የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዮሐንስ 4:7-28

ዮሐንስ 4:7-28 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እነሆ፥ ከሰ​ማ​ርያ አን​ዲት ሴት ውኃ ልት​ቀዳ መጣች፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ውኃ አጠ​ጪኝ” አላት። ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበ​ርና። ያቺ የሰ​ማ​ርያ ሴትም፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን፥ እኔም ሳም​ራ​ዊት ስሆን እን​ዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልት​ጠጣ ትለ​ም​ና​ለህ?” አለ​ችው፤ አይ​ሁድ ከሳ​ም​ራ​ው​ያን ጋር በሥ​ር​ዐት አይ​ተ​ባ​በ​ሩም ነበ​ርና። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦ​ታና ውኃ አጠ​ጪኝ ብሎ የሚ​ለ​ም​ንሽ ማን እንደ ሆነ ብታ​ው​ቂስ አንቺ ደግሞ በለ​መ​ን​ሺው ነበር፤ እር​ሱም የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ በሰ​ጠሽ ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላት። ያቺ ሴትም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ መቅጃ እንኳ የለ​ህም፤ ጕድ​ጓ​ዱም ጥልቅ ነው፤ እን​ግ​ዲህ የሕ​ይ​ወት ውኃ ከወ​ዴት ታገ​ኛ​ለህ? ይህን ጕድ​ጓድ ከሰ​ጠን ከአ​ባ​ታ​ችን ከያ​ዕ​ቆብ አንተ ትበ​ል​ጣ​ለ​ህን? እር​ሱም ልጆ​ቹም፥ ከብ​ቶ​ቹም ከእ​ርሱ ጠጥ​ተ​ዋል።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ከዚህ ውኃ የሚ​ጠጣ ሁሉ ዳግ​መኛ ይጠ​ማል። እኔ ከም​ሰ​ጠው ውኃ የሚ​ጠጣ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም፤ እኔ የም​ሰ​ጠው ውኃ በው​ስጡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የሚ​ፈ​ልቅ የውኃ ምንጭ ይሆ​ን​ለ​ታል እንጂ።” ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እን​ዳ​ል​ጠማ፥ ዳግ​መ​ኛም ውኃ ልቀዳ ወደ​ዚህ እን​ዳ​ል​መጣ እባ​ክህ ከዚህ ውኃ ስጠኝ፤” አለ​ችው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሂደሽ ባል​ሽን ጥሪና ወደ​ዚህ ነይ” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “ባል የለ​ኝም” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “ባል የለ​ኝም በማ​ለ​ትሽ መል​ካም ተና​ገ​ርሽ። ቀድሞ አም​ስት ባሎች ነበ​ሩሽ፤ ዛሬ አብ​ሮሽ ያለው ግን ባልሽ አይ​ደ​ለም፤ ይህ​ንስ እው​ነት አልሽ።” ሴቲ​ቱም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያ​ለሁ። አባ​ቶ​ቻ​ችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እና​ንተ ግን ይሰ​ግ​ዱ​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባው ስፍራ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነው ትላ​ላ​ችሁ።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት በዚህ ተራራ ወይም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ብቻ ለአብ የማ​ይ​ሰ​ግ​ዱ​በት ሰዓት እን​ደ​ም​ት​መጣ እመ​ኝኝ። እና​ንተ ለማ​ታ​ው​ቁት ትሰ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እኛ ግን ለም​ና​ው​ቀው እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን፤ መድ​ኀ​ኒት ከአ​ይ​ሁድ ወገን ነውና። ነገር ግን በእ​ው​ነት የሚ​ሰ​ግዱ በመ​ን​ፈ​ስና በእ​ው​ነት ለአብ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ባት ጊዜ ትመ​ጣ​ለች፤ እር​ስ​ዋም አሁን ናት። አብ እን​ዲህ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ለ​ትን ይሻ​ልና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነውና፤ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ለ​ትም በመ​ን​ፈ​ስና በእ​ው​ነት ይሰ​ግ​ዱ​ለት ዘንድ ይገ​ባል።” ሴቲ​ቱም፥ “ክር​ስ​ቶስ የሚ​ሉት መሲሕ እን​ደ​ሚ​መጣ እና​ው​ቃ​ለን፤ እር​ሱም በሚ​መጣ ጊዜ ሁሉን ይነ​ግ​ረ​ናል” አለ​ችው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የማ​ነ​ጋ​ግ​ርሽ እኔ እርሱ ነኝ” አላት። በዚ​ያም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ መጡ፤ ከሴት ጋርም ይነ​ጋ​ገር ነበ​ርና ተደ​ነቁ፤ ነገር ግን፥ “ምን ትሻ​ለህ? ወይስ ከእ​ር​ስዋ ጋር ለምን ትነ​ጋ​ገ​ራ​ለህ?” ያለው የለም። ሴቲ​ቱም እን​ስ​ራ​ዋን ትታ ወደ ከተማ ገባች፤ ለሰ​ዎ​ችም ነገ​ረች።

ዮሐንስ 4:7-28 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አንዲት ሳምራዊት ሴት ውሃ ለመቅዳት ስትመጣ ኢየሱስ፣ “እባክሽ የምጠጣው ስጪኝ” አላት፤ ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ለመግዛት ወደ ከተማ ሄደው ነበር። ሳምራዊቷም፣ “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ፣ እኔን ሳምራዊቷን እንዴት ውሃ አጠጪኝ ትላለህ?” አለችው፤ ይህን ማለቷ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር ስለማይተባበሩ ነው። ኢየሱስም፣ “የእግዚአብሔርን ስጦታ ብታውቂና ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑን ብትረጂ ኖሮ፣ አንቺው በጠየቅሽው፣ እርሱም የሕይወትን ውሃ በሰጠሽ ነበር” ሲል መለሰላት። ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ፣ መቅጃ የለህም፤ ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ ታዲያ ይህን የሕይወት ውሃ ከየት ታገኛለህ? ለመሆኑ አንተ፣ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን፣ ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? እርሱ ራሱና ልጆቹ፣ እንስሳቱም ከዚሁ ጕድጓድ ጠጥተዋል።” ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላት፤ “ከዚህ ውሃ የሚጠጣ እንደ ገና ይጠማል፤ እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ግን ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል።” ሴትዮዋም፣ “ጌታዬ፤ እንዳልጠማና ውሃ ለመቅዳት እንዳልመላለስ፣ እባክህ ይህን ውሃ ስጠኝ” አለችው። እርሱም፣ “ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ተመለሽ” አላት። ሴትዮዋም፣ “ባል የለኝም” ብላ መለሰች። ኢየሱስም፣ እንዲህ አላት፤ “ባል የለኝም ማለትሽ ትክክል ነው፤ በርግጥ አምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁን ከአንቺ ጋር ያለውም ባልሽ ስላልሆነ፣ የተናገርሽው እውነት ነው።” ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ፣ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ፤ አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ ሰገዱ፤ እናንተ አይሁድ ግን ሰው መስገድ ያለበት በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ” አለችው። ኢየሱስም እንዲህ አላት፤ “አንቺ ሴት፤ በዚህ ተራራም ሆነ በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ እንደሚመጣ እመኚኝ። እናንተ ሳምራውያን ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን ድነት ከአይሁድ ስለሆነ ለምናውቀው እንሰግዳለን። በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፤ አሁንም መጥቷል፤ አብም እንደዚህ በእውነት የሚሰግዱለትን ይፈልጋል። እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባል።” ሴትዮዋም፣ “ክርስቶስ የተባለ መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ነገር ይነግረናል” አለችው። ኢየሱስም፣ “የማነጋግርሽ እኮ እኔ እርሱ ነኝ” ሲል ገልጦ ነገራት። በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሰው መጡ፤ ከሴት ጋር ሲነጋገር በማግኘታቸው ተደነቁ፤ ሆኖም ግን፤ “ምን ፈለግህ?” ወይም፣ “ከእርሷ ጋር የምትነጋገረው ለምንድን ነው?” ብሎ የጠየቀው ማንም አልነበረም። ሴትዮዋም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ተመለሰች፤ ለሕዝቡም፣

ዮሐንስ 4:7-28 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከሰማርያ አንዲት ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም፦ ውኃ አጠጪኝ አላት፤ ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበርና። ስለዚህ ሳምራዊቲቱ፦ አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና። ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ወኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት። ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ መቅጃ የለህም ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ? በእውኑ አንተ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? ራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል አለችው። ኢየሱስም መልሶ፦ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት። ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ አለችው። ኢየሱስም፦ ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነዪ አላት። ሴቲቱ መልሳ፦ ባል የለኝም አለችው። ኢየሱስም፦ ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤ አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ አላት። ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ። አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተ፦ ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ አለችው። ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል። እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን። ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። ሴቲቱ፦ ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው። ኢየሱስ፦ የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት። በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን፦ ምን ትፈልጊያለሽ? ወይም፦ ስለ ምን ትናገራታለህ? ያለ ማንም አልነበረም። ሴቲቱም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደች ለሰዎቹም፦

ዮሐንስ 4:7-28 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በዚያን ጊዜ አንዲት የሰማርያ አገር ሴት ውሃ ልትቀዳ ወደ ጒድጓዱ መጣች፤ ኢየሱስም “ውሃ አጠጪኝ!” አላት። በዚያን ወቅት ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበር። ይህችም ሳምራዊት ሴት ኢየሱስን፦ “አንተ ከአይሁድ ወገን ሆነህ እንዴት እኔን ሳምራዊቷን ‘ውሃ አጠጪኝ!’ ብለህ ትጠይቀኛለህ?” አለችው፤ ይህን ማለትዋ፥ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር ስምምነት ስላልነበራቸው ነው። ኢየሱስም “የእግዚአብሔርን ስጦታና ‘ውሃ አጠጪኝ!’ የሚልሽ ማን እንደ ሆነ ብታውቂው ኖሮ፥ እርሱን መለመን የሚገባሽ አንቺ ነበርሽ፤ እርሱም የሕይወትን ውሃ ይሰጥሽ ነበር” አላት። እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰች፤ “ጌታ ሆይ! አንተ መቅጃ የለህም፤ ጒድጓዱም ጥልቅ ነው፤ ታዲያ፥ የሕይወት ውሃ ከየት ታገኛለህ? አንተ ይህን ጒድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? እርሱና ልጆቹ፥ ከብቶቹም ከዚህ ጒድጓድ ጠጥተዋል።” ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላት፤ “ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማዋል፤ እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ለዘለዓለም ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ፥ ለሚጠጣው ሰው ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል።” ሴትዮዋም “ጌታ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ውሃ እንዳይጠማኝና ወደዚህም ለመቅዳት እንዳልመጣ እባክህ እንዲህ ዐይነቱን ውሃ ስጠኝ!” አለችው። ኢየሱስም “ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ተመለሺ” አላት። ሴትዮዋም “ባል የለኝም” ስትል መለሰች፤ በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላት፦ “ባል የለኝም ማለትሽ ልክ ነው፤ አምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁንም ከአንቺ ጋር ያለው ሰው ባልሽ አይደለም፤ ስለዚህ እውነቱን ተናግረሻል።” ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ “ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደ ሆንክ አሁን ዐወቅሁ፤ አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ ሰገዱ፤ እናንተ ግን ‘ሰዎች ሊሰግዱ የሚገባቸው በኢየሩሳሌም ነው’ ትላላችሁ።” ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “አንቺ ሴት፥ በዚህ ተራራ ላይ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ እንደሚመጣ እመኚኝ፤ እናንተ ለማታውቁት አምላክ ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን መዳን የሚመጣው ከአይሁድ ስለ ሆነ ለምናውቀው አምላክ እንሰግዳለን። ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ፥ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፤ እንዲያውም አሁን መጥቶአል፤ አብም የሚፈልገው በዚህ መንገድ የሚሰግዱለትን ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባቸዋል።” ሴትዮዋም “ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ነገር ይነግረናል” አለችው። ኢየሱስም “እነሆ! አሁን የማነጋግርሽ እኔ እርሱ ነኝ” አላት። በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ከሄዱበት ተመልሰው መጡ፤ ኢየሱስ ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተገረሙ፤ ይሁን እንጂ “ምን ትፈልጋለህ? ወይም ከእርስዋ ጋር ለምን ትነጋገራለህ?” ብሎ የጠየቀው ማንም አልነበረም። ከዚህ በኋላ ሴትዮዋ እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደችና ለሰዎቹ እንዲህ አለች፦

ዮሐንስ 4:7-28 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አንዲት የሰማርያ ሴት ውሃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም “ውሃ አጠጪኝ” አላት፤ ደቀመዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበርና። ስለዚህ ሳምራዊቲቱ “አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ?” አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና። ኢየሱስ መልሶ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ‘ወሃ አጠጪኝ’ የሚልሽ ማን መሆኑን ብታውቂ ኖሮ፥ አንቺ በለመንሽው ነበር፤ የሕይወትም ውሃ በሰጠሽ ነበር፤” አላት። ሴቲቱ “ጌታ ሆይ! መቅጃ የለህም፤ ጉድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውሃ ከወዴት ታገኛለህ? በእውኑ አንተ ይህን ጉድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? እራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል፤” አለችው። ኢየሱስም መልሶ “ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል፤ እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፤” አላት። ሴቲቱ “ጌታ ሆይ! እንዳልጠማ ውሃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውሃ ስጠኝ፤” አለችው። ኢየሱስም “ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነዪ፤” አላት። ሴቲቱ መልሳ “ባል የለኝም፤” አለችው። ኢየሱስም “‘ባል የለኝም፤’ በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤ አምስት ባሎች ነበሩሽና፤ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነቱን ተናገርሽ፤” አላት። ሴቲቱ “ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደሆንህ አያለሁ። አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተ ‘ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው፤’ ትላላችሁ፤” አለችው። ኢየሱስም እንዲህ አላት “አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፤ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል። እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ለምናውቀው እንሰግዳለን፥ መዳን ከአይሁድ ነውና። ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፤ ይኸውም አሁን ነው፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባል።” ሴቲቱ “ክርስቶስ የሚባል መሢሕ እንደሚመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል፤” አለችው። ኢየሱስ “የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ፤” አላት። በዚያም ጊዜ ደቀመዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን “ምን ፈለግህ?” ወይም “ስለምን ትናገራታለህ?” ያለ ማንም አልነበረም። ሴቲቱም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደች፤ ለሰዎቹም