ማቴዎስ 11:2-4
ማቴዎስ 11:2-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና፦ የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ? አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት፤
Share
ማቴዎስ 11 ያንብቡማቴዎስ 11:2-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
መጥምቁ ዮሐንስ በወህኒ ቤት ሳለ፥ የክርስቶስን ሥራ በመሰማቱ ሁለት ደቀ መዛሙርት ልኮ፥ “ያ ይመጣል የተባለው መሲሕ አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ብለው ኢየሱስን እንዲጠይቁት አደረገ። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሂዱና ያያችሁትንና የሰማችሁትን ሁሉ ለዮሐንስ ንገሩት።
Share
ማቴዎስ 11 ያንብቡማቴዎስ 11:2-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና “የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው “ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ ንገሩት፤
Share
ማቴዎስ 11 ያንብቡ