ኢሳይያስ 48:16
ኢሳይያስ 48:16 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ወደ እኔ ቀርባችሁ ይህን ስሙ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ የተናገርኩት በምሥጢር አይደለም፤ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እኔ እዚያ ነበርኩ።” አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።
ኢሳይያስ 48:16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፤ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።
ኢሳይያስ 48:16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህን ስሙ፤ “ከመጀመሪያ ጀምሮ በስውር አልተናገርሁም፤ ሲፈጸምም እኔ እዚያው ነበርሁ።” አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።
ኢሳይያስ 48:16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፥ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፥ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።