ዕብራውያን 11:8-13

ዕብራውያን 11:8-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ። በእ​ም​ነ​ትም ከሀ​ገሩ ወጥቶ ተስፋ በሰ​ጠው ሀገር እንደ ስደ​ተኛ በድ​ን​ኳን፥ ተስ​ፋ​ውን ከሚ​ወ​ር​ሱ​አት ከይ​ስ​ሐ​ቅና ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ኖረ። መሠ​ረት ያላ​ትን ሠሪ​ዋና ፈጣ​ሪዋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆ​ነ​ላ​ትን ከተማ ደጅ ይጠኑ ነበ​ርና። ራስዋ ሳራም መካን ሳለች ባረ​ጀ​ች​በት ወራት ዘር ታስ​ገኝ ዘንድ በእ​ም​ነት ኀይ​ልን አገ​ኘች፤ ተስፋ የሰ​ጣት የታ​መነ እንደ ሆነ አም​ና​ለ​ችና። ስለ​ዚ​ህም ደግሞ በብ​ዛ​ታ​ቸው እንደ ሰማይ ኮከብ፥ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠ​ርም በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ የነ​በ​ሩት የሞ​ተን ሰው እንኳ ከመ​ሰ​ለው ከአ​ንዱ ተወ​ለዱ። እነ​ዚህ ሁሉ አም​ነው ሞቱ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም አላ​ገ​ኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይ​ተው እጅ ነሱ​ኣት፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ላይ እነ​ርሱ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ።

ዕብራውያን 11:8-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው። ከእርሱ ጋር የተስፋው ቃል ወራሾች ከሆኑት ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር በተስፋይቱ አገር መጻተኛ ሆኖ በድንኳን የኖረው በእምነት ነው። ይህንንም ያደረገው ጽኑ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር ያቀዳትንና የሠራትን ከተማ ይጠባበቅ ስለ ነበር ነው። ሣራም ተስፋ የሰጣት እግዚአብሔር ታማኝ መሆኑን ስላወቀች ምንም እንኳ በዕድሜ በመግፋቷ መውለድ የማትችል ብትሆን የመፅነስን ኀይል ያገኘችው በእምነት ነው። ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠረው ከአንዱ ከአብርሃም እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የማይቈጠር ዘር ተገኘ። እነዚህ ሁሉ በእምነት እንዳሉ ሞቱ፤ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውንም ነገር አላገኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይተው ልክ እንዳገኙት አድርገው በደስታ ተቀበሉት። በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውንም ተገነዘቡ።

ዕብራውያን 11:8-13 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴትም እንደሚሄድም ሳያውቅ ሄደ። ለባዕድ አገር እያለም በተስፋ ቃል በተሰጠው ምድር፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ወራሾች እንደሆኑት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በእምነት በድንኳን ኖረ፤ ምክንያቱም መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበር። ሣራም ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደሆነ ስለ ቈጠረች፥ ምንም እንኳን መካን ብትሆን፥ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠር ከዚህ ከአንድ ሰው፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ተቈጥሮ የማያልቅ ዘር ተገኘ። እነዚህ ሁሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ሳያገኙ እምነታቸውን እንደ ጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከርቀት አይተውት ሰላምታ አቀረቡለት፤ በዚህ ምድር ሲኖሩም እንግዶችና መጻተኞች ለመሆንም ታመኑ።