ዮሐንስ 19:25-29
ዮሐንስ 19:25-29 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በጌታችን በኢየሱስ መስቀል አጠገብም እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊት ማርያምም ቆመው ነበር። ጌታችን ኢየሱስም እናቱንና የሚወደውን ደቀ መዝሙሩን ቆመው ባያቸው ጊዜ እናቱን፥ “አንች ሆይ፥ እነሆ፥ ልጅሽ” አላት። ከዚህም በኋላ ደቀ መዝሙሩን፥ “እናትህ እነኋት” አለው፤ ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ተቀብሎ ወደ ቤቱ ወሰዳት። ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ሁሉ እንደ ተፈጸመ ባየ ጊዜ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ “ተጠማሁ” አለ። በዚያም ሆምጣጤ የመላበት ማሰሮ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በስምዛ ዘንግ ከአፉ አገናኝተው ጨመቁት።
ዮሐንስ 19:25-29 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱና የእናቱ እኅት፣ እንዲሁም የቀለዮጳ ሚስት ማርያምና መግደላዊት ማርያም ቆመው ነበር። በዚያም ኢየሱስ እናቱንና የሚወድደውም ደቀ መዝሙር አጠገቧ ቆሞ ሲያያቸው እናቱን፣ “አንቺ ሴት ሆይ፤ ልጅሽ ይኸው” አላት፤ ደቀ መዝሙሩንም፣ “እናትህ ይህችው” አለው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ ደቀ መዝሙር ወደ ቤቱ ወሰዳት። ከዚያም ኢየሱስ ሁሉ ነገር እንደ ተፈጸመ ዐውቆ፣ የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም፣ “ተጠማሁ” አለ። በዚያም የሖመጠጠ ወይን የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሰፍነግ በወይን ጠጅ ነክረው፣ በሂሶጵ ዘንግ ወደ አፉ አቀረቡለት፤
ዮሐንስ 19:25-29 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ። ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፦ “አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ” አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን፦ “እናትህ እነኋት” አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ፦ “ተጠማሁ” አለ። በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት።
ዮሐንስ 19:25-29 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱና የእናቱ እኅት፥ የቀልዮጳ ሚስት ማርያምና መግደላዊት ማርያም ቆመው ነበር፤ ኢየሱስ እናቱንና የሚወደውን ደቀ መዝሙር አጠገቡ ቆመው ባያቸው ጊዜ፥ እናቱን “እናቴ ሆይ! እነሆ፥ ልጅሽ!” አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን “እነኋት እናትህ!” አለው፤ ከዚያ ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉም ነገር እንደ ተፈጸመ ዐውቆ በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈውም ቃል እንዲፈጸም “ተጠማሁ!” አለ። እዚያ ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ ስለዚህ እዚያ የነበሩ ሰዎች፥ ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞሉና በሂሶጵ እንጨት አንጠልጥለው ወደ አፉ አቀረቡለት፤
ዮሐንስ 19:25-29 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም እንዲሁም መግደላዊት ማርያም ቆመው ነበር። ኢየሱስም እናቱንና ይወደው የነበረውንም ደቀመዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን “አንቺ ሴት ሆይ! እነሆ ልጅሽ” አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን “እናትህ እነኋት” አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከወዲሁ ሁሉ ነገር እንደ ተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉም ቃል ይፈጸም ዘንድ “ተጠማሁ” አለ። በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት።