ዮሐንስ 6:18-21
ዮሐንስ 6:18-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ባሕሩ ግን ይታወክ ነበር፤ ጽኑ ነፋስ ይነፍስ ነበርና። ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ያህል ከሄዱ በኋላ ጌታችን ኢየሱስን በባሕር ላይ ሲሄድ አዩት፤ ወደ ታንኳዉ በቀረበ ጊዜም ፈሩ። እርሱም፥ “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው። ወደ ታንኳውዪቱ ሊያወጡት ሲሹም ታንኳዪቱ ወዲያውኑ ሊሄዱ ወደ ወደዱበት ወደብ ደረሰች።
Share
ዮሐንስ 6 ያንብቡዮሐንስ 6:18-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኀይለኛ ነፋስ ይነፍስ ስለ ነበር ባሕሩ ተናወጠ። አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያህል እንደ ቀዘፉ፣ ኢየሱስ በውሃ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲመጣ አይተው ደነገጡ። እርሱ ግን፣ “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው። እነርሱም እንዲሳፈር ፈለጉ፤ ጀልባዋም ወዲያውኑ ወደሚሄዱበት ዳርቻ ደረሰች።
Share
ዮሐንስ 6 ያንብቡዮሐንስ 6:18-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ብርቱ ነፋስም ስለ ነፈሰ ባሕሩ ተናወጠ። ሀያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ከቀዘፉ በኋላም፥ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ ታንኳይቱ ሲቀርብ አይተው ፈሩ። እርሱ ግን፦ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ አላቸው። ስለዚህ በታንኳይቱ ሊቀበሉት ወደዱ፤ ወዲያውም ታንኳይቱ ወደሚሄዱበት ምድር ደረሰች።
Share
ዮሐንስ 6 ያንብቡ