ሰቈቃወ 3:17-26
ሰቈቃወ 3:17-26 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነፍሴ ሰላምን ዐጣች፤ ደስታ ምን እንደ ሆነ ረሳሁ። ስለዚህ፣ “ክብሬ፣ ከእግዚአብሔርም ተስፋ ያደረግሁት ሁሉ ሄዷል” አልሁ። የጭንቀቴንና የመንከራተቴን፣ ምሬትንና ሐሞትን ዐስባለሁ። ዘወትር አስበዋለሁ፤ ነፍሴም በውስጤ ተዋርዳለች። ሆኖም ይህን ዐስባለሁ፤ እንግዲያስ ተስፋ አለኝ፤ ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህም ብዙ ነው። ራሴን እንዲህ አልሁት፤ “እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ።” እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው። ሰው የእግዚአብሔርን ማዳን፣ ዝም ብሎ ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።
ሰቈቃወ 3:17-26 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ነፍሴን ከሰላም አራቅህ፥ በጎ ነገርን ረሳሁ። እኔም፦ ኃይሌ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያለው ተስፋዬ ጠፋ አልሁ። ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ። ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች። ይህችን በልቤ አኖራለሁ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ። ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፥ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፥ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ነፍሴ፦ እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው፥ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች። ጤት። እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው። ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።
ሰቈቃወ 3:17-26 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ሕይወቴ ሰላም እንዲያጣ ተደረገ፤ ደስታም ምን እንደ ሆነ ረሳሁ። ስለዚህ፦ “ክብሬ ተለይቶኛል፤ ከእግዚአብሔር የምጠብቀውም ተስፋ ሁሉ ተቋርጦአል” አልኩ። መከራዬንና ከርታታነቴን ማስታወስ እንደ እሬትና እንደ ሐሞት ሆነብኝ። ስለዚህም ሁኔታ ሁልጊዜ ሳስብ መንፈሴ ይጨነቃል፤ ሆኖም ይህን አንድ ነገር በማስብበት ጊዜ በተስፋ እሞላለሁ። ይኸውም ሳንጠፋ የቀረነው የእግዚአብሔር ምሕረት ከቶ የማያቋርጥና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ ነው። እነርሱ በየማለዳው ይታደሳሉ፤ ስለዚህ የአንተ ታማኝነት ታላቅ ነው። የእኔ አለኝታ እግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ እርሱን ብቻ ተስፋ አደርጋለሁ። እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠባበቁትና እርሱን ለሚፈልጉ መልካም ነው። ሰው የእግዚአብሔርን አዳኝነት ጸጥ ብሎ መጠበቁ መልካም ነው።
ሰቈቃወ 3:17-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነፍሴን ከሰላም አራቀ፤ በጎ ነገርን ረሳሁ። እኔም፦ ኀይሌን፥ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያለውን ተስፋዬን አጣሁ። ዛይ። ስደቴንና ችግሬን፥ እሬትንና ሐሞትን አስብ። ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች። ይህችን በልቤ አኖራለሁ፤ ስለዚህ እታገሣለሁ። ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ነፍሴ፥ “እግዚአብሔር እድል ፋንታዬ ነው፤ ስለዚህ ጠበቅሁት” አለች። ጤት። እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር ነው፤ ለምትሻውና ለምትታገሥ፥ ዝም ብላም የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ለምታደርግ ነፍስ መልካም ነው።
ሰቈቃወ 3:17-26 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ነፍሴን ከሰላም አራቅህ፥ በጎ ነገርን ረሳሁ። እኔም፦ ኃይሌ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያለው ተስፋዬ ጠፋ አልሁ። ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ። ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች። ይህችን በልቤ አኖራለሁ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ። ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፥ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፥ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ነፍሴ፦ እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው፥ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች። ጤት። ጌታ በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው። ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።