ኤርምያስ 20:7-14

ኤርምያስ 20:7-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ሆይ፤ አታለልኸኝ፤ እኔም ተታለልሁ፤ አንተ ከእኔ እጅግ በረታህ፤ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሙሉ ማላገጫ ሆንሁ፤ ሁሉም ተዘባበቱብኝ። በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ “ሁከትና ጥፋት!” ብዬ ዐውጃለሁ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣ ቀኑን ሙሉ ስድብና ነቀፋ አስከተለብኝ። ነገር ግን፣ “ከእንግዲህ የርሱን ስም አላነሣም፤ በስሙም አልናገርም” ብል፣ ቃሉ በልቤ እንደ እሳት፣ በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ፤ ዐፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ ጨርሶ መቋቋም አልቻልሁም። “በየቦታው ሽብር አለ፤ አውግዙት፤ እናውግዘው፤” ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤ መውደቄን በመጠባበቅ፣ ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣ “ይታለል ይሆናል፣ ከዚያም እናሸንፈዋለን፤ እንበቀለዋለንም” ይላሉ። ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋራ ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤ ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤ ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም። ጻድቁን የምትፈትን ልብንና አእምሮን የምትመረምር፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጕዳዬን ለአንተ አሳልፌ ሰጥቻለሁና ስትበቀላቸው ለማየት አብቃኝ። ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርቡ፤ የድኻውን ነፍስ፣ ከክፉዎች እጅ ታድጓልና። የተወለድሁባት ዕለት የተረገመች ትሁን፤ እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን አትባረክ።

ኤርምያስ 20:7-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ሆይ! አታለልከኝ፤ እኔም ተታለልኩ፤ አንተ ከእኔ ትበረታለህ፤ ኀይልህም በእኔ ላይ እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ሰው ሁሉ በየዕለቱ በማሽሟጠጥ ይዘባበትብኛል። እኔ በምናገርበት ጊዜ ሁሉ የምናገረው ዐመፅንና ጥፋትን ነው፤ አምላክ ሆይ! አንተ ያዘዝከኝን የትንቢት ቃል በመናገሬ፥ እኔ ዘወትር እሰደባለሁ፤ መላገጫም ሆኛለሁ። ነገር ግን “ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አላስታውስም፤ በስሙም አልናገርም” በምልበት ጊዜ፥ ከእርሱ የተሰጠኝ የትንቢት ቃል በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በውስጤ ሰውሬ ልይዘው ብሞክርም፤ አፍኜ ላስቀረው አይቻለኝም። ብዙ ሰዎች ፈርተው በሹክሹክታ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ፤ “አሁን ኤርምያስን ለመክሰስ መልካም አጋጣሚ ነው!” ወዳጆቼ ናቸው የሚባሉት እንኳ ስሕተት እንዳደርግ ይጠባበቃሉ፤ “ኤርምያስ ሊታለል ይችል ይሆናል፤ ይህም ከሆነ እርሱን ይዘን እንበቀለዋለን፤” ይላሉ። እግዚአብሔር ግን እንደ ጀግና ወታደር ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ በመደናቀፍ ኀይል አጥተው ይወድቃሉ። በሚወድቁበትም ጊዜ ክፉኛ ይዋረዳሉ፤ ውርደታቸውም ለረጅም ጊዜ ይታወሳል። የሠራዊት አምላክ ሆይ! ጻድቅን ፈትነህ ታረጋግጣለህ፤ የልብንም ጥልቅ ሐሳብ ትመረምራለህ፤ አቤቱታዬን ለአንተ አቅርቤአለሁ፤ ስለዚህ ጠላቶቼን ስትበቀል እንዳይ አድርገኝ። ለእግዚአብሔር ዘምሩ! ጌታን አመስግኑ! እርሱ ችግረኞችን ከክፉ ሰዎች ኀይል ይታደጋል። የተወለድኩበት ቀን የተረገመ ይሁን! እናቴ እኔን የወለደችበትም ዕለት የተባረከ አይሁን!

ኤርምያስ 20:7-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አቤቱ! አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ እኔም ተታ​ለ​ልሁ፤ ከእ​ኔም በረ​ታህ አሸ​ነ​ፍ​ህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳ​ቂያ ሆኛ​ለሁ፤ ሁሉም ያፌ​ዙ​ብ​ኛል። በተ​ና​ገ​ርሁ ቍጥር እጮ​ኻ​ለሁ፤ ግፍና ጥፋት ብዬ እጠ​ራ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድ​ብና ዋዛ ሆኖ​ብ​ኛ​ልና። እኔም እን​ዲህ አልሁ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አላ​ነ​ሣም፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በስሙ አል​ና​ገ​ርም፥” በአ​ጥ​ን​ቶች ውስጥ እንደ ገባ እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነ​ብኝ፤ ደከ​ምሁ፤ መሸ​ከ​ምም አል​ቻ​ል​ሁም። በእኔ ላይ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና የከ​በ​ቡ​ኝን የብዙ ሰዎ​ችን ስድብ ሰም​ቻ​ለሁ፤ መው​ደ​ቄን የሚ​ጠ​ብቁ የሰ​ላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምና​ል​ባት ይታ​ለል እንደ ሆነ፥ እና​ሸ​ን​ፈ​ውም እንደ ሆነ፥ እር​ሱ​ንም እን​በ​ቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እን​ነ​ሣ​ለን” ይላሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለ​ዚህ አሳ​ዳ​ጆች ይሰ​ና​ከ​ላሉ፤ አያ​ሸ​ን​ፉም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም የማ​ይ​ረሳ ጕስ​ቍ​ል​ና​ቸ​ውን አላ​ወ​ቁ​ምና ፈጽ​መው አፈሩ። አቤቱ! ጽድ​ቅን የም​ት​ፈ​ትን ኵላ​ሊ​ት​ንና ልብን የም​ት​መ​ረ​ምር የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሆይ! ክር​ክ​ሬን ገል​ጬ​ል​ሃ​ለ​ሁና ፍረ​ድ​ልኝ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፤ አመ​ስ​ግ​ኑ​ትም፤ የች​ግ​ረ​ኛ​ውን ነፍስ ከክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎች እጅ አድ​ኖ​አ​ልና። የተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባት ቀን፥ እናቴ እኔን የወ​ለ​ደ​ች​ባት ቀን የተ​ረ​ገ​መች ትሁን፤ የተ​ባ​ረ​ከ​ችም አት​ሁን።

ኤርምያስ 20:7-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ሆይ፤ አታለልኸኝ፤ እኔም ተታለልሁ፤ አንተ ከእኔ እጅግ በረታህ፤ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሙሉ ማላገጫ ሆንሁ፤ ሁሉም ተዘባበቱብኝ። በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ “ሁከትና ጥፋት!” ብዬ ዐውጃለሁ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣ ቀኑን ሙሉ ስድብና ነቀፋ አስከተለብኝ። ነገር ግን፣ “ከእንግዲህ የርሱን ስም አላነሣም፤ በስሙም አልናገርም” ብል፣ ቃሉ በልቤ እንደ እሳት፣ በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ፤ ዐፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ ጨርሶ መቋቋም አልቻልሁም። “በየቦታው ሽብር አለ፤ አውግዙት፤ እናውግዘው፤” ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤ መውደቄን በመጠባበቅ፣ ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣ “ይታለል ይሆናል፣ ከዚያም እናሸንፈዋለን፤ እንበቀለዋለንም” ይላሉ። ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋራ ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤ ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤ ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም። ጻድቁን የምትፈትን ልብንና አእምሮን የምትመረምር፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጕዳዬን ለአንተ አሳልፌ ሰጥቻለሁና ስትበቀላቸው ለማየት አብቃኝ። ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርቡ፤ የድኻውን ነፍስ፣ ከክፉዎች እጅ ታድጓልና። የተወለድሁባት ዕለት የተረገመች ትሁን፤ እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን አትባረክ።

ኤርምያስ 20:7-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አቤቱ፥ አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ፥ ከእኔም በረታህ አሸነፍህም፥ ቀኑን ሁሉ መሳቂያ ሆኛለሁ፥ ሁሉም ያላግጡብኛል። በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፥ ግፍና ጥፋት ብዬ እጮኻለሁ፥ የእግዚአብሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና ዋዛ ሆኖብኛልና። እኔም፦ የእግዚአብሔርን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፥ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም። የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ ምናልባት ይታለል እንደ ሆነ፥ እናሸንፈውም እንደ ሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደ ሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን ይላሉ። እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያልና እንደ ጨካኝ ከእኔ ጋር ነው፥ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፥ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘላለምም በማይረሳ ጕስቍልና ይጐሰቍላሉ። አቤቱ፥ ጻድቅን የምትመረምር ኵላሊትንና ልብን የምትመለከት የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ ክርክሬን ገልጬልሃለሁና በቀልህን በላያቸው ለይ። ለእግዚአብሔር ዘምሩ እግዚአብሔርንም አመስግኑ፥ የችግረኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና። የተወለድሁባት ቀን የተረገመች ትሁን፥ እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን የተባረከች አትሁን።

ኤርምያስ 20:7-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ሆይ! አታለልከኝ፤ እኔም ተታለልኩ፤ አንተ ከእኔ ትበረታለህ፤ ኀይልህም በእኔ ላይ እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ሰው ሁሉ በየዕለቱ በማሽሟጠጥ ይዘባበትብኛል። እኔ በምናገርበት ጊዜ ሁሉ የምናገረው ዐመፅንና ጥፋትን ነው፤ አምላክ ሆይ! አንተ ያዘዝከኝን የትንቢት ቃል በመናገሬ፥ እኔ ዘወትር እሰደባለሁ፤ መላገጫም ሆኛለሁ። ነገር ግን “ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አላስታውስም፤ በስሙም አልናገርም” በምልበት ጊዜ፥ ከእርሱ የተሰጠኝ የትንቢት ቃል በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በውስጤ ሰውሬ ልይዘው ብሞክርም፤ አፍኜ ላስቀረው አይቻለኝም። ብዙ ሰዎች ፈርተው በሹክሹክታ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ፤ “አሁን ኤርምያስን ለመክሰስ መልካም አጋጣሚ ነው!” ወዳጆቼ ናቸው የሚባሉት እንኳ ስሕተት እንዳደርግ ይጠባበቃሉ፤ “ኤርምያስ ሊታለል ይችል ይሆናል፤ ይህም ከሆነ እርሱን ይዘን እንበቀለዋለን፤” ይላሉ። እግዚአብሔር ግን እንደ ጀግና ወታደር ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ በመደናቀፍ ኀይል አጥተው ይወድቃሉ። በሚወድቁበትም ጊዜ ክፉኛ ይዋረዳሉ፤ ውርደታቸውም ለረጅም ጊዜ ይታወሳል። የሠራዊት አምላክ ሆይ! ጻድቅን ፈትነህ ታረጋግጣለህ፤ የልብንም ጥልቅ ሐሳብ ትመረምራለህ፤ አቤቱታዬን ለአንተ አቅርቤአለሁ፤ ስለዚህ ጠላቶቼን ስትበቀል እንዳይ አድርገኝ። ለእግዚአብሔር ዘምሩ! ጌታን አመስግኑ! እርሱ ችግረኞችን ከክፉ ሰዎች ኀይል ይታደጋል። የተወለድኩበት ቀን የተረገመ ይሁን! እናቴ እኔን የወለደችበትም ዕለት የተባረከ አይሁን!

ኤርምያስ 20:7-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አቤቱ! አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ፥ ከእኔም በረታህ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳቂያ ሆኛለሁ፥ ሁሉም ያላግጡብኛል። በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ “ግፍና ጥፋት” ብዬ እጮኻለሁ፤ የጌታ ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና መዘበቻ ሆኖብኛልና። እኔም፦ “የጌታን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም” ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም። የብዙ ሰዎችን የክፋት ሹክሹክታ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ “ምናልባት ይታለል እንደሆነ፥ እናሸንፈውም እንደሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን” ይላሉ። ጌታ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘለዓለምም በማይረሳ ውርደት ይዋረዳሉ። የሠራዊት ጌታ ሆይ! ጻድቅን የምትመረምር ኩላሊትንና ልብን የምትመለከት፥ ሙግቴን ገልጬልሃለሁና በቀልህን በላያቸው ልይ። ለጌታ ዘምሩ ጌታንም አመስግኑ፤ የችግርተኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና። የተወለድሁባት ቀን የተረገመች ትሁን! እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን የተባረከች አትሁን!