የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 6:1-6

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 6:1-6 አማ2000

ከዚህ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ወደ ጥብ​ር​ያ​ዶስ ሄደ። በበ​ሽ​ተ​ኞ​ችም ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት ስለ አዩ ብዙ ሰዎች ተከ​ተ​ሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ተራራ ወጣ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጋር በዚያ ተቀ​መጠ። የአ​ይ​ሁድ የፋ​ሲካ በዓ​ልም ቀርቦ ነበር። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ሲመጡ አየና ፊል​ጶ​ስን፥ “ለእ​ነ​ዚህ ሰዎች የም​ና​በ​ላ​ቸው እን​ጀራ ከወ​ዴት እን​ግዛ?” አለው። ሲፈ​ት​ነው ይህን አለ እንጂ፥ እር​ሱስ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ያውቅ ነበር።