የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 19:25-29

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 19:25-29 አማ2000

በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ መስ​ቀል አጠ​ገ​ብም እናቱ፥ የእ​ና​ቱም እኅት፥ የቀ​ለ​ዮ​ጳም ሚስት ማር​ያም፥ መግ​ደ​ላ​ዊት ማር​ያ​ምም ቆመው ነበር። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እና​ቱ​ንና የሚ​ወ​ደ​ውን ደቀ መዝ​ሙ​ሩን ቆመው ባያ​ቸው ጊዜ እና​ቱን፥ “አንች ሆይ፥ እነሆ፥ ልጅሽ” አላት። ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዝ​ሙ​ሩን፥ “እና​ትህ እነ​ኋት” አለው፤ ከዚ​ያ​ችም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝ​ሙሩ ተቀ​ብሎ ወደ ቤቱ ወሰ​ዳት። ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሁሉ እንደ ተፈ​ጸመ ባየ ጊዜ የመ​ጽ​ሐፉ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ “ተጠ​ማሁ” አለ። በዚ​ያም ሆም​ጣጤ የመ​ላ​በት ማሰሮ ነበር፤ እነ​ር​ሱም ሆም​ጣ​ጤ​ውን በሰ​ፍ​ነግ ሞል​ተው በስ​ምዛ ዘንግ ከአፉ አገ​ና​ኝ​ተው ጨመ​ቁት።