ወደ ዕብራውያን 12
12
እግዚአብሔር ልጆቹን እንደሚገሥጽ
1እንግዲህ እነደዚህ ዓይነት ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ማንኛውንም ሸክምና የተጣበቅንበትን ኅጢአት ሁሉ አራግፈን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ። 2የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።
3በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኀጢአተኞች የደረሰበትን እንዲህ ያለውን ተቃውሞ እንዴት እንደተቋቋመ አስቡ። 4ከኃጢአት ጋር በምታደርጉት ተጋድሎ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም፤ 5#ኢዮብ 5፥17፤ ምሳ. 3፥11፤12።እንደ ልጆችም እንዲህ በማለት የተነገራችሁን ምክር ረስታችኋል፦
“ልጄ ሆይ! የጌታን ተግሣጽ አታቅልል፤
በሚገሥጽህም ጊዜ ተስፋ አትቁረጥ፤
6ጌታ የሚወደውን ይገሥጻልና፤
እንደ ልጅ የሚቀበለውንም ሁሉ ይቀጣል።”
7እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፥ የተግሣጽን ቅጣት ታገሡ፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? 8ሁሉም ተካፋይ ከሆኑበት ቅጣት ውጭ ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። 9ከዚህም በተጨማሪ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ እንዴት በላቀ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር አይገባንም? 10እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበር፤ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል። 11ለጊዜው ቅጣት ሁሉ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰላማዊ የጽድቅን ፍሬ ያፈራላቸዋል።
12 #
ኢሳ. 35፥3። ስለዚህ የላሉትን እጆቻችሁን የሰለሉትንም ጉልበቶቻችሁን አቅኑ። 13#ምሳ. 4፥26።አንካሳውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይሰበር፥ ለእግራችሁ ቀና መንገድ አበጁ።
የእግዚአብሔርን ጸጋ ለሚንቁ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
14ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር ጣሩ፤ ያለ ቅድስናም ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና ለመቀደስም ፈልጉ። 15#ዘዳ. 29፥18።ከመካከላችሁ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት መራራ ሥር በቅሎ እንዳያስጨንቃችሁ፥ 16#ዘፍ. 25፥29-34።ማንም ሴሰኛ እንዳይሆን ወይም ስለ አንድ መብል በኩርነቱን እንደ ሸጠው ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው ሆኖ እንዳይገኝ ተጠንቀቁ። 17#ዘፍ. 27፥30-40።በኋላ እንኳን በረከቱን ለመውረስ ቢፈልግም እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ እያለቀሰ ቢፈልግም እንኳን ለንስሓ ስፍራ አላገኘምና።
18 #
ዘፀ. 19፥16-22፤ 20፥18-21፤ ዘዳ. 4፥11፤12፤ 5፥22-27። ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፥ ወደ ጭጋጉና ወደ ጨለማው፥ ወደ ዐውሎ ነፋሱ ገና አልደረሳችሁም፤ 19ወደ መለከት ድምፅ፥ ወይም ቃልን ወደሚያሰማ ድምጽ አልመጣችሁም። ያን ነገር የሰሙት ሁሉ ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው እስኪለምኑ አደረሳቸው፤ 20#ዘፀ. 19፥12፤13።ምክንያቱም “እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት፤” የምትለውን ትእዛዝ መሸከም አልቻሉም። 21#ዘዳ. 9፥19።ሙሴም “እጅግ እፈራለሁ፤ እንቀጠቀጥማለሁ፤” እስኪል ድረስ የሚታየው ነገር እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤ 22ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፤ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥ 23በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥ 24#ዘፍ. 4፥10።የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።
25 #
ዘፀ. 20፥22። የሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላይ ሲያስረዳቸው እምቢ ያሉት ካላመለጡ፥ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅቀን ፈቀቅ የምንል እኛ እንዴት እናመልጣለን? 26#ሐጌ 2፥6።ያንጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጧት ነበር፤ አሁን ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም፤” ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል። 27ዳሩ ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ” የሚል ቃል የማይናወጡት ጸንተው እንዲኖሩ፥ የሚናወጡት ፍጡራን ነገሮች እንደሆኑና እንደሚለወጡ ያሳያል። 28ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤ 29#ዘዳ. 4፥24።አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን 12: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ