ሚልክያስ 1:11-13
ሚልክያስ 1:11-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ የእግዚአብሔር ገበታ ርኩስ ነው፣ ፍሬውና መብሉም የተናቀ ነው በማለታችሁ አስነቀፋችሁት። እናንተ፦ እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በቅሚያ የያዛችሁትንም አንካሳውንም የታመመውንም አቅርባችኋል፣ እንዲሁ ቍርባንን ታመጣላችሁ፣ በውኑ ከእጃችሁ ይህን ልቀበለውን? ይላል እግዚአብሔር።
ሚልክያስ 1:11-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ከፀሓይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ፣ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናል፤ በየስፍራውም ሁሉ ለስሜ ዕጣንና ንጹሕ ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናልና” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት። “እናንተ ግን የእግዚአብሔር ገበታ፣ ‘ርኩስ ነው’ ምግቡም፣ ‘የተናቀ ነው’ በማለት ታቃልላላችሁ። ደግሞም፣ ‘ይህ ድካም ነው’ በማለት በንቀት ጢቅ አላችሁበት” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት። “በቅሚያ የመጣውን፣ ዐንካሳውንና የታመመውን እንስሳ ቍርባን አድርጋችሁ ስታቀርቡ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል እግዚአብሔር፤
ሚልክያስ 1:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፥ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ የእግዚአብሔር ገበታ ርኩስ ነው፥ ፍሬውና መብሉም የተናቀ ነው በማለታችሁ አስነቀፋችሁት። እናንተ፦ እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ በቅሚያ የያዛችሁትንም አንካሳውንም የታመመውንም አቅርባችኋል፥ እንዲሁ ቍርባንን ታመጣላችሁ፥ በውኑ ከእጃችሁ ይህን ልቀበለውን? ይላል እግዚአብሔር።
ሚልክያስ 1:11-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል። እናንተ ግን ‘የእግዚአብሔር መሠዊያ የረከሰ ነው’ ብላችሁ የተናቀ መሥዋዕት ባቀረባችሁ ጊዜ አረከሳችሁት። እነሆ፥ እናንተ እየተሳለቃችሁ ‘ይህ ሁሉ ምን አሰልቺ ነገር ነው!’ ትላላችሁ። የተሰረቀውን፥ አንካሳውን ወይም የታመመውን እንስሳ ለመሥዋዕትነት ታቀርባላችሁ፤ እኔ ይህን የምቀበል ይመስላችኋልን?
ሚልክያስ 1:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
“ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፤ በሁሉም ስፍራ ለስሜ ዕጣን ያመጣሉ፥ ንጹሕ ቁርባንም ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፥” ይላል የሠራዊት ጌታ። እናንተ ግን፦ “የጌታ ገበታ የረከሰ ነው፤ ፍሬውና ምግቡም የተናቀ ነው በማለታችሁ አረከሳችሁት። “እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ “የተሰረቀውን፥ አንካሳውንና የታመመውን አምጥታችኋል፤ እንዲሁም ቁርባንን አምጥታችኋል፤ በውኑ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል ጌታ።