ሉቃስ 8:10 - Compare All Versions

ሉቃስ 8:10 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ምሥ​ጢር ማወቅ ለእ​ና​ንተ ተሰ​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ ለእ​ነ​ዚያ ግን አይ​ተው እን​ዳ​ያዩ፥ ሰም​ተ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም በም​ሳሌ ነው።

ሉቃስ 8:10 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እርሱም እንዲህ አለ፤ “የእግዚአብሔርን መንግሥት ምስጢር ማወቅ ለእናንተ ተሰጥቷል፤ ለሌሎች ግን በምሳሌ እናገራለሁ፤ ይኸውም፣ “ ‘እያዩ ልብ እንዳይሉ፣ እየሰሙም እንዳያስተውሉ ነው።’

ሉቃስ 8:10 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እርሱም እንዲህ አለ፦ ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለሌሎች ግን እያዩ እንዳያዩ እየሰሙም እንዳያስተውሉ በምሳሌ ነው።

ሉቃስ 8:10 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ሌሎች ግን ሁሉ ነገር በምሳሌ ይነገራቸዋል፤ እነርሱ እያዩ ልብ እንዳያደርጉ፥ እየሰሙም እንዳያስተውሉ ነው።”

ሉቃስ 8:10 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እርሱም “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለሌሎች ግን እያዩ እንዳያዩ እየሰሙም እንዳያስተውሉ በምሳሌዎች ይነገራቸዋል” አላቸው።