ኦሪት ዘፍጥረት 5:28-32

ኦሪት ዘፍጥረት 5:28-32 መቅካእኤ

ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ወንድ ልጅም ወለደ። ስሙንም፥ “ጌታ በረገማት ምድር፥ ከሥራችን እና ከእጅ ድካማችን፥ ይህ ያሳርፈናል” ሲል፥ ኖኅ ብሎ ጠራው። ኖኅንም ከወለደ በኋላ ላሜሕ አምስት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ ሰባ ሰባት ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ኖኅም ሴምን፥ ካምን እና ያፌትን ወለደ፤ ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}