ዘፍጥረት 5:28-32
ዘፍጥረት 5:28-32 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ላሜሕ፣ ዕድሜው 182 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ ልጅ ወለደ። ስሙንም “እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከጕልበታችን ድካም ያሳርፈናል” ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው። ላሜሕ ኖኅን ከወለደ በኋላ፣ 595 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። ላሜሕ በአጠቃላይ 777 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ። ኖኅ ዕድሜው 500 ዓመት ሲሆን ሴምን፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።
ዘፍጥረት 5:28-32 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ልጅንም ወለደ። ስሙንም ከሥራዬ፥ ከእጄ ድካምና እግዚአብሔር ከረገማት ምድር ይህ ያሳርፈኝ ዘንድ አለው ሲል “ኖኅ” ብሎ ጠራው። ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ላሜሕም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ፤ ሞተም። ለኖኅም አምስት መቶ ዓመት ሆነው፤ ኖህም ሦስት ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው።
ዘፍጥረት 5:28-32 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ላሜሕ፣ ዕድሜው 182 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ ልጅ ወለደ። ስሙንም “እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከጕልበታችን ድካም ያሳርፈናል” ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው። ላሜሕ ኖኅን ከወለደ በኋላ፣ 595 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። ላሜሕ በአጠቃላይ 777 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ። ኖኅ ዕድሜው 500 ዓመት ሲሆን ሴምን፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።
ዘፍጥረት 5:28-32 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ልጅንም ወለደ። ስሙንም፤ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከተግባራችንና ከእጅ ሥራችን ይህ ያሳርፈናል ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው። ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኍላ የኖረው አምስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ዓመት ሆነ ሞተም። ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ፤ ኖኅም ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ።
ዘፍጥረት 5:28-32 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ላሜክ 182 ዓመት ሲሆነው ወንድ ልጅ ወለደ፤ “ይህ ልጅ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ላይ ከብርቱ ሥራችን ያሳርፈናል” ሲል “ኖኅ” ብሎ ጠራው። ከዚህ በኋላ ላሜክ 595 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ ዕድሜው 777 ሲሆነውም ሞተ። ኖኅ 500 ዓመት ከሆነው በኋላ ሦስት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ እነርሱም ሴም፥ ካምና ያፌት ይባሉ ነበር።
ዘፍጥረት 5:28-32 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ወንድ ልጅም ወለደ። ስሙንም፥ “ጌታ በረገማት ምድር፥ ከሥራችን እና ከእጅ ድካማችን፥ ይህ ያሳርፈናል” ሲል፥ ኖኅ ብሎ ጠራው። ኖኅንም ከወለደ በኋላ ላሜሕ አምስት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ ሰባ ሰባት ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ኖኅም ሴምን፥ ካምን እና ያፌትን ወለደ፤ ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ።