ኢሳይያስ 44:6-8
ኢሳይያስ 44:6-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እንዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። እንደ እኔ ያለ አዳኝ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ፤ ይናገርም፤ ሰውን ከፈጠርሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለሙ የሚሆነውን ያዘጋጅልኝ፤ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይናገር። ራሳችሁን አትደብቁ፤ ከጥንት ጀምሮ አልሰማችሁምን? አልነገርኋችሁምን? ከእኔ ሌላ አምላክ እንደ ሌለ ምስክሮች ናችሁ።”
ኢሳይያስ 44:6-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“የእስራኤል ንጉሥና ቤዛ እግዚአብሔር፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የፊተኛውም እኔ ነኝ፤ የኋለኛውም እኔ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም። እስቲ እንደ እኔ ማን አለ? ይናገር፤ ሕዝቤን ከጥንት ስመሠርት ምን እንደ ነበረ፣ ገና ወደ ፊት ምን እንደሚሆን፣ ይናገር፤ በፊቴ ያስረዳ፤ ስለሚመጣውም ነገር አስቀድሞ ይናገር። አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ይህን አልነገርኋችሁምን? ቀድሞስ አላሳወቅኋችሁምን? ለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አለን? ፈጽሞ! ወይም ሌላ ዐለት አለ? የለም! ማንንም አላውቅም።”
ኢሳይያስ 44:6-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም፥ ከጥንት የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፥ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ። አትፍሩ አትደንግጡም፥ ከጥንቱም ጀምሬ አልነገርኋችሁምን? ወይስ አላሳየኋችሁምን? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም፥ ማንንም አላውቅም።
ኢሳይያስ 44:6-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የሠራዊት አምላክ፥ የእስራኤል ንጉሥና አዳኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም። እንደ እኔ ያለ ማነው? እስቲ ካለ ይናገር፤ እስቲ ማስረጃውን በፊቴ ያቅርብ፤ ወደፊት የሚሆነውን አስቀድሞ የተናገረ ማነው? እስቲ ወደፊት የሚሆነውን ይናገር። እናንተ አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ አስቀድሜ አልነገርኳችሁምን? ወይስ አልገለጽኩላችሁምን? ለዚህም እናንተ ምስክሮቼ ናቸሁ፤ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ከእኔ ሌላ መጠጊያ አለት የለም፤ ማንም የለም።”
ኢሳይያስ 44:6-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የእስራኤል ንጉሥ ጌታ፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ፥ እኔ ፍጻሜም ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም፤ ከጥንት የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፥ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገረኝ። አትፍሩ አትደንግጡም፤ ከጥንቱም ጀምሬ አልነገርኋችሁም? ወይስ አላሳየኋችሁም? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ሌላ ዐለት የለም፤ አንድም አላውቅም።