የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 4:7-28

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 4:7-28 አማ2000

እነሆ፥ ከሰ​ማ​ርያ አን​ዲት ሴት ውኃ ልት​ቀዳ መጣች፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ውኃ አጠ​ጪኝ” አላት። ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበ​ርና። ያቺ የሰ​ማ​ርያ ሴትም፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን፥ እኔም ሳም​ራ​ዊት ስሆን እን​ዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልት​ጠጣ ትለ​ም​ና​ለህ?” አለ​ችው፤ አይ​ሁድ ከሳ​ም​ራ​ው​ያን ጋር በሥ​ር​ዐት አይ​ተ​ባ​በ​ሩም ነበ​ርና። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦ​ታና ውኃ አጠ​ጪኝ ብሎ የሚ​ለ​ም​ንሽ ማን እንደ ሆነ ብታ​ው​ቂስ አንቺ ደግሞ በለ​መ​ን​ሺው ነበር፤ እር​ሱም የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ በሰ​ጠሽ ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላት። ያቺ ሴትም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ መቅጃ እንኳ የለ​ህም፤ ጕድ​ጓ​ዱም ጥልቅ ነው፤ እን​ግ​ዲህ የሕ​ይ​ወት ውኃ ከወ​ዴት ታገ​ኛ​ለህ? ይህን ጕድ​ጓድ ከሰ​ጠን ከአ​ባ​ታ​ችን ከያ​ዕ​ቆብ አንተ ትበ​ል​ጣ​ለ​ህን? እር​ሱም ልጆ​ቹም፥ ከብ​ቶ​ቹም ከእ​ርሱ ጠጥ​ተ​ዋል።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ከዚህ ውኃ የሚ​ጠጣ ሁሉ ዳግ​መኛ ይጠ​ማል። እኔ ከም​ሰ​ጠው ውኃ የሚ​ጠጣ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም፤ እኔ የም​ሰ​ጠው ውኃ በው​ስጡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የሚ​ፈ​ልቅ የውኃ ምንጭ ይሆ​ን​ለ​ታል እንጂ።” ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እን​ዳ​ል​ጠማ፥ ዳግ​መ​ኛም ውኃ ልቀዳ ወደ​ዚህ እን​ዳ​ል​መጣ እባ​ክህ ከዚህ ውኃ ስጠኝ፤” አለ​ችው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሂደሽ ባል​ሽን ጥሪና ወደ​ዚህ ነይ” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “ባል የለ​ኝም” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “ባል የለ​ኝም በማ​ለ​ትሽ መል​ካም ተና​ገ​ርሽ። ቀድሞ አም​ስት ባሎች ነበ​ሩሽ፤ ዛሬ አብ​ሮሽ ያለው ግን ባልሽ አይ​ደ​ለም፤ ይህ​ንስ እው​ነት አልሽ።” ሴቲ​ቱም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያ​ለሁ። አባ​ቶ​ቻ​ችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እና​ንተ ግን ይሰ​ግ​ዱ​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባው ስፍራ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነው ትላ​ላ​ችሁ።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት በዚህ ተራራ ወይም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ብቻ ለአብ የማ​ይ​ሰ​ግ​ዱ​በት ሰዓት እን​ደ​ም​ት​መጣ እመ​ኝኝ። እና​ንተ ለማ​ታ​ው​ቁት ትሰ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እኛ ግን ለም​ና​ው​ቀው እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን፤ መድ​ኀ​ኒት ከአ​ይ​ሁድ ወገን ነውና። ነገር ግን በእ​ው​ነት የሚ​ሰ​ግዱ በመ​ን​ፈ​ስና በእ​ው​ነት ለአብ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ባት ጊዜ ትመ​ጣ​ለች፤ እር​ስ​ዋም አሁን ናት። አብ እን​ዲህ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ለ​ትን ይሻ​ልና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነውና፤ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ለ​ትም በመ​ን​ፈ​ስና በእ​ው​ነት ይሰ​ግ​ዱ​ለት ዘንድ ይገ​ባል።” ሴቲ​ቱም፥ “ክር​ስ​ቶስ የሚ​ሉት መሲሕ እን​ደ​ሚ​መጣ እና​ው​ቃ​ለን፤ እር​ሱም በሚ​መጣ ጊዜ ሁሉን ይነ​ግ​ረ​ናል” አለ​ችው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የማ​ነ​ጋ​ግ​ርሽ እኔ እርሱ ነኝ” አላት። በዚ​ያም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ መጡ፤ ከሴት ጋርም ይነ​ጋ​ገር ነበ​ርና ተደ​ነቁ፤ ነገር ግን፥ “ምን ትሻ​ለህ? ወይስ ከእ​ር​ስዋ ጋር ለምን ትነ​ጋ​ገ​ራ​ለህ?” ያለው የለም። ሴቲ​ቱም እን​ስ​ራ​ዋን ትታ ወደ ከተማ ገባች፤ ለሰ​ዎ​ችም ነገ​ረች።