ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 11:8-13

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 11:8-13 አማ2000

አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ። በእ​ም​ነ​ትም ከሀ​ገሩ ወጥቶ ተስፋ በሰ​ጠው ሀገር እንደ ስደ​ተኛ በድ​ን​ኳን፥ ተስ​ፋ​ውን ከሚ​ወ​ር​ሱ​አት ከይ​ስ​ሐ​ቅና ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ኖረ። መሠ​ረት ያላ​ትን ሠሪ​ዋና ፈጣ​ሪዋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆ​ነ​ላ​ትን ከተማ ደጅ ይጠኑ ነበ​ርና። ራስዋ ሳራም መካን ሳለች ባረ​ጀ​ች​በት ወራት ዘር ታስ​ገኝ ዘንድ በእ​ም​ነት ኀይ​ልን አገ​ኘች፤ ተስፋ የሰ​ጣት የታ​መነ እንደ ሆነ አም​ና​ለ​ችና። ስለ​ዚ​ህም ደግሞ በብ​ዛ​ታ​ቸው እንደ ሰማይ ኮከብ፥ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠ​ርም በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ የነ​በ​ሩት የሞ​ተን ሰው እንኳ ከመ​ሰ​ለው ከአ​ንዱ ተወ​ለዱ። እነ​ዚህ ሁሉ አም​ነው ሞቱ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም አላ​ገ​ኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይ​ተው እጅ ነሱ​ኣት፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ላይ እነ​ርሱ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ።