የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሉቃስ 1:26-33

ሉቃስ 1:26-33 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወር መል​አኩ ገብ​ር​ኤል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ስሟ ናዝ​ሬት ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ አን​ዲት የገ​ሊላ ከተማ ከዳ​ዊት ወገን ለሚ​ሆን ዮሴፍ ለሚ​ባል ሰው ወደ ታጨ​ችው ወደ አን​ዲት ድን​ግል ተላከ፤ የዚ​ያ​ችም ድን​ግል ስምዋ ማር​ያም ይባል ነበረ። መል​አ​ኩም ወደ እር​ስዋ ገብቶ፥ “ደስ ያለሽ፥ ጸጋ​ንም የተ​መ​ላሽ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካንቺ ጋር ነው፤ ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተሽ አንቺ የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ” አላት። እር​ስ​ዋም በአ​የ​ችው ጊዜ ከአ​ነ​ጋ​ገሩ የተ​ነሣ ደነ​ገ​ጠ​ችና “ይህ እን​ዴት ያለ ሰላ​ምታ ነው?” ብላ ዐሰ​በች። መል​አ​ኩም እን​ዲህ አላት፥ “ማር​ያም ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አግ​ኝ​ተ​ሻ​ልና አት​ፍሪ። እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ስሙ​ንም ኢየ​ሱስ ትይ​ዋ​ለሽ። እር​ሱም ታላቅ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ዙፋን ይሰ​ጠ​ዋል። ለያ​ዕ​ቆብ ወገ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ይነ​ግ​ሣል፤ ለመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ፍጻሜ የለ​ውም።”