ኤርምያስ 11:3-4
ኤርምያስ 11:3-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንደዚህም በሏቸው፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የዚህን ቃል ኪዳን ቃል የማይሰማ ሰው ርጉም ይሁን፤ ከግብፅ ሀገር ከብረት ምድጃ ባወጣኋቸው ቀን ለአባቶቻችሁ ያዘዝሁትን፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ፤ እንዲሁም እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ” ያልሁትን ቃሌን ስሙ።
Share
ኤርምያስ 11 ያንብቡኤርምያስ 11:3-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው፤ ‘ለዚህ ኪዳን ቃል የማይታዘዝ ሰው የተረገመ ይሁን፤ ይህም ትእዛዝ የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር፣ ከብረት ማቅለጫው ምድጃ ባወጣኋቸው ጊዜ ድምፄን ቢሰሙ፣ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቁ፣ እነርሱ ሕዝቤ፣ እኔም አምላካቸው እንድሆን የሰጠኋቸው ቃል ነው፤
Share
ኤርምያስ 11 ያንብቡኤርምያስ 11:3-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንደዚህም በላቸው፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከግብጽ አገር ከብረት ምድጃ ባወጣኋቸው ቀን ለአባቶቻችሁ ያዘዝሁትን የዚህን ቃል ኪዳን ቃል የማይሰማ ሰው ርጉም ይሁን፥ አልሁም፦ ቃሌን ስሙ፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ፥ እንዲሁም እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።
Share
ኤርምያስ 11 ያንብቡ