝንጣፊ እየቈረጡ በመንገድ ላይ ይጐዘጒዙ ነበር። ከፊት የቀደሙትና ከኋላ የሚከተሉትም ሁሉ፥ “ሆሳዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! የምትመጣው የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሳዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር። ኢየሱስም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዙሪያውም ያለውን ነገር ሁሉ ተመለከተ፤ ቀኑም መሽቶ ስለ ነበር ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ወደ ቢታንያ ሄደ። በማግስቱም ከቢታንያ ሲመለሱ ኢየሱስ ተራበ። ቅጠልዋ የለመለመ የበለስ ዛፍም በሩቅ አይቶ ምናልባት ፍሬ ይገኝባት እንደ ሆነ በማለት ወደ እርስዋ ሄደ፤ ነገር ግን ወደ እርስዋ በቀረበ ጊዜ በለስ የሚያፈራበት ወራት ስላልነበረ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። ስለዚህ ኢየሱስ የበለስዋን ዛፍ፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ!” አላት። ይህንንም ሲናገር ደቀ መዛሙርቱ ሰሙ። ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በውስጡ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሰዎች ያስወጣ ጀመር፤ የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠ፤ ማንም ሰው ምንም ዕቃ ተሸክሞ በቤተ መቅደሱ ግቢ ውስጥ እንዲተላለፍ አልፈቀደም። እንዲህም ሲል አስተማራቸው፤ “ ‘ቤቴ ለሕዝብ ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል!’ ተብሎ አልተጻፈምን? እናንተ ግን የቀማኞች ዋሻ አደረጋችሁት።” የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ይህን ሲናገር ሰሙት፤ ሕዝቡም ሁሉ በትምህርቱ ይደነቁ ስለ ነበር ፈሩት፤ ስለዚህ እንዴት አድርገው እንደሚያጠፉት ዘዴ ይፈልጉ ነበር። በመሸም ጊዜ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከከተማ ወጡ። በማግስቱ ማለዳ በመንገድ ሲያልፉ የበለሲቱ ዛፍ ከነስርዋ ደርቃ አዩአት። ጴጥሮስም ነገሩ ትዝ ብሎት ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ! እነሆ፥ የረገምሃት ዛፍ ደርቃለች” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ሰው በልቡ ሳይጠራጠር የሚፈልገው ነገር እንደሚፈጸምለት አምኖ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነሥተህ ወደ ባሕር ተወርወር፤’ ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ በጸሎት ማናቸውንም ነገር ብትለምኑ፥ እንደ ተፈጸመላችሁ አድርጋችሁ እመኑ፤ የምትለምኑትም ሁሉ ይሰጣችኋል። በሰማይ ያለው አባታችሁ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲልላችሁ እናንተም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ ሰው በአንዳች ነገር አስቀይሞአችሁ ከሆነ ይቅርታ አድርጉለት። እናንተ የሌሎችን በደል ይቅር ባትሉ ግን በሰማይ ያለው አባታችሁ የእናንተንም ኃጢአት ይቅር አይልላችሁም።”
ማርቆስ 11:1-26 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ወደ ኢየሩሳሌም በደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፥ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ በማለት ላካቸው፦ በፊታችሁ ወዳለው መንደር ሂዱ፥ ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ የአህያ ውርንጫ እዚያ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈታችሁ አምጡት፤ ማንም፥ “ምን ማድረጋችሁ ነው?” ቢላችሁ፥ “ለጌታ ያስፈልገዋል፤ በቶሎም መልሶ ይልከዋል” ብላችሁ ንገሩት። እነርሱም ሄዱ፤ በአንድ ቤት በራፍ እመንገድ ላይ የአህያ ውርንጫ ታስሮ አገኙት፤ ፈቱትም። በዚያ ከቆሙት አንዳንድ ሰዎች፥ “ውርንጫውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ ያላቸውን ለሰዎቹ በነገሯቸው ጊዜ ፈቀዱላቸው። ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አምጥተው ልብሳቸውን በጀርባው ላይ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት። ብዙ ሰዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎች ደግሞ ለምለም የዛፍ ቅርንጫፍ እየቆረጡ ያነጥፉ ነበር። ከፊቱ የቀደሙትና ከኋላው የተከተሉትም በታላቅ ድምፅ፤ እንዲህ ይሉ ነበር፤ “ሆሣዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው የምትመጣው የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት! ሆሣዕና በአርአያም!” ኢየሱስም ኢየሩሳሌም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ ተመለከተ፤ ቀኑም ስለመሸ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ። በማግሥቱ ከቢታንያ ሲወጡ ኢየሱስ ተራበ። እርሱም ቅጠል ያላት የበለስ ዛፍ ከሩቅ አየ፤ ምናልባት ፍሬ ይገኝባት እንደሆነ ብሎ ወደ እርሷ መጣ፤ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። ከዚያም ዛፏን፥ “ከአሁን ጀምሮ ለዘለዓለም ማንም ፍሬ ከአንቺ አይብላ” አላት። ደቀ መዛሙርቱም ይህን ሲናገር ሰሙ። ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ፥ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያስወጣ ጀመር። የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛና የርግብ ሻጮችን መቀመጫ ገለባበጠ፤ ማንም ዕቃ ተሸክሞ በቤተ መቅደሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳያልፍ ከለከለ። ሲያስተምራቸውም፥ “ቤቴ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል፥ ተብሎ አልተጻፈምን? እናንተ ግን የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት” አላቸው። የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም፥ ይህን ሲሰሙ እንዴት እንደሚያጠፉት መንገድ ይፈልጉ ጀመር፤ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ በመገረማቸው ፈርተውታልና። በመሸም ጊዜ ከከተማዪቱ ወጥተው ሄዱ። በማግስቱ ጠዋት በመንገድ ሲያልፉ፥ በለሲቱ ከነሥሯ ደርቃ አዩ። ጴጥሮስ ነገሩ ትዝ አለውና ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ፤ እነሆ፤ የረገምካት በለስ ደርቃለች” አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “በእግዚአብሔር እመኑ፤” እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ይህን ተራራ፥ “ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር” ቢለውና ይህንንም በልቡ ሳይጠራጠር ቢያምን ይሆንለታል። ስለዚህ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ እንደ ተቀበላችሁት አድርጋችሁ ብታምኑ ይሆንላችኋል። እንዲሁም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ፥ የሰማዩ አባታችሁ ኀጢአታችሁን ይቅር እንዲልላችሁ፥ እናንተም በሰው ላይ ያላችሁን ሁሉ ይቅር በሉ። ይቅር ባትሉ ግን የሰማዩ አባታችሁ ኀጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።