የዮሐንስ ወንጌል 8:3-11

የዮሐንስ ወንጌል 8:3-11 መቅካእኤ

ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ፤ በመካከልም እርሱዋን አቁመው እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ! ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርሷ ምን ትላለህ?” የሚከሱበትን ምክንያት እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህንን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት የመጀመሪያውን ድንጋይ ይወርውርባት፤” አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። እነርሱም ይህን ሲሰሙ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። ኢየሱስም ቀና ብሎ “አንቺ ሴት! ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት። እርሷም “ጌታ ሆይ! አንድም እንኳን፤” አለች። ኢየሱስም “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ፤ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ፤” አላት።