ሉቃስ 18:3-5
ሉቃስ 18:3-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፤ ዕለት ዕለትም ወደ እርሱ እየመጣች ከባለጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። እንቢ ብሎም አዘገያት። ከዚህም በኋላ በልቡ ዐስቦ እንዲህ አለ፦ ‘ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ፥ ሰውንም ባላፍር ይህቺ ሴት እንዳትዘበዝበኝ፥ ዘወትርም እየመጣች እንዳታታክተኝ እፈርድላታለሁ’።”
Share
ሉቃስ 18 ያንብቡሉቃስ 18:3-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በዚያችው ከተማ የምትኖር አንዲት መበለት ነበረች፤ እርሷም፣ ‘ከባላጋራዬ ጋር ስላለብኝ ጕዳይ ፍረድልኝ’ እያለች ወደ እርሱ ትመላለስ ነበር። “ዳኛውም ለተወሰነ ጊዜ አልተቀበላትም ነበር፤ በኋላ ግን በልቡ እንዲህ አለ፤ ‘ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ፣ ሰውንም ባላከብር፣ ይህች መበለት ስለምትጨቀጭቀኝ እፈርድላታለሁ፤ አለዚያ ዘወትር እየተመላለሰች ታሰለቸኛለች።’ ”
Share
ሉቃስ 18 ያንብቡሉቃስ 18:3-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች፦ ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፦ ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ።
Share
ሉቃስ 18 ያንብቡ