ኢሳይያስ 35:1-2
ኢሳይያስ 35:1-2 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የተጠማው ምድረ በዳ ደስ ይለዋል፤ በረሃውም ሐሤት ያደርጋል፤ እንደ ጽጌረዳም ያብባል። የዮርዳኖስም ምድረ በዳ ያብባል፤ ሐሤትንም ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብርና የቀርሜሎስ ክብር ይሰጠዋል፤ ሕዝቤም የጌታን ክብር፥ የአምላክንም ግርማ ያያሉ።
Share
ኢሳይያስ 35 ያንብቡኢሳይያስ 35:1-2 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፤ በረሓው ሐሤት ያደርጋል፤ ይፈካል፤ እንደ አደይም ያብባል። በደስታና በዝማሬ ሐሤት ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል፤ የቀርሜሎስንና የሳሮንን ግርማ ይለብሳል። የአምላካችንን ታላቅ ግርማ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ያያሉ።
Share
ኢሳይያስ 35 ያንብቡኢሳይያስ 35:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፥ በረሃውም ሐሤት ያደርጋል እንደ ጽጌ ረዳም ያብባል። እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፥ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፥ የእግዚአብሔርንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።
Share
ኢሳይያስ 35 ያንብቡ