ሉቃስ 1:1-14

ሉቃስ 1:1-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በእኛ ዘንድ የተ​ፈ​ጸ​መ​ው​ንና የታ​መ​ነ​ውን የሥ​ራ​ውን ዜና በሥ​ር​ዐት ሊጽፉ የጀ​መሩ ብዙ​ዎች ናቸው። ከእኛ አስ​ቀ​ድሞ በዐ​ይን ያዩ​ትና የቃሉ አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በሩ እንደ አስ​ተ​ላ​ለ​ፉ​ልን፤ የከ​በ​ርህ ቴዎ​ፍ​ሎስ ሆይ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ተከ​ትዬ፥ ሁሉ​ንም በየ​ተ​ራው እው​ነ​ተ​ኛ​ውን እጽ​ፍ​ልህ ዘንድ መል​ካም ሁኖ ታየኝ። የተ​ማ​ር​ኸ​ውን የነ​ገ​ሩን እው​ነት ጠን​ቅ​ቀህ ታውቅ ዘንድ። በይ​ሁዳ ንጉሥ በሄ​ሮ​ድስ ዘመን ከአ​ብያ ክፍል የሆነ ዘካ​ር​ያስ የሚ​ባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስ​ቱም ከአ​ሮን ልጆች ወገን ነበ​ረች፤ ስም​ዋም ኤል​ሳ​ቤጥ ነበረ። ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ። ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር። እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በተ​ራው የክ​ህ​ነ​ትን ሥራ በሚ​ሠ​ራ​በት ጊዜ፥ ካህ​ናት እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት የሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጊዜ ደረሰ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደ​ስም ገባ። ዕጣን በሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጊዜም ሕዝቡ በሙሉ በውጭ ይጸ​ልዩ ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በዕ​ጣን መሠ​ው​ያው በስ​ተ​ቀኝ ቆሞ ታየው። ዘካ​ር​ያ​ስም ባየው ጊዜ ደነ​ገጠ፤ ፍር​ሀ​ትም ረዓ​ድም ወረ​ደ​በት። መል​አ​ኩም እን​ዲህ አለው፥ “ዘካ​ር​ያስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ ጸሎ​ትህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፤ ሚስ​ትህ ኤል​ሣ​ቤ​ጥም ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ዮሐ​ንስ ትለ​ዋ​ለህ። ደስ​ታና ሐሤ​ትም ይሆ​ን​ል​ሃል፤ በመ​ወ​ለ​ዱም ብዙ​ዎች ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

ሉቃስ 1:1-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በእኛ መካከል ስለ ተፈጸሙት ነገሮች ብዙዎች ታሪኩን የተቻላቸውን ያህል ጽፈውት ይገኛል፤ ይህም ታሪክ ከመጀመሪያው አንሥቶ የዐይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የነበሩት ያስተላለፉልን ነው። ክቡር ቴዎፍሎስ ሆይ፤ እኔም በበኩሌ ሁሉን ከመሠረቱ በጥንቃቄ ከመረመርሁ በኋላ፣ ታሪኩን ቅደም ተከተሉን በጠበቀ ሁኔታ ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ፤ ይህንም የማደርገው የተማርኸው ነገር እውነተኛ መሆኑን እንድታውቅ ነው። በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን፣ ከአብያ የክህነት ምድብ የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ነገድ ስትሆን፣ ስሟም ኤልሳቤጥ ነበረ። ሁለቱም የጌታን ትእዛዝና ሥርዐት ሁሉ ጠብቀው ያለ ነቀፋ የሚኖሩ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መካን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜ የገፉ ነበሩ። አንድ ቀን ዘካርያስ በምድቡ ተራ፣ በእግዚአብሔር ፊት በክህነት በሚያገለግልበት ጊዜ፣ በሥርዐተ ክህነቱ መሠረት፣ ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን በዕጣ ተመረጠ። ዕጣን በሚታጠንበትም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ሆኖ ይጸልይ ነበር። የጌታም መልአክ ከዕጣን መሠዊያው በስተቀኝ ቆሞ ታየው። ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሀትም ተዋጠ። መልአኩ ግን እንዲህ አለው፤ “ዘካርያስ ሆይ፤ አትፍራ፤ ጸሎትህ ተሰምቷል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። በርሱ ተድላና ደስታ ታገኛለህ፤ ብዙዎችም እርሱ በመወለዱ ደስ ይላቸዋል፤

ሉቃስ 1:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ። በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ። ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ። ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር። እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል፥ እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት። በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር። የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው። ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት። መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።

ሉቃስ 1:1-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የተከበርክ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ በእኛ መካከል የተፈጸሙትን ነገሮች የሚገልጥ ታሪክ ከዚህ ቀደም ብዙዎች ጽፈዋል። ይህን መልእክት ለእኛ ያስተላለፉልን ከመጀመሪያው አንሥቶ የዐይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የነበሩት ናቸው። እንዲሁም እኔ ከመጀመሪያው አንሥቼ ሁሉን ነገር በጥንቃቄ ከመረመርኩ በኋላ ታሪኩን በቅደም ተከተል እጽፍልህ ዘንድ መልካም ሆኖ አገኘሁት። ይህንንም ማድረጌ የተማርከውን ትምህርት እውነተኛነት በደምብ እንድትረዳ ብዬ ነው። ሄሮድስ በይሁዳ ምድር ንጉሥ በነበረበት ዘመን፥ ከአብያ የክህነት አገልግሎት ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበር። እርሱም ከአሮን ዘር የምትወለድ ኤልሳቤጥ የምትባል ሚስት ነበረችው። ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ የጌታንም ትእዛዝና ሥርዓት ያለ ነቀፋ ይጠብቁ ነበር። ኤልሳቤጥ መኻን ስለ ነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ ደግሞ ሁለቱም በጣም አርጅተው ነበር። በዚያን ጊዜ የዘካርያስ የክህነት ቡድን ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ተረኛ ነበር፤ ስለዚህ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት የክህነቱን አገልግሎት በመፈጸም ላይ ነበር። እንደ ካህናት አሠራር ልማድ ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን ለማጠን ዕጣ ደረሰው። በቤተ መቅደሱም ውስጥ ዕጣን በሚታጠንበት ጊዜ፥ ሕዝቡ ሁሉ በውጪ ቆመው ይጸልዩ ነበር። የጌታ መልአክ ዕጣን በሚጤስበት መሠዊያ በስተቀኝ በኩል ቆሞ ለዘካርያስ ታየው። ዘካርያስ መልአኩን ባየው ጊዜ ደንግጦ በፍርሃት ተዋጠ። መልአኩ ግን እንዲህ አለው፦ “ዘካርያስ ሆይ! አትፍራ! ጸሎትህ ተሰምቶልሃል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ብለህ ትጠራዋለህ። የእርሱ መወለድ ለአንተ ተድላና ደስታ ይሆንልሃል፤ ብዙዎችም በመወለዱ እንዲሁ ደስ ይላቸዋል።

ሉቃስ 1:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እጅግ የተከበርክ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ብዙዎች በእኛ መካከል ስለ ተፈጸሙት ክስተቶች በጽሑፍ ለማዘጋጀት እንደሞከሩት ሁሉ፥ ከመጀመሪያው አንሥቶ የዐይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት ለእኛ ባስተላለፉልን መሠረት፥ ከመጀመሪያው አንሥቶ ስለሆኑት ነገሮች ሁሉ በጥንቃቄ በመመርመር፥ ለአንተ ቅደም ተከተሉን የጠበቀ ታሪክ ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ። በዚህም ስለ ተማርካቸው ነገሮች እርግጠኛነት በደንብ እንድታውቅ ብዬ ነው። በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ሴት ልጆች ወገን ነበረች፤ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ። ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ በጌታ ትእዛዛትና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ ይመላለሱ ነበር። ኤልሳቤጥም መካን ስለ ነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር። እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት በክህነት ሲያገለግል፥ እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰው። በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር። የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው። ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሃትም ተዋጠ። መልአኩ ግን እንዲህ አለው፦ “ዘካርያስ ሆይ! ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ብለህ ትጠራዋለህ። ደስታና ሐሤትም ይሆንልሃል፤ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።