ማቴዎስ 18:32-35
ማቴዎስ 18:32-35 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ ‘አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን?’ አለው። ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው። ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።”
ማቴዎስ 18:32-35 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“በዚህ ጊዜ ጌታው ባሪያውን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ ‘አንተ ክፉ ባሪያ፤ ስለ ለመንኸኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ አንተም ባልንጀራህን ልትምረው አይገባህም ነበርን?’ በቍጣም ያለበትን ዕዳ ከፍሎ እስኪጨርስ ድረስ ለአሳሪዎች አሳልፎ ሰጠው። “ስለዚህ እያንዳንዳችሁ ወንድሞቻችሁን ከልባችሁ ይቅር ካላላችሁ፣ የሰማዩ አባቴም እንደዚሁ ያደርግባችኋል።”
ማቴዎስ 18:32-35 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ፦ አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው። ጌታውም ተቍኦጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው። ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።
ማቴዎስ 18:32-35 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ጌትዮውም ያን አገልጋይ አስጠርቶ እንዲህ አለው፦ ‘አንተ ክፉ አገልጋይ! ስለ ለመንከኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውኩልህ፤ ታዲያ፥ እኔ ዕዳህን እንደ ተውኩልህ፥ አንተስ ባልንጀራህ ለሆነው አገልጋይ ዕዳውን ልትተውለት አይገባህም ነበርን?’ ስለዚህ ጌታው ተቈጥቶ ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍል ድረስ ለወህኒ ቤቱ ኀላፊዎች አሳልፎ ሰጠው። “እንግዲህ እናንተም እያንዳንዳችሁ ወንድማችሁን ከልብ ይቅር ባትሉ በሰማይ ያለው አባቴም እንዲሁ ያደርግባችኋል።”