የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዕብራውያን 12:4-11

ዕብራውያን 12:4-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ገና አል​ጸ​ና​ች​ሁ​ምና ደማ​ች​ሁን ለማ​ፍ​ሰስ እስ​ክ​ት​ደ​ርሱ ኀጢ​አ​ትን ተጋ​ደ​ሉ​ኣት፥ አሸ​ን​ፉ​ኣ​ትም፤ ተስ​ፋ​ች​ሁን የም​ታ​ገ​ኙ​ባ​ትን ትም​ህ​ር​ትም ውደ​ዷት። እንደ ልጆ​ችም ከእ​ና​ንተ ጋር፥ “ልጄ ሆይ፥ የጌ​ታን ቅጣት አታ​ቅ​ልል በሚ​ገ​ሥ​ጽ​ህም ጊዜ አት​ድ​ከም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ደ​ውን ይገ​ሥ​ጻ​ልና፥ የሚ​ወ​ደ​ደ​ው​ንም ልጅ ሁሉ ይገ​ር​ፈ​ዋል” ብሎ የሚ​ነ​ጋ​ገ​ረ​ውን ምክር ረስ​ታ​ች​ኋል። ቅጣ​ታ​ች​ሁን ታገሡ፤ ልጆቹ እንደ መሆ​ና​ችሁ ይወ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ አባቱ የማ​ይ​ቈ​ጣው ልጅ ማን ነው? ነገር ግን ሁሉ የቅ​ጣት ተካ​ፋይ ሆኖ​አ​ልና፥ ያለ ቅጣት ብት​ኖሩ ዲቃ​ሎች እንጂ ልጆች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም። በሥጋ የወ​ለ​ዱን አባ​ቶ​ቻ​ችን የሚ​ቀ​ጡን፥ እኛም የም​ን​ፈ​ራ​ቸው ከሆነ፥ እን​ግ​ዲያ ይል​ቁን ለመ​ን​ፈስ አባ​ታ​ችን ልን​ታ​ዘ​ዝና ልን​ገዛ በሕ​ይ​ወ​ትም ልን​ኖር እን​ዴት ይገ​ባን ይሆን? እነ​ርሱ መል​ካም ሆኖ እንደ ታያ​ቸው ለጥ​ቂት ቀን ይቀ​ጡ​ናል፤ እርሱ ግን ከቅ​ድ​ስ​ናው እን​ድ​ን​ካ​ፈል ለጥ​ቅ​ማ​ችን ይቀ​ጣ​ናል። ቅጣት ሁሉ በጊ​ዜው ያሳ​ዝ​ናል እንጂ ደስ አያ​ሰ​ኝም፤ በኋላ ግን ለተ​ቀጡ ሰላ​ምን ያፈ​ራል፤ ጽድ​ቅ​ንም ያሰ​ጣ​ቸ​ዋል።

ዕብራውያን 12:4-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከኀጢአት ጋር ስትታገሉ ገና ደማችሁን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም። ልጆች እንደ መሆናችሁ እንዲህ በማለት የተናገራችሁን ማበረታቻ ቃልም ረስታችኋል፦ “ልጄ ሆይ፤ የጌታን ቅጣት አታቃልል፤ በሚገሥጽህም ጊዜ ተስፋ አትቍረጥ፤ ምክንያቱም ጌታ የሚወድደውን ይገሥጻል፤ እንደ ልጅ የሚቀበለውንም ይቀጣል።” እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ ይዟችኋልና የተግሣጽን ምክር ታገሡ፤ ለመሆኑ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ልጆች ሁሉ በሚቀጡበት ቅጣት ተካፋይ ካልሆናችሁ፣ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። ከዚህም በላይ፣ እኛ ሁላችን የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር። ታዲያ ለመናፍስት አባት እንዴት አብልጠን በመገዛት በሕይወት አንኖርም? አባቶቻችን መልካም መስሎ እንደ ታያቸው ለጥቂት ጊዜ ይቀጡን ነበር፤ እግዚአብሔር ግን የቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለእኛ ጥቅም ሲል ይቀጣናል። ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰዎች የጽድቅና የሰላም ፍሬ ያስገኝላቸዋል።

ዕብራውያን 12:4-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከኃጢአት ጋር እየተጋደላችሁ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም፤ እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር፦ ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል። ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን? እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል። ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል።

ዕብራውያን 12:4-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እናንተ ከኃጢአት ጋር በመታገል ገና ደም እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም። እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ አድርጎ እንዲህ ሲል የመከራችሁን ረስታችኋል፤ “ልጄ ሆይ! የጌታን ተግሣጽ አታቃል፤ በቀጣህም ጊዜ ተስፋ አትቊረጥ፤ ጌታ የሚወደውን ይገሥጻል፤ እንደ ልጁ አድርጎ የሚያየውንም ይቀጣል።” እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ ስለሚቈጥራችሁ ቅጣትን ታገሡ፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ልጆች የሆኑ ሁሉ የሚቀበሉትን ቅጣት እናንተም ካልተቀበላችሁ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። ከዚህም በቀር እኛ ሁላችን የሚቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ፥ በሕይወት ለመኖር ለመንፈሳዊ አባታችን በይበልጥ መታዘዝ እንዴት አይገባንም! እነርሱ መልካም መስሎ እንደ ታያቸው ለጥቂት ጊዜ ቀጥተውናል፤ እርሱ ግን የቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለጥቅማችን ይቀጣናል። ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ የሚያስደስት አይመስልም፤ በኋላ ግን ለተለማመዱት ሰዎች ሰላም የሞላበትን የጽድቅ ፍሬ ያስገኝላቸዋል።

ዕብራውያን 12:4-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ከኃጢአት ጋር በምታደርጉት ተጋድሎ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም፤ እንደ ልጆችም እንዲህ በማለት የተነገራችሁን ምክር ረስታችኋል፦ “ልጄ ሆይ! የጌታን ተግሣጽ አታቅልል፤ በሚገሥጽህም ጊዜ ተስፋ አትቁረጥ፤ ጌታ የሚወደውን ይገሥጻልና፤ እንደ ልጅ የሚቀበለውንም ሁሉ ይቀጣል።” እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፥ የተግሣጽን ቅጣት ታገሡ፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ሁሉም ተካፋይ ከሆኑበት ቅጣት ውጭ ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። ከዚህም በተጨማሪ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ እንዴት በላቀ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር አይገባንም? እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበር፤ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል። ለጊዜው ቅጣት ሁሉ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰላማዊ የጽድቅን ፍሬ ያፈራላቸዋል።