የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 52:1-12

ኢሳይያስ 52:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ጽዮን ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ኀይልን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ! የክብር ልብስሽን ልበሺ፤ ያልተገረዘ የረከሰም ከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም። ትቢያሽን አራግፊ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ በዙፋንሽ ላይ ተቀመጪ፤ ምርኮኛዪቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ የዐንገትሽን የእስራት ሰንሰለት አውልቀሽ ጣዪ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤ ያለ ገንዘብ ትቤዣላችሁ።” ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በመጀመሪያ ሕዝቤ ይኖር ዘንድ ወደ ግብጽ ወረደ፤ በኋላም አሦር ያለ ምክንያት አስጨንቆ ገዛው። “አሁን እዚህ ምን አለኝ?” ይላል እግዚአብሔር፤ “ሕዝቤ ያለ ምክንያት ተወስዷል፤ የገዟቸው ተሣልቀውባቸዋል” ይላል እግዚአብሔር። “ቀኑን ሙሉ፣ ስሜ ያለ ማቋረጥ ይሰደባል። ስለዚህ ሕዝቤ ስሜን ያውቃል፤ በዚያ ቀንም፣ አስቀድሜ የተናገርሁ እኔ መሆኔን ይረዳል፤ እነሆ፤ እኔው ነኝ።” በተራሮች ላይ የቆሙ፣ የምሥራችን የሚያመጡ እግሮች፣ ሰላምን የሚናገሩ፣ መልካም ዜና የሚያበሥሩ፣ ድነትን የሚያውጁ፣ ጽዮንንም፣ “አምላክሽ ነግሧል!” የሚሉ እንዴት ያማሩ ናቸው። ስሚ! ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገዋል፤ በአንድነት በእልልታ ይዘምራሉ። እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ፣ በዐይኖቻቸው ያያሉ። እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣ በአንድነት በእልልታ ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቷል፤ ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቷልና። እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ፊት፣ የተቀደሰ ክንዱን ይገልጣል፤ በምድር ዳርቻዎች ያሉ ሁሉ፣ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ። እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ፣ ተለዩ! ተለዩ! ከመካከልዋ ውጡ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከዚያ ውጡ ንጹሓንም ሁኑ፤ ሆኖም በችኰላ አትወጡም፤ ሸሽታችሁም አትሄዱም፤ እግዚአብሔር ፊት ፊታችሁ ይሄዳል፤ የእስራኤል አምላክ ደጀን ይሆናችኋል።

ኢሳይያስ 52:1-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይ​ል​ሽን ልበሺ፤ አን​ቺም ቅድ​ስ​ቲቱ ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘና ርኩስ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያ​ል​ፍ​ምና ክብ​ር​ሽን ልበሺ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ትቢ​ያን አራ​ግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀ​መጪ፤ ምር​ኮ​ኛ​ዪቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ የአ​ን​ገ​ት​ሽን እስ​ራት ፍቺ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በከ​ንቱ ተሸ​ጣ​ችሁ ነበር፤ ያለ ወር​ቅም እቤ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።” ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕዝቤ አስ​ቀ​ድሞ ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚ​ያም በስ​ደት ኖሩ፤ ከዚ​ያም ወደ አሦር በግድ ተወ​ሰዱ። ሕዝቤ በከ​ንቱ ተወ​ስ​ዶ​አ​ልና አሁን ከዚህ ምን አቆ​ማ​ችሁ?” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ፤ ትጮ​ሃ​ላ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ስሜም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ሁል​ጊዜ ይሰ​ደ​ባል። ስለ​ዚህ ሕዝቤ ስሜን ያው​ቃል፤ የም​ና​ገ​ርና ያለሁ እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያው​ቃሉ።” ሰላ​ምን የሚ​ያ​ወራ፥ መል​ካም የም​ሥ​ራ​ች​ንም የሚ​ና​ገር፥ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም የሚ​ያ​ወራ፥ ጽዮ​ን​ንም፥ “አም​ላ​ክሽ ነግ​ሦ​አል” የሚል ሰው እግሩ በተ​ራ​ሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው። እነሆ፥ የሚ​ጠ​ብ​ቁሽ ሰዎች ድምፅ ከፍ ከፍ ይላ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጽዮ​ንን ይቅር ባላት ጊዜ ዐይን በዐ​ይን ይተ​ያ​ያ​ሉና በአ​ን​ድ​ነት በቃ​ላ​ቸው ደስ ይላ​ቸ​ዋል። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ፍር​ስ​ራ​ሾች ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ብሎ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን አድ​ኖ​አ​ታ​ልና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ክን​ዱን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ገል​ጦ​አል፤ በም​ድር ዳርቻ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ሁሉ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ማዳን ያያሉ። እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕቃ የም​ት​ሸ​ከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩ​ስን ነገር አት​ንኩ፤ ከመ​ካ​ከ​ልዋ ውጡ፤ ራሳ​ች​ሁን ለዩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ይሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና በች​ኮላ አት​ወ​ጡም፤ በመ​ኮ​ብ​ለ​ልም አት​ሄ​ዱም።

ኢሳይያስ 52:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፥ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትቢያን አራግፊ፥ ተነሺ፥ ተቀመጪ፥ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በከንቱ ተሽጣችሁ ነበር፥ ያለ ገንዘብም ትቤዣላችሁ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወገኔ በዚያ እንግዳ ሆኖ ይቀመጥ ዘንድ አስቀድሞ ወደ ግብጽ ወረደ፥ አሦርም ያለ ምክንያት በደለው። ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል እግዚአብሔር፥ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ስሜም ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ይሰደባል። ስለዚህ ወገኔ ስሜን ያውቃል፥ ስለዚህም የምናገር እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያውቃሉ፥ እነሆ፥ እኔ ነኝ። የምስራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው። እነሆ፥ ጕበኞችሽ ጮኸዋል፥ እግዚአብሔር ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ በአንድነትም ይዘምራሉ። እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ፥ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና፥ ኢየሩሳሌምንም ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፥ በአንድነትም ዘምሩ። እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፥ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ። እናንተ የእግዚአብሔር ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፥ እልፍ በሉ፥ ከዚያ ውጡ፥ ርኩስን ነገር አትንኩ፥ ከመካከልዋ ውጡ፥ ንጹሐን ሁኑ። እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኮላ አትወጡም በመኮብለልም አትሄዱም።

ኢሳይያስ 52:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ጽዮን ሆይ! ተነሺ፤ ንቂ! ኀይልሽን እንደ ልብስ ልበሺ! ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ! የተዋበ ልብስሽን ልበሺ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዙና በሥርዓት ያልነጹ ሰዎች ወደ ቅጥርሽ ውስጥ አይገቡም። ምርኮኛይቱ ኢየሩሳሌም ሆይ! ተነሥተሽ ትቢያሽን አራግፊ፤ በዙፋን ላይም ተቀመጪ፤ እናንተም የጽዮን ምርኮኞች ሆይ! የታሰራችሁበትን ሰንሰለት ከአንገታችሁ ፍቱ። እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዲህ ይላል፦ “ለባርነት ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤ የምትዋጁትም ዋጋ ሳይከፈል ነው። ከዚህ በፊት ወደ ግብጽ ወርዳችሁ በስደት የኖራችሁት በፈቃዳችሁ ነበር፤ አሦራውያን ግን ምንም ሳይከፍሉባችሁ ማርከው በመውሰድ በብርቱ ጨቊነው ገዙአችሁ”። “ሕዝቤ ያለ ዋጋ ሲወሰድ እያየሁ አሁን እኔ የማደርገው ምን አለ? ገዢዎቻቸውም ይሳለቁባቸዋል፤ ያለማቋረጥም ስሜን ይሰድባሉ። ስለዚህ በዚያን ጊዜ ሕዝቤ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን፥ ይህንንም የምናገረው እኔ መሆኔን ያውቃሉ።” በተራሮች ላይ ስለ ሰላምና ስለ መዳን የሚናገር፥ መልካም ዜናንም የሚያበሥር፥ “አምላክሽ ይነግሣል!” ብሎ ለጽዮን የሚነግራት የመልክተኛ እግሩ ምንኛ ድንቅ ነው! እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ በግልጽ ስለሚያዩ ከተማ ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የደስታ መዝሙር ሲዘምሩ አድምጪ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል ኢየሩሳሌምንም ይታደጋል ስለዚህ እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ! ተባብራችሁ በደስታ ዘምሩ። እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ፊት ኀያልነቱን ይገልጣል፤ መላው ዓለምም የእርሱን አዳኝነት ያያል። እናንተ የቤተ መቅደስን ንዋያተ ቅድሳት የተሸከማችሁ! ከባቢሎን ውጡ፤ ከእርሱም ተለዩ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋም ወጥታችሁ ራሳችሁን አንጹ። እግዚአብሔር በፊታችሁ ሆኖ ስለሚመራችሁ፥ የእስራኤል አምላክ ከበኋላ ሆኖ ስለሚጠብቃችሁ ስትወጡም በችኰላና በመኰብለል አይሆንም።

ኢሳይያስ 52:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትቢያን አራግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀመጪ፤ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ። ጌታ እንዲህ ይላል፦ በከንቱ ተሽጣችሁ ነበር፥ ያለ ገንዘብም ትቤዣላችሁ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወገኔ በዚያ እንግዳ ሆኖ ይቀመጥ ዘንድ አስቀድሞ ወደ ግብጽ ወረደ፥ አሦርም ያለ ምክንያት በደለው። ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል ጌታ፤ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፥ ይላል ጌታ፥ ስሜም ያለማቋረጥ በየእለቱ ቀኑን ሙሉ ይሰደባል። ስለዚህ ወገኔ ስሜን ያውቃል፥ ስለዚህም የምናገር እኔ እንደሆንሁ በዚያ ቀን ያውቃሉ፤ እነሆ፥ እኔ ነኝ። የምሥራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምሥራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ውብ ነው። እነሆ፥ ጉበኞችሽ ጮኸዋል፤ ጌታ ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዐይን በዐይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ በአንድነትም ይዘምራሉ። እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ፥ ጌታ ሕዝቡን አጽናንቶአልና፥ ኢየሩሳሌምንም ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፥ በአንድነትም ዘምሩ። ጌታ የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፥ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ። እናንተ የጌታን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ፥ እልፍ በሉ፥ ከዚያ ውጡ፥ ርኩስን ነገር አትንኩ፥ ከመካከልዋ ውጡ፥ ንጹሐን ሁኑ። ጌታ ቀድሟችሁ ያልፋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኮላ አትወጡም፤ በመኮብለልም አትሄዱም።