የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሉቃስ 12:22-28

ሉቃስ 12:22-28 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ለደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ህ​ዋ​ለሁ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ስለ​ም​ት​በ​ሉ​ትና ስለ​ም​ት​ጠ​ጡት፥ ለሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁም ስለ​ም​ት​ለ​ብ​ሱት አት​ጨ​ነቁ። ነፍስ ከም​ግብ ትበ​ል​ጣ​ለ​ችና፤ ሰው​ነ​ትም ከል​ብስ ይበ​ል​ጣ​ልና። የማ​ይ​ዘ​ሩ​ት​ንና የማ​ያ​ጭ​ዱ​ትን፥ ጎተ​ራና ጕድ​ጓድ የሌ​ላ​ቸ​ውን የቍ​ራ​ዎ​ችን ጫጭ​ቶች ተመ​ል​ከቱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ይመ​ግ​ባ​ቸ​ዋል፤ እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ከወ​ፎች እን​ዴት እጅግ አት​በ​ል​ጡም? ከእ​ና​ን​ተስ ዐስቦ በቁ​መቱ ላይ አንድ ክንድ መጨ​መር የሚ​ቻ​ለው ማነው? ይህን ቀላ​ሉን የማ​ት​ችሉ ከሆነ በሌ​ላው ለምን ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ? እነሆ፥ አበ​ባ​ዎ​ችን እን​ደ​ሚ​ያ​ድጉ ተመ​ል​ከቱ፤ አይ​ፈ​ት​ሉም፤ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ ነገር ግን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሰሎ​ሞን እንኳ በክ​ብሩ ዘመን ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ አል​ለ​በ​ሰም። እነሆ፥ ዛሬ ያለ​ውን፥ ነገም ወደ እሳት የሚ​ጣ​ለ​ውን የአ​በባ አገዳ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ከሆነ፥ እና​ንተ እም​ነት የጐ​ደ​ላ​ችሁ፥ ለእ​ና​ን​ተማ እን​ዴት አብ​ልጦ አያ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ?

ሉቃስ 12:22-28 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “ስለዚህ ለሕወታችሁ ‘ምን እንበላለን? ለሰውነታችሁም ምን እንለብሳለን?’ በማለት ስለ ኑሮአችሁ አትጨነቁ እላችኋለሁ። ከምግብ ሕይወት፥ ከልብስም ሰውነት ይበልጣል። እስቲ ቊራዎችን ተመልከቱ! እነርሱ አይዘሩም ወይም አያጭዱም፤ የእህል ማከማቻ ቦታ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይመግባቸዋል፤ እናንተማ ከወፎች የቱን ያኽል ትበልጣላችሁ! ለመሆኑ ከእናንተ መካከል በመጨነቅ በዕድሜው ላይ አንድ ቀን መጨመር የሚችል ማን ነው? እንግዲህ ይህን ትንሹን ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆናችሁ፥ ስለምን በሌላው ነገር ትጨነቃላችሁ? የአሸንድዬ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ እስቲ ተመልከቱ፤ እነርሱ በሥራ አይደክሙም፤ አይፈትሉም፤ ይሁን እንጂ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ ከእነርሱ እንደ አንዲቱ ያጌጠ ልብስ አለበሰም። ታዲያ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ታይቶ ነገ በእሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር እንዲህ አስጊጦ የሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፥ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም!