የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 1

1
ወን​ጌ​ልን ስለ መጻፍ
1በእኛ ዘንድ የተ​ፈ​ጸ​መ​ው​ንና የታ​መ​ነ​ውን የሥ​ራ​ውን ዜና በሥ​ር​ዐት ሊጽፉ የጀ​መሩ ብዙ​ዎች ናቸው። 2ከእኛ አስ​ቀ​ድሞ በዐ​ይን ያዩ​ትና የቃሉ አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በሩ እንደ አስ​ተ​ላ​ለ​ፉ​ልን፤ 3የከ​በ​ርህ ቴዎ​ፍ​ሎስ ሆይ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ተከ​ትዬ፥ ሁሉ​ንም በየ​ተ​ራው እው​ነ​ተ​ኛ​ውን እጽ​ፍ​ልህ ዘንድ መል​ካም ሁኖ ታየኝ። 4የተ​ማ​ር​ኸ​ውን የነ​ገ​ሩን እው​ነት ጠን​ቅ​ቀህ ታውቅ ዘንድ።
ስለ ዘካ​ር​ያ​ስና ስለ ኤል​ሳ​ቤጥ
5 # 1ዜ.መ. 24፥10። በይ​ሁዳ ንጉሥ በሄ​ሮ​ድስ ዘመን ከአ​ብያ ክፍል የሆነ ዘካ​ር​ያስ የሚ​ባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስ​ቱም ከአ​ሮን ልጆች ወገን ነበ​ረች፤ ስም​ዋም ኤል​ሳ​ቤጥ ነበረ። 6ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ። 7ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።
8እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በተ​ራው የክ​ህ​ነ​ትን ሥራ በሚ​ሠ​ራ​በት ጊዜ፥ 9ካህ​ናት እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት የሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጊዜ ደረሰ፤#በግ​ሪኩ “ዕጣ ደረ​ሰው” ይላል። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደ​ስም ገባ። 10ዕጣን በሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጊዜም ሕዝቡ በሙሉ በውጭ ይጸ​ልዩ ነበር። 11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በዕ​ጣን መሠ​ው​ያው በስ​ተ​ቀኝ ቆሞ ታየው። 12ዘካ​ር​ያ​ስም ባየው ጊዜ ደነ​ገጠ፤ ፍር​ሀ​ትም ረዓ​ድም ወረ​ደ​በት። 13መል​አ​ኩም እን​ዲህ አለው፥ “ዘካ​ር​ያስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ ጸሎ​ትህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፤ ሚስ​ትህ ኤል​ሣ​ቤ​ጥም ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ዮሐ​ንስ ትለ​ዋ​ለህ። 14ደስ​ታና ሐሤ​ትም ይሆ​ን​ል​ሃል፤ በመ​ወ​ለ​ዱም ብዙ​ዎች ደስ ይላ​ቸ​ዋል። 15#ዘኍ​. 6፥3። እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታላቅ ይሆ​ና​ልና የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ ሁሉ አይ​ጠ​ጣም፤ ከእ​ናቱ ማሕ​ፀን ጀም​ሮም መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​በ​ታል። 16ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ብዙ​ዎ​ችን ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ሳ​ቸ​ዋል። 17#ሚል. 4፥5-6። እር​ሱም የአ​ባ​ቶ​ችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከ​ሓ​ድ​ያ​ን​ንም ዐሳብ ወደ ጻድ​ቃን ዕው​ቀት ይመ​ልስ ዘንድ፥ ሕዝ​ብ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ዘ​ጋጀ ያደ​ርግ ዘንድ በኤ​ል​ያስ መን​ፈ​ስና ኀይል በፊቱ ይሄ​ዳል።” 18ዘካ​ር​ያ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ እን​ዲህ አለው፥ “ይህ እን​ደ​ሚ​ሆን በምን አው​ቃ​ለሁ? እነሆ፥ እኔ አር​ጅ​ች​አ​ለሁ፤ የሚ​ስ​ቴም ዘመ​ንዋ አል​ፏል።” 19#ዳን. 8፥16፤ 9፥21። መል​አ​ኩም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የም​ቆ​መው ገብ​ር​ኤል ነኝ፤ ይህ​ንም እነ​ግ​ር​ህና አበ​ሥ​ርህ ዘንድ ወደ አንተ ተል​ኬ​አ​ለሁ። 20አሁ​ንም በጊ​ዜው የሚ​ሆ​ነ​ው​ንና የሚ​ፈ​ጸ​መ​ውን ነገ​ሬን አላ​መ​ን​ኽ​ኝ​ምና ይህ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ዲዳ ትሆ​ና​ለህ፤ መና​ገ​ርም ይሳ​ን​ሃል።” 21ሕዝቡ ግን ዘካ​ር​ያ​ስን ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ በቤተ መቅ​ደስ ውስጥ ዘግ​ይቶ ነበ​ርና እጅግ ተደ​ነቁ። 22ወደ እነ​ርሱ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜም እነ​ር​ሱን ማነ​ጋ​ገር ተሳ​ነው፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም የተ​ገ​ለ​ጠ​ለት እን​ዳለ ዐወቁ፤ እን​ዲ​ሁም ዲዳ ሆኖ በእጁ እያ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸው ኖረ። 23ከዚ​ህም በኋላ የማ​ገ​ል​ገሉ ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ።
24ከእ​ነ​ዚ​ያም ቀኖች በኋላ#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ትር​ጕም “ከሁ​ለት ቀኖች በኋላ” ይላል። ሚስቱ ኤል​ሳ​ቤጥ ፀነ​ሰች፤ ፅን​ስ​ዋ​ንም ለአ​ም​ስት ወር ሸሸ​ገች፤ እን​ዲህ ስትል፦ 25“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ወራት ከሰው ስድ​ቤን ያርቅ ዘንድ በጐ​በ​ኘኝ ጊዜ እን​ዲህ አደ​ረ​ገ​ልኝ።”
ቅዱስ ገብ​ር​ኤል እመ​ቤ​ታ​ች​ንን እንደ አበ​ሠ​ራት
26በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወር መል​አኩ ገብ​ር​ኤል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ስሟ ናዝ​ሬት ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ አን​ዲት የገ​ሊላ ከተማ ከዳ​ዊት ወገን ለሚ​ሆን ዮሴፍ ለሚ​ባል ሰው ወደ ታጨ​ችው ወደ አን​ዲት ድን​ግል ተላከ፤ 27#ማቴ. 1፥18። የዚ​ያ​ችም ድን​ግል ስምዋ ማር​ያም ይባል ነበረ። 28መል​አ​ኩም ወደ እር​ስዋ ገብቶ፥ “ደስ ያለሽ፥#“ደስ ያለሽ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ የለም። ጸጋ​ንም የተ​መ​ላሽ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካንቺ ጋር ነው፤ ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተሽ አንቺ የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ” አላት። 29እር​ስ​ዋም በአ​የ​ችው ጊዜ ከአ​ነ​ጋ​ገሩ የተ​ነሣ ደነ​ገ​ጠ​ችና “ይህ እን​ዴት ያለ ሰላ​ምታ ነው?” ብላ ዐሰ​በች። 30መል​አ​ኩም እን​ዲህ አላት፥ “ማር​ያም ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አግ​ኝ​ተ​ሻ​ልና አት​ፍሪ። 31#ማቴ. 1፥21። እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ስሙ​ንም ኢየ​ሱስ ትይ​ዋ​ለሽ። 32እር​ሱም ታላቅ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ዙፋን ይሰ​ጠ​ዋል። 33#2ሳሙ. 7፥12-13፤ 16፤ ኢሳ. 9፥7። ለያ​ዕ​ቆብ ወገ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ይነ​ግ​ሣል፤ ለመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ፍጻሜ የለ​ውም።” 34ማር​ያ​ምም መል​አ​ኩን፥ “ወንድ ስለ​ማ​ላ​ውቅ ይህ እን​ዴት ይሆ​ን​ል​ኛል?” አለ​ችው። 35መል​አ​ኩም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያድ​ር​ብ​ሻል፤ የል​ዑል ኀይ​ልም ይጋ​ር​ድ​ሻል፤ ከአ​ንቺ የሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ቅዱስ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል። 36እነሆ፥ ከዘ​መ​ዶ​ችሽ ወገን የም​ት​ሆን ኤል​ሣ​ቤ​ጥም እር​ስዋ እንኳ በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ፀን​ሳ​ለች፤ መካን ትባል የነ​በ​ረ​ችው ከፀ​ነ​ሰች እነሆ፥ ይህ ስድ​ስ​ተኛ ወር ነው። 37#ዘፍ. 18፥14። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር የለ​ምና”። 38ማር​ያ​ምም መል​አ​ኩን፥ “እነ​ሆኝ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያው አለሁ፤ እንደ ቃልህ ይሁ​ን​ልኝ” አለ​ችው፤ ከዚህ በኋ​ላም መል​አኩ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ ሄደ።
ማር​ያም ወደ ኤል​ሣ​ቤጥ ስለ መሄ​ድዋ
39በዚ​ያም ወራት ማር​ያም ፈጥና ተነ​ሣች፤ ወደ ተራ​ራ​ማው ሀገር#ግእዙ “ደወለ ዐይነ ከርም” ይላል። ወደ ይሁዳ ከተ​ማም ደረ​ሰች። 40ወደ ዘካ​ር​ያስ ቤትም ገብታ ለኤ​ል​ሣ​ቤጥ ሰላ​ምታ ሰጠ​ቻት። 41ኤል​ሳ​ቤ​ጥም የማ​ር​ያ​ምን ሰላ​ምታ በሰ​ማች ጊዜ ፅንሱ በማ​ኅ​ፀ​ንዋ ዘለለ፤ በኤ​ል​ሣ​ቤ​ጥም መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባት። 42በታ​ላቅ ቃልም ጮሃ እን​ዲህ አለች፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተሽ አንቺ የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ፤ የማ​ኅ​ፀ​ን​ሽም ፍሬ ቡሩክ ነው። 43የጌ​ታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምን​ድን ነኝ? 44እነሆ፥ ሰላ​ምታ ስት​ሰ​ጭኝ ቃል​ሽን በሰ​ማሁ ጊዜ፥ ፅንሱ በማ​ኅ​ፀኔ በደ​ስታ ዘሎ​አ​ልና። 45ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የነ​ገ​ሩሽ ቃል እን​ደ​ሚ​ሆን የም​ታ​ምኚ አንቺ ብፅ​ዕት ነሽ።”#በግ​ሪኩ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ነ​ገ​ረ​ላት ይፈ​ጸ​ማ​ልና የም​ታ​ምን ብፅ​ዕት ናት” ይላል።
46 # 1ሳሙ. 2፥1-10። ማር​ያ​ምም እን​ዲህ አለች፥ “ሰው​ነቴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታከ​ብ​ረ​ዋ​ለች። 47ልቡ​ና​ዬም በአ​ም​ላኬ በመ​ድ​ኀ​ኒቴ ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች። 48#1ሳሙ. 1፥11። የባ​ር​ያ​ውን ትሕ​ትና ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና። እነሆ፥ ከዛሬ ጀምሮ ትው​ልድ ሁሉ ብፅ​ዕት ይሉ​ኛል። 49ታላቅ ሥራን ሠር​ቶ​ል​ኛ​ልና፤#በግ​ሪኩ “ብርቱ የሆነ እርሱ ለእኔ ታላቅ ሥራ አድ​ር​ጎ​አ​ልና” ይላል። ስሙም ቅዱስ ነው። 50ይቅ​ር​ታ​ውም ለሚ​ፈ​ሩት ለልጅ ልጅ ነው። 51በክ​ንዱ ኀይ​ልን አደ​ረገ፤ በል​ባ​ቸው ዐሳብ የሚ​ታ​በ​ዩ​ት​ንም በተ​ና​ቸው። 52#ኢዮብ 5፥11፤ 12፥19። ኀያ​ላ​ኑን ከዙ​ፋ​ና​ቸው አዋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ትሑ​ታ​ኑ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ረ​ጋ​ቸው። 53የተ​ራ​ቡ​ትን ከበ​ረ​ከቱ አጠ​ገ​ባ​ቸው፤ ባለ​ጠ​ጎ​ች​ንም ባዶ እጃ​ቸ​ውን ሰደ​ዳ​ቸው። 54ብላ​ቴ​ና​ውን እስ​ራ​ኤ​ልን ተቀ​በ​ለው፤ ይቅ​ር​ታ​ው​ንም ዐሰበ። 55#ዘፍ. 17፥7። ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለዘሩ እስከ ዘለ​ዓ​ለም እንደ ተና​ገ​ረው።”
56ማር​ያ​ምም ሦስት ወር ያህል በእ​ር​ስዋ ዘንድ ተቀ​መ​ጠች፤ ከዚህ በኋ​ላም ወደ ቤቷ ተመ​ለ​ሰች።
ስለ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ልደት
57የኤ​ል​ሣ​ቤ​ጥም የመ​ው​ለ​ጃዋ ጊዜ ደረሰ፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች። 58ዘመ​ዶ​ች​ዋና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ዋም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ቱን እን​ዳ​በ​ዛ​ላት በሰሙ ጊዜ ከእ​ር​ስዋ ጋር ደስ አላ​ቸው። 59#ዘሌ. 12፥3። ከዚ​ህም በኋላ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ሕፃ​ኑን ሊገ​ዝ​ሩት መጡ፤ በአ​ባ​ቱም ስም ዘካ​ር​ያስ ብለው ጠሩት። 60እናቱ ግን መልሳ፥ “አይ​ሆ​ንም፥ ዮሐ​ንስ ይባል እንጂ” አለች። 61እነ​ር​ሱም፥ “ከዘ​መ​ዶ​ችሽ ስሙ እን​ደ​ዚህ የሚ​ባል የለም” አሉ​አት። 62አባ​ቱ​ንም ጠቅ​ሰው፥ “ማን ሊሉት ትወ​ዳ​ለህ?” አሉት። 63ብራ​ናም ለመ​ነና “ስሙ ዮሐ​ንስ ይባል” ብሎ ጻፈ፤ ሁሉም አደ​ነቁ። 64ያን​ጊ​ዜም አፉ ተከ​ፈተ፤ አን​ደ​በ​ቱም ተና​ገረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገነ። 65በዚ​ያም ሀገር ሰው ሁሉ ላይ ፍር​ሀት ሆነ፤ ይህም ነገር ሁሉ በይ​ሁዳ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሁሉ ተወራ። 66የሰ​ሙ​ትም ሁሉ፥ “እን​ግ​ዲህ ይህ ሕፃን ምን ይሆን?” እያሉ በል​ባ​ቸው አኖ​ሩት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና።
67በአ​ባቱ በዘ​ካ​ር​ያ​ስም መን​ፈስ ቅዱስ መላ​በት፤ እን​ዲ​ህም ብሎ ትን​ቢት ተና​ገረ፦ 68“ይቅር ያለን፥ ለወ​ገ​ኖ​ቹም ድኅ​ነ​ትን ያደ​ረገ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ 69ከባ​ር​ያው ከዳ​ዊት ቤት የም​ን​ድ​ን​በ​ትን ቀንድ አስ​ነ​ሣ​ልን፤ 70ከጥ​ንት ጀምሮ በነ​በሩ በቅ​ዱ​ሳን በነ​ቢ​ያት አፍ እንደ ተና​ገረ። 71ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ፥ ከሚ​ጠ​ሉ​ንም ሁሉ እጅ ያድ​ነን ዘንድ። 72ቸር​ነ​ቱን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ያደ​ርግ ዘንድ፥ ቅዱስ ኪዳ​ኑ​ንም ያስብ ዘንድ። 73ለአ​ባ​ታ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ለ​ውን መሐላ ያስብ ዘንድ። 74ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ድነን ያለ ፍር​ሀት፥ 75በቅ​ድ​ስ​ናና በጽ​ድቅ በፊቱ በዘ​መ​ና​ችን ሁሉ እን​ድ​ና​መ​ል​ከው ይሰ​ጠን ዘንድ። 76#ሚል. 3፥1። አን​ተም ሕፃን፥ የል​ዑል ነቢይ ትባ​ላ​ለህ፤ መን​ገ​ዱን ትጠ​ርግ ዘንድ በፊቱ ትሄ​ዳ​ለ​ህና። 77ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ዘንድ መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ውቁ ለአ​ሕ​ዛብ ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ። 78ከአ​ር​ያም በጐ​በ​ኘን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በይ​ቅ​ር​ታ​ውና በቸ​ር​ነቱ። 79በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ለነ​በ​ሩት ብር​ሃ​ኑን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ፥ እግ​ሮ​ቻ​ች​ን​ንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ።” 80ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ጸና፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እስ​ከ​ታ​የ​በት ቀን ድረስ በም​ድረ በዳ ኖረ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ