የማ​ቴ​ዎስ ወን​ጌል 18:32-35

የማ​ቴ​ዎስ ወን​ጌል 18:32-35 አማ2000

ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ ‘አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን?’ አለው። ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው። ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።”

ተዛማጅ ቪዲዮዎች