የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ሚልክያስ 1:11-13

ትንቢተ ሚልክያስ 1:11-13 መቅካእኤ

“ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፤ በሁሉም ስፍራ ለስሜ ዕጣን ያመጣሉ፥ ንጹሕ ቁርባንም ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፥” ይላል የሠራዊት ጌታ። እናንተ ግን፦ “የጌታ ገበታ የረከሰ ነው፤ ፍሬውና ምግቡም የተናቀ ነው በማለታችሁ አረከሳችሁት። “እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ “የተሰረቀውን፥ አንካሳውንና የታመመውን አምጥታችኋል፤ እንዲሁም ቁርባንን አምጥታችኋል፤ በውኑ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል ጌታ።