ሉቃስ 7:41-43
ሉቃስ 7:41-43 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እርሱም እንዲህ አለው፥ “ለአንድ አበዳሪ ሁለት ባለ ዕዳዎች ነበሩት፤ በአንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት፤ በሁለተኛውም አምሳ። የሚከፍሉትም ባጡ ጊዜ ለሁለቱም ተወላቸው፤ እንግዲህ ከሁለቱ አብልጦ ሊወደው የሚገባው ማንኛው ነው?” ስምዖንም መልሶ፥ “ብዙውን የተወለት ነው እላለሁ” አለው፤ እርሱም፥ “መልካም ፈረድህ” አለው።
ሉቃስ 7:41-43 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ አንደኛው አምስት መቶ ዲናር፣ ሁለተኛው ደግሞ አምሳ ዲናር ነበረበት። የሚከፍሉትም ቢያጡ ዕዳቸውን ለሁለቱም ተወላቸው። እንግዲህ ከሁለቱ አበዳሪውን አብልጦ የሚወድደው የትኛው ነው?” ስምዖንም፣ “ብዙው ዕዳ የተተወለት ይመስለኛል” ሲል መለሰ። ኢየሱስም፣ “ትክክል ፈርደሃል” አለው።
ሉቃስ 7:41-43 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ለአንድ አበዳሪ ሁለት ተበዳሪዎች ነበሩት በአንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት በሁለተኛውም አምሳ። የሚከፍሉትም ቢያጡ ለሁለቱም ተወላቸው። እንግዲህ ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው ማንኛው ነው? ስምዖንም መልሶ፦ ብዙ የተወለቱ ይመስለኛል አለ። እርሱም፦ በእውነት ፈረድህ አለው።
ሉቃስ 7:41-43 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስም እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፤ “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ አንዱ አምስት መቶ ዲናር ሌላው ደግሞ ኀምሳ ዲናር ተበደሩ፤ ሁለቱም የተበደሩትን መክፈል ቢያቅታቸው አበዳሪው ዕዳቸውን ተወላቸው፤ ታዲያ፥ ከሁለቱ ባለዕዳዎች፥ አበዳሪውን አብልጦ የሚወድ የትኛው ይመስልሃል?” አለው። ስምዖንም፦ “ብዙ ዕዳ የቀረለት ሰው አብልጦ የሚወደው ይመስለኛል፤” ሲል መለሰ። ኢየሱስም “መልስህ ልክ ነው፤” አለው።