ዕብራውያን 12:11-12
ዕብራውያን 12:11-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ቅጣት ሁሉ በጊዜው ያሳዝናል እንጂ ደስ አያሰኝም፤ በኋላ ግን ለተቀጡ ሰላምን ያፈራል፤ ጽድቅንም ያሰጣቸዋል። ስለዚህም የላሉትን እጆች፥ የሰለሉትንም ጕልበቶች አቅኑ።
Share
ዕብራውያን 12 ያንብቡዕብራውያን 12:11-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰዎች የጽድቅና የሰላም ፍሬ ያስገኝላቸዋል። ስለዚህ የዛለውን ክንዳችሁንና የደከመውን ጕልበታችሁን አበርቱ።
Share
ዕብራውያን 12 ያንብቡዕብራውያን 12:11-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል። ስለዚህ የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጉልበቶች አቅኑ፤
Share
ዕብራውያን 12 ያንብቡዕብራውያን 12:11-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ የሚያስደስት አይመስልም፤ በኋላ ግን ለተለማመዱት ሰዎች ሰላም የሞላበትን የጽድቅ ፍሬ ያስገኝላቸዋል። ስለዚህ የዛሉትን እጆቻችሁንና የደከሙትን ጒልበቶቻችሁን አበርቱ።
Share
ዕብራውያን 12 ያንብቡ