ኤርምያስ 44:16-17
ኤርምያስ 44:16-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“አንተ በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን ቃል አንሰማም። ነገር ግን እኛና አባቶቻችን፥ ነገሥታቶቻችንም፥ አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ እናደርገው እንደ ነበረ፥ ለሰማይ ንግሥት እናጥን ዘንድ፥ የመጠጥንም ቍርባን እናፈስስላት ዘንድ ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በርግጥ እናደርጋለን፤ በዚያ ጊዜም እንጀራን እንጠግብ ነበር፥ መልካምም ይሆንልን ነበር፤ ክፉም አናይም ነበር።
ኤርምያስ 44:16-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“አንተ በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን መልእክት አንሰማም፤ እናደርጋለን ያልነውን ሁሉ እናደርጋለን፤ አባቶቻችን፣ ነገሥታታችንና ባለሥልጣኖቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች እንዳደረጉት ሁሉ እኛም ለሰማይዋ ንግሥት እናጥናለን፤ የመጠጥ ቍርባን እናፈስስላታለን። በዚያ ጊዜ የተትረፈረፈ ምግብ ነበረን፤ በመልካም ሁኔታ እንገኝ ነበር እንጂ ምንም ክፉ ነገር አልገጠመንም።
ኤርምያስ 44:16-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አንተ በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን ቃል አንሰማህም። ነገር ግን እኛና አባቶቻችን ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞች በኢየሩሳሌም አደባባይ እናደርገው እንደ ነበረ፥ ለሰማይ ንግሥት እናጥን ዘንድ የመጠጥንም ቍርባን እናፈስስላት ዘንድ ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በእርግጥ እናደርጋለን፥ በዚያን ጊዜም እንጀራ እንጠግብ ነበር፥ መልካምም ይሆንልን ክፉም አናይም ነበር።
ኤርምያስ 44:16-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“አንተ በእግዚአብሔር ስም የተናገርከውን ሁሉ መስማት አንፈልግም፤ እኛ እንፈጽማለን ብለን ያሰብነውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ የሰማይ ንግሥት ተብላ ለምትጠራው አምላካችን ዕጣን እናጥናለን፤ እኛና የቀድሞ አባቶቻችን፥ ንጉሦቻችንና መሪዎቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ስናደርግ በነበረው ዐይነት አሁንም የወይን ጠጅ መባ እናቀርብላታለን። ይህን ሁሉ በምናደርግበት በዚያን ጊዜ ብዙ ሲሳይ ነበረን፤ ባለጸጎችም ስለ ነበርን ምንም ችግር አልነበረብንም።