የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዮሐንስ 3:1-18

ዮሐንስ 3:1-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን የአ​ይ​ሁድ አለቃ የሆነ ኒቆ​ዲ​ሞስ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ። እር​ሱም በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ ልታ​ስ​ተ​ምር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ መጣህ እና​ው​ቃ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ይህን ተአ​ምር ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ችል የለ​ምና።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ለማ​የት አይ​ች​ልም” አለው። ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም፥ “ሰው ከሸ​መ​ገለ በኋላ ዳግ​መኛ መወ​ለድ እን​ደ​ምን ይች​ላል? ዳግ​መኛ ይወ​ለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅ​ፀን ተመ​ልሶ መግ​ባት ይች​ላ​ልን?” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ከው​ኃና ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ሊገባ አይ​ች​ልም። ከሥጋ የተ​ወ​ለደ ሥጋ ነውና፤ ከመ​ን​ፈ​ስም የተ​ወ​ለደ መን​ፈስ ነውና። ስለ​ዚ​ህም ዳግ​መኛ ልት​ወ​ለዱ ይገ​ባ​ች​ኋል ስለ አል​ሁህ አታ​ድ​ንቅ። ነፋስ ወደ ወደ​ደው ይነ​ፍ​ሳ​ልና፤ ድም​ፁ​ንም ትሰ​ማ​ለህ፤ ነገር ግን ከየት እን​ደ​ሚ​መጣ ወዴ​ትም እን​ደ​ሚ​ሄድ አታ​ው​ቅም፤ ከመ​ን​ፈስ የሚ​ወ​ለድ ሁሉ እን​ዲሁ ነው።” ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም መልሶ፥ “ይህ ሊሆን እን​ዴት ይቻ​ላል?” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መም​ህ​ራ​ቸው ነህ፤ ነገር ግን እን​ዴት ይህን አታ​ው​ቅም?” አለው። እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ የም​ና​ው​ቀ​ውን እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ያየ​ነ​ው​ንም እን​መ​ሰ​ክ​ራ​ለን፤ ነገር ግን ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ንን አት​ቀ​በ​ሉ​ንም። በም​ድር ያለ​ውን ስነ​ግ​ራ​ችሁ ካላ​መ​ና​ች​ሁኝ በሰ​ማይ ያለ​ውን ብነ​ግ​ራ​ችሁ እን​ዴት ታም​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ? ከሰ​ማይ ከወ​ረ​ደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤ እር​ሱም በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው ነው። ሙሴ በም​ድረ በዳ እባ​ቡን እንደ ሰቀ​ለው የሰው ልጅ እን​ዲሁ ይሰ​ቀል ዘንድ አለው። ያመ​ነ​በት ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕያው ሆኖ እን​ዲ​ኖር እንጂ እን​ዳ​ይ​ጠፋ። በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኝ እንጂ እን​ዳ​ይ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ድያ ልጁን ቤዛ አድ​ርጎ እስ​ኪ​ሰጥ ድረስ ዓለ​ሙን እን​ዲህ ወዶ​ታ​ልና። ዓለም በእ​ርሱ ይድን ዘንድ ነው እንጂ በዓ​ለም እን​ዲ​ፈ​ርድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ወደ​ዚህ ዓለም አል​ላ​ከ​ው​ምና። በእ​ርሱ ያመነ አይ​ፈ​ረ​ድ​በ​ትም፤ በእ​ርሱ ያላ​መነ ግን ፈጽሞ ተፈ​ር​ዶ​በ​ታል፤ በአ​ንዱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ስም አላ​መ​ነ​ምና።

ዮሐንስ 3:1-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከፈሪሳውያን ወገን፣ ከአይሁድ አለቆች አንዱ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ ሰው ነበረ፤ በሌሊትም ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ “ረቢ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ ሰው በቀር አንተ የምታደርጋቸውን ታምራዊ ምልክቶች ማንም ሊያደርግ ስለማይችል፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር እንደ ሆንህ እናውቃለን” አለው። ኢየሱስም መልሶ፣ “እውነት እልሃለሁ፤ ማንም ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም” አለው። ኒቆዲሞስም፣ “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ እንዲወለድ ተመልሶ ወደ እናቱ ማሕፀንስ ሊገባ ይችላልን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እውነት እልሃለሁ፤ ማንም ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፤ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደም መንፈስ ነው። ‘ዳግመኛ መወለድ አለባችሁ’ ስላልሁህ አትገረም፤ ነፋስ ወደሚወድደው ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ነገር ግን ከየት እንደ መጣ፣ ወዴት እንደሚሄድም አታውቅም፤ ከመንፈስም የተወለደ ሁሉ እንደዚሁ ነው።” ኒቆዲሞስም፣ “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አንተ የእስራኤል መምህር ሆነህ ሳለ እነዚህን ነገሮች አታውቅምን? እውነት እልሃለሁ፤ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ እናንተ ግን ምስክርነታችንን አትቀበሉም። ስለ ምድራዊው ነገር ነግሬአችሁ ያላመናችሁ፣ ስለ ሰማያዊው ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር፣ ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም። ሙሴ በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ፣ የሰው ልጅም እንዲሁ ሊሰቀል ይገባዋል፤ ይኸውም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና። እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው። በእርሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል።

ዮሐንስ 3:1-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለም መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው። ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ። ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው። ኒቆዲሞስ መልሶ፦ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን? እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም። ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።

ዮሐንስ 3:1-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱ ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ ነበረ። ይህ ሰው በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ “መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ካልሆነ በቀር እነዚህን አንተ የምታደርጋቸውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል ማንም የለም፤ ስለዚህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር እንደ ሆንክ እናውቃለን” አለው። ኢየሱስም “እውነት፥ እውነት እልሃለሁ፤ ሰው እንደገና ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም” አለው። ኒቆዲሞስም “ታዲያ፥ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ ወደ እናቱ ማሕፀን ገብቶ መወለድ ይችላልን?” ሲል ጠየቀ። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እውነት፥ እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው። ስለዚህ ‘ዳግመኛ መወለድ ያስፈልጋችኋል’ ስላልኩህ አትደነቅ። ነፋስ ወደ ፈለገው አቅጣጫ ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ነገር ግን ከየት እንደሚመጣና ወዴትም እንደሚሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።” ኒቆዲሞስም “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አንተ የእስራኤል መምህር ሆነህ ይህን አታውቅምን? እውነት፥ እውነት እልሃለሁ፤ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ እናንተ ግን ምስክርነታችንን አትቀበሉትም። ምድራዊውን ነገር ስነግራችሁ የማታምኑ ከሆነ ሰማያዊውን ነገር ስነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም። “ሙሴ በበረሓ እባብን ከፍ አድርጎ እንደ ሰቀለ እንዲሁም የሰው ልጅ ከፍ ብሎ ሊሰቀል ይገባዋል። ይህም የሚሆነው በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለምን ሕይወት እንዲያገኝ ነው። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር ዓለምን እጅግ ስለ ወደደው አንድያ ልጁን ሰጠ። እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው፥ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም ላይ ለመፍረድ አይደለም። “በእርሱ የሚያምን አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ ቀድሞውኑ ተፈርዶበታል።

ዮሐንስ 3:1-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ከፈሪሳውያንም ወገን አንድ ሰው ነበረ፤ ስሙ ኒቆዲሞስ ሲሆን የአይሁድም አለቃ ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ “መምህር ሆይ! ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር መሆንህን እናውቃለን፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ካልሆነ በስተቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል ማንም የለምና፤” አለው። ኢየሱስም መልሶ “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም፤” አለው። ኒቆዲሞስም “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ መወለድ ይችላልን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። ዳግመኛ መወለድ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አትደነቅ። ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ነገር ግን ከወዴት እንደመጣ ወዴትም እንደሚሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስም የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።” ኒቆዲሞስ መልሶ “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው “አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህንን አታውቅምን? እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ የእኛንም ምስክርነት አትቀበሉትም። ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ከሰማይም ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፤ እርሱም የሰው ልጅ ነው። ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ የሰው ልጅም መሰቀል ይገባዋል። በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት ይኖረው ዘንድ። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። በእርሱ የሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ ከወዲሁ ተፈርዶበታል።