ጽዮን ሆይ! ተነሺ፤ ንቂ! ኀይልሽን እንደ ልብስ ልበሺ! ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ! የተዋበ ልብስሽን ልበሺ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዙና በሥርዓት ያልነጹ ሰዎች ወደ ቅጥርሽ ውስጥ አይገቡም። ምርኮኛይቱ ኢየሩሳሌም ሆይ! ተነሥተሽ ትቢያሽን አራግፊ፤ በዙፋን ላይም ተቀመጪ፤ እናንተም የጽዮን ምርኮኞች ሆይ! የታሰራችሁበትን ሰንሰለት ከአንገታችሁ ፍቱ። እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዲህ ይላል፦ “ለባርነት ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤ የምትዋጁትም ዋጋ ሳይከፈል ነው። ከዚህ በፊት ወደ ግብጽ ወርዳችሁ በስደት የኖራችሁት በፈቃዳችሁ ነበር፤ አሦራውያን ግን ምንም ሳይከፍሉባችሁ ማርከው በመውሰድ በብርቱ ጨቊነው ገዙአችሁ”። “ሕዝቤ ያለ ዋጋ ሲወሰድ እያየሁ አሁን እኔ የማደርገው ምን አለ? ገዢዎቻቸውም ይሳለቁባቸዋል፤ ያለማቋረጥም ስሜን ይሰድባሉ። ስለዚህ በዚያን ጊዜ ሕዝቤ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን፥ ይህንንም የምናገረው እኔ መሆኔን ያውቃሉ።” በተራሮች ላይ ስለ ሰላምና ስለ መዳን የሚናገር፥ መልካም ዜናንም የሚያበሥር፥ “አምላክሽ ይነግሣል!” ብሎ ለጽዮን የሚነግራት የመልክተኛ እግሩ ምንኛ ድንቅ ነው! እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ በግልጽ ስለሚያዩ ከተማ ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የደስታ መዝሙር ሲዘምሩ አድምጪ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል ኢየሩሳሌምንም ይታደጋል ስለዚህ እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ! ተባብራችሁ በደስታ ዘምሩ። እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ፊት ኀያልነቱን ይገልጣል፤ መላው ዓለምም የእርሱን አዳኝነት ያያል። እናንተ የቤተ መቅደስን ንዋያተ ቅድሳት የተሸከማችሁ! ከባቢሎን ውጡ፤ ከእርሱም ተለዩ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋም ወጥታችሁ ራሳችሁን አንጹ። እግዚአብሔር በፊታችሁ ሆኖ ስለሚመራችሁ፥ የእስራኤል አምላክ ከበኋላ ሆኖ ስለሚጠብቃችሁ ስትወጡም በችኰላና በመኰብለል አይሆንም።
ትንቢተ ኢሳይያስ 52 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ኢሳይያስ 52:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos