የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዕብራውያን 12:1-6

ዕብራውያን 12:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን የሚ​ያ​ህሉ ምስ​ክ​ሮች እንደ ደመና በዙ​ሪ​ያ​ችን ካሉ​ልን እኛ ደግሞ ሸክ​ምን ሁሉ፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ጭን​ቀት ከእኛ አስ​ወ​ግ​ደን፥ በፊ​ታ​ችን ያለ​ውን ሩጫ በት​ዕ​ግ​ሥት እን​ሩጥ። የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና። በነ​ፍ​ሳ​ችሁ ዝላ​ችሁ እን​ዳ​ት​ደ​ክሙ፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች በደ​ረ​ሰ​በት እን​ዲህ ባለ መቃ​ወም የጸ​ና​ውን እስኪ ዐስ​ቡት። ገና አል​ጸ​ና​ች​ሁ​ምና ደማ​ች​ሁን ለማ​ፍ​ሰስ እስ​ክ​ት​ደ​ርሱ ኀጢ​አ​ትን ተጋ​ደ​ሉ​ኣት፥ አሸ​ን​ፉ​ኣ​ትም፤ ተስ​ፋ​ች​ሁን የም​ታ​ገ​ኙ​ባ​ትን ትም​ህ​ር​ትም ውደ​ዷት። እንደ ልጆ​ችም ከእ​ና​ንተ ጋር፥ “ልጄ ሆይ፥ የጌ​ታን ቅጣት አታ​ቅ​ልል በሚ​ገ​ሥ​ጽ​ህም ጊዜ አት​ድ​ከም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ደ​ውን ይገ​ሥ​ጻ​ልና፥ የሚ​ወ​ደ​ደ​ው​ንም ልጅ ሁሉ ይገ​ር​ፈ​ዋል” ብሎ የሚ​ነ​ጋ​ገ​ረ​ውን ምክር ረስ​ታ​ች​ኋል።

ዕብራውያን 12:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እንደ ደመና በዙሪያችን የከበቡን እነዚህ ሁሉ ምስክሮች ስላሉን እኛ እንደ ሸክም የሆነብንን ነገር ሁሉ በእኛ ላይ የተጣበቀብንን ኃጢአት አስወግደን በፊታችንም ያለውን የሩጫ እሽቅድድም በትዕግሥት በመጽናት እንሩጥ። የምንሮጠውም የእምነታችን መሥራችና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ እርሱ በፊቱ በተደቀነው ደስታ ምክንያት በመስቀል ላይ የመሞትን ውርደት ከምንም ሳይቈጥር የመስቀልን መከራና ሞት ታገሠ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝም ተቀመጠ። እንግዲህ ሳትሰለቹና ተስፋ ሳትቈርጡ ይህን ሁሉ የኃጢአተኞችን ተቃውሞ የታገሠውን ኢየሱስን ተመልከቱ። እናንተ ከኃጢአት ጋር በመታገል ገና ደም እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም። እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ አድርጎ እንዲህ ሲል የመከራችሁን ረስታችኋል፤ “ልጄ ሆይ! የጌታን ተግሣጽ አታቃል፤ በቀጣህም ጊዜ ተስፋ አትቊረጥ፤ ጌታ የሚወደውን ይገሥጻል፤ እንደ ልጁ አድርጎ የሚያየውንም ይቀጣል።”

ዕብራውያን 12:1-6

ዕብራውያን 12:1-6 NASVዕብራውያን 12:1-6 NASVዕብራውያን 12:1-6 NASVዕብራውያን 12:1-6 NASVዕብራውያን 12:1-6 NASVዕብራውያን 12:1-6 NASV