ኢሳይያስ 1:16-18
ኢሳይያስ 1:16-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ፤ መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን እሹ፣ የተገፉትን አጽናኑ፤ አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ ለመበለቶችም ተሟገቱ። “ኑና እንዋቀሥ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላ፣ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም፣ እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል።
ኢሳይያስ 1:16-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ይልቁንስ ታጥባችሁ ንጹሕ ሁኑ፤ ክፉ ሥራችሁን ሁሉ ከፊቴ አስወግዱ፤ በደል መፈጸማችሁንም ተዉ። መልካም ማድረግንም ተማሩ፤ ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ የተጨቈኑትን ታደጉ፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት ጠብቁ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ ስሙ።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስቲ ኑና እንወያይ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ቢቀላ እኔ አጥቤ እንደ በረዶ ይጸዳል፤ እንደ ደም የቀላ ቢሆን እንደ ባዘቶ ይነጣል።
ኢሳይያስ 1:16-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ታጠቡ፤ ንጹሓንም ሁኑ፤ የሰውነታችሁን ክፋት ከዐይኖች ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግንም ተዉ፤ መልካም መሥራትን ተማሩ፤ ፍርድን ፈልጉ፤ የተገፋውን አድኑ፤ ለድሃአደጉ ፍረዱለት፤ ስለ መበለቲቱም ተሙአገቱ።” “ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነጻዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ።
ኢሳይያስ 1:16-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ፤ መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን እሹ፣ የተገፉትን አጽናኑ፤ አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ ለመበለቶችም ተሟገቱ። “ኑና እንዋቀሥ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላ፣ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም፣ እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል።
ኢሳይያስ 1:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፥ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፥ ክፉ ማድረግን ተዉ፥ መልካም መሥራትን ተማሩ፥ ፍርድን ፈልጉ፥ የተገፋውን አድኑ፥ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ። ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፥ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፥ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።