ዮሐንስ 6:1-6
ዮሐንስ 6:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከዚህ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ወደ ጥብርያዶስ ሄደ። በበሽተኞችም ላይ ያደረገውን ተአምራት ስለ አዩ ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤ ጌታችን ኢየሱስም ወደ ተራራ ወጣ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር በዚያ ተቀመጠ። የአይሁድ የፋሲካ በዓልም ቀርቦ ነበር። ጌታችን ኢየሱስም ዐይኖቹን አንሥቶ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ሲመጡ አየና ፊልጶስን፥ “ለእነዚህ ሰዎች የምናበላቸው እንጀራ ከወዴት እንግዛ?” አለው። ሲፈትነው ይህን አለ እንጂ፥ እርሱስ የሚያደርገውን ያውቅ ነበር።
ዮሐንስ 6:1-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ጥብርያዶስ የተባለውን የገሊላ ባሕር ተሻግሮ ራቅ ወዳለው የባሕሩ ዳርቻ ሄደ። ብዙ ሰዎችም በሽተኞችን በመፈወስ ያደረጋቸውን ታምራዊ ምልክቶች ስላዩ ተከተሉት። ከዚያም ኢየሱስ ወደ ተራራ ወጥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ተቀመጠ። የአይሁድ የፋሲካ በዓልም ተቃርቦ ነበር። ኢየሱስም ቀና ብሎ ሲመለከት፣ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ አየ፤ ፊልጶስንም፣ “እነዚህ ሰዎች እንዲበሉ እንጀራ ከየት እንግዛ?” አለው። ይህን የጠየቀው ሊፈትነው እንጂ ራሱ ሊያደርግ ያሰበውን ያውቅ ነበር።
ዮሐንስ 6:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ፤ እርሱም የጥብርያዶስ ባሕር ነው። በበሽተኞችም ያደረገውን ምልክቶች ስላዩ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። ኢየሱስም ወደ ተራራ ወጣና በዚያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ። የአይሁድ በዓልም ፋሲካ ቀርቦ ነበር። ኢየሱስም ዓይኖቹን አንሥቶ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ አየና ፊልጶስን፦ እነዚህ እንዲበሉ እንጀራ ከወዴት እንገዛለን? አለው። ራሱ ሊያደርግ ያለውን ያውቅ ነበርና ሊፈትነው ይህን ተናገረ።
ዮሐንስ 6:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ጥብርያዶስ ወደሚባለው ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ። ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በሽተኞችን በመፈወስ ያደረገውን ተአምር ስላዩ ተከተሉት። ኢየሱስ ወደ ተራራ ወጣና በዚያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ። የአይሁድ ፋሲካ በዓል ቀርቦ ነበር። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ ቀና ብሎ አየና ፊልጶስን፦ “ለዚህ ሁሉ ሰው የሚበቃ ምግብ ከየት መግዛት እንችላለን?” አለው። ኢየሱስ ይህን የተናገረው ፊልጶስን ለመፈተን ነበር እንጂ፥ የሚያደርገውንስ እርሱ ራሱ ያውቅ ነበር።
ዮሐንስ 6:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ፤ እርሱም የጥብርያዶስ ባሕር ነው። በበሽተኞችም ያደረገውን ምልክቶች ስላዩ ብዙ ሕዝብ ተከተለው። ኢየሱስም ወደ ተራራ ወጣና በዚያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ። የአይሁድ በዓል ፋሲካም ቀርቦ ነበር። ኢየሱስም ዐይኖቹን አንሥቶ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ አየና ፊልጶስን “እነዚህ እንዲበሉ እንጀራ ከወዴት እንገዛለን?” አለው። ሊፈትነው ይህን ተናገረ፤ እራሱ ሊያደርግ ያለውን ያውቅ ነበርና።