የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮሐንስ ወንጌል 6:18-21

የዮሐንስ ወንጌል 6:18-21 አማ05

ኀይለኛ ነፋስ ይነፍስ ስለ ነበር፤ ባሕሩ ተናወጠ። ደቀ መዛሙርቱ አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያኽል እየቀዘፉ ከተጓዙ በኋላ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲቀርብ አይተው ፈሩ። እርሱ ግን “እኔ ነኝ! አትፍሩ!” አላቸው። እነርሱም በደስታ ተቀብለው ወደ ጀልባዋ ሊያስገቡት ፈለጉ፤ ወዲያውኑ ጀልባዋ ወደሚሄዱበት ቦታ ደረሰች።