ዮሐንስ 8:3-11

ዮሐንስ 8:3-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም በዝ​ሙት የተ​ያ​ዘች ሴት ወደ እርሱ አም​ጥ​ተው በመ​ካ​ከል አቆ​ሙ​አት። እን​ዲ​ህም አሉት፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይቺን ሴት ስታ​መ​ነ​ዝር አግ​ኝ​ተን ያዝ​ናት። እን​ደ​ዚ​ችም ያለ​ችው በድ​ን​ጋይ እን​ድ​ት​ደ​በ​ደብ ሙሴ በኦ​ሪት አዘ​ዘን፤ እን​ግ​ዲህ አንተ ስለ እር​ስዋ ምን ትላ​ለህ?” በእ​ር​ሱም ላይ ምክ​ን​ያት ሊያ​ገኙ ሲፈ​ት​ኑት ይህን አሉ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጐን​በስ ብሎ በጣቱ በም​ድር ላይ ጻፈ። ብዙ ጊዜ መላ​ል​ሰው በጠ​የ​ቁት ጊዜም ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ፥ “ከእ​ና​ንተ ኀጢ​ኣት የሌ​ለ​በት አስ​ቀ​ድሞ ድን​ጋይ ይጣ​ል​ባት” አላ​ቸው። ዳግ​መ​ኛም ጐን​በስ ብሎ በጣቱ በም​ድር ላይ ጻፈ። እነ​ርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊ​ና​ቸው ወቅ​ሶ​አ​ቸው ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጀምሮ እስከ ኋለ​ኞቹ ድረስ፥ አን​ዳ​ንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ብቻ​ውን ቀረ፤ ሴት​ዮ​ዪ​ቱም በመ​ካ​ከል ቆማ ነበር። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ቀና ብሎ ወደ እር​ስዋ ተመ​ለ​ከ​ተና እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት፥ የሚ​ከ​ሱሽ ወዴት አሉ?” እር​ስ​ዋም፥ “ጌታ ሆይ፥ የማ​የው የለም” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔም አል​ፈ​ር​ድ​ብ​ሽም፤ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ዳግ​መኛ ኀጢ​ኣት አት​ሥሪ” አላት።

ዮሐንስ 8:3-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን በምንዝር የተያዘች ሴት አመጡ፤ በሕዝቡም ፊት አቁመዋት፣ ኢየሱስን እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፣ ይህች ሴት ስታመነዝር ተያዘች፤ ሙሴም፣ እንደዚች ያሉ ሴቶች በድንጋይ እንዲወገሩ በሕጉ አዝዞናል፤ አንተስ ምን ትላለህ?” ይህን ጥያቄ ያቀረቡለት፣ እርሱን የሚከስሱበት ምክንያት ለማግኘት ሲፈትኑት ነው። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ይጽፍ ጀመር። በጥያቄ ሲወተውቱት ቀና ብሎ፣ “ከእናንተ ኀጢአት የሌለበት እርሱ አስቀድሞ ድንጋይ ይወርውርባት” አላቸው። እንደ ገናም ጐንበስ ብሎ በምድር ላይ ጻፈ። ይህን እንደ ሰሙ፣ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ በአንድ ወጡ፤ ሴትዮዋም እዚያው ፊቱ እንደ ቆመች ኢየሱስ ብቻውን ቀረ። ኢየሱስም ቀና ብሎ፣ “አንቺ ሴት፣ ሰዎቹ የት ሄዱ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት። እርሷም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንድም የለም” አለች። ኢየሱስም፣ “እኔም አልፈርድብሽም፤ በይ ሂጂ፤ ከእንግዲህ ግን ኀጢአት አትሥሪ” አላት።]

ዮሐንስ 8:3-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፦ “መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ?” አሉት። የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፦ “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት” አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸዋና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፦ “አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት። እርስዋም፦ “ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ” አለች። ኢየሱስም፦ “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ” አላት።

ዮሐንስ 8:3-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ስታመነዝር የተያዘች ሴት አመጡና በሕዝቡ መካከል አቆሙአት። ኢየሱስንም እንዲህ አሉት፦ “መምህር ሆይ፥ እነሆ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተይዛለች፤ እንዲህ ዐይነትዋ ሴት በድንጋይ ተወግራ እንድትሞት ሙሴ በሕጋችን አዞናል፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ?” ይህንንም ያሉት በእርሱ ላይ የክስ ምክንያት እንዲያገኙ ሊፈትኑት ፈልገው ነበር፤ ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በመሬት ላይ ይጽፍ ጀመር። ደጋግመው በጠየቁት ጊዜ ቀና አለና፥ “ከእናንተ መካከል ኃጢአት የሌለበት የመጀመሪያውን ድንጋይ በእርስዋ ላይ ይጣል!” አላቸው። ከዚህም በኋላ እንደገና ጐንበስ ብሎ በመሬት ላይ ጻፈ። እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ ከሽማግሌዎች ጀምሮ ሁሉም አንድ በአንድ ከዚያ ሄዱ፤ ስለዚህ ኢየሱስ በመካከል ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ብቻውን ቀረ። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ቀና ብሎ፥ “አንቺ ሴት ከሳሾችሽ የት አሉ? የፈረደብሽ ማንም የለምን?” አላት። እርስዋም “ጌታ ሆይ! ማንም የለም” አለች። ኢየሱስም “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ፤ ዳግመኛ ኃጢአት አትሥሪ” አላት።

ዮሐንስ 8:3-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ፤ በመካከልም እርሱዋን አቁመው እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ! ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርሷ ምን ትላለህ?” የሚከሱበትን ምክንያት እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህንን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት የመጀመሪያውን ድንጋይ ይወርውርባት፤” አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። እነርሱም ይህን ሲሰሙ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። ኢየሱስም ቀና ብሎ “አንቺ ሴት! ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት። እርሷም “ጌታ ሆይ! አንድም እንኳን፤” አለች። ኢየሱስም “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ፤ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ፤” አላት።