የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 5:1-27

ዘፍጥረት 5:1-27 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የሰ​ዎች የት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ይህ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዳ​ምን በፈ​ጠረ ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሳሌ አደ​ረ​ገው፤ ወን​ድና ሴት አድ​ርጎ ፈጠ​ራ​ቸው፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም። እነ​ር​ሱ​ንም በፈ​ጠ​ረ​በት ቀን ስሙን አዳም ብሎ ጠራው። አዳ​ምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅ​ንም እንደ ምሳ​ሌው እንደ መልኩ ወለደ፤ ስሙ​ንም ሴት ብሎ ጠራው። አዳ​ምም ሴትን ከወ​ለደ በኋላ የኖ​ረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። አዳ​ምም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም። ሴትም ሁለት መቶ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ሄኖ​ስ​ንም ወለደ፤ ሴትም ሄኖ​ስን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። ሴትም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም። ሄኖ​ስም መቶ ዘጠና ዓመት ኖረ፤ ቃይ​ና​ን​ንም ወለደ፤ ሄኖ​ስም ቃይ​ና​ንን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ዐሥራ አም​ስት ዓመት ኖረ። ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። ሄኖ​ስም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አም​ስት ዓመት ሆነ፤ ሞተም። ቃይ​ና​ንም መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፤ መላ​ል​ኤ​ል​ንም ወለደ፤ ቃይ​ና​ንም መላ​ል​ኤ​ልን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። ቃይ​ና​ንም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥር ዓመት ሆነ፤ ሞተም። መላ​ል​ኤ​ልም መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ያሬ​ድ​ንም ወለደ፤ መላ​ል​ኤ​ልም ያሬ​ድን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። መላ​ል​ኤ​ልም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ስም​ንት መቶ ዘጠና አም​ስት ዓመት ሆነ፤ ሞተም። ያሬ​ድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ሄኖ​ክ​ንም ወለደ፤ ያሬ​ድም ሄኖ​ክን ከወ​ለደ በኋላ ስም​ንት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። ያሬ​ድም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም። ሄኖ​ክም መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ማቱ​ሳ​ላ​ንም ወለደ፤ ሄኖ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው፤ ሄኖ​ክም ማቱ​ሳ​ላን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። ሄኖ​ክም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት ሆነ። ሄኖ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ስላ​ሰ​ኘው አል​ተ​ገ​ኘም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው​ሮ​ታ​ልና። ማቱ​ሳ​ላም መቶ ሰማ​ንያ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ላሜ​ሕ​ንም ወለደ፤ ማቱ​ሳ​ላም ላሜ​ሕን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰማ​ንያ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። ማቱ​ሳ​ላም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።

ዘፍጥረት 5:1-27 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የተጻፈው የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው። እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው በራሱ አምሳል አበጀው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ባረካቸው፤ በተፈጠሩም ጊዜ “ሰው” ብሎ ጠራቸው፦ አዳም፣ ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን ራሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው። ሴት ከተወለደም በኋላ፣ አዳም 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ። ሴት፣ ዕድሜው 105 ዓመት ሲሆን ሄኖስን ወለደ፤ ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ 807 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። ሴት በአጠቃላይ 912 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ። ሄኖስ፣ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነ ጊዜ ቃይናንን ወለደ፤ ሄኖስ ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። ሄኖስ በአጠቃላይ 905 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ። ቃይናን፣ ዕድሜው 70 ዓመት ሲሆን መላልኤልን ወለደ፤ ቃይናን መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። ቃይናን በአጠቃላይ 910 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ። መላልኤል፣ ዕድሜው 65 ዓመት በሆነ ጊዜ ያሬድን ወለደ፤ መላልኤል ያሬድን ከወለደ በኋላ 830 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። መላልኤል በአጠቃላይ 895 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ። ያሬድ፣ ዕድሜው 162 ዓመት ሲሆን ሔኖክን ወለደ፤ ያሬድ ሔኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። ያሬድ በአጠቃላይ 962 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ። ሔኖክ፣ ዕድሜው 65 ዓመት በሆነ ጊዜ ማቱሳላን ወለደ፤ ሔኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋራ በማድረግ 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። ሔኖክ በአጠቃላይ 365 ዓመት ኖረ፤ ሔኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋራ አደረገ፤ እግዚአብሔር ስለ ወሰደውም አልተገኘም። ማቱሳላ፣ ዕድሜው 187 ዓመት ሲሆን ላሜሕን ወለደ፤ ማቱሳላ ላሜሕን ከወለደ በኋላ፣ 782 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ ማቱሳላ በአጠቃላይ 969 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።

ዘፍጥረት 5:1-27 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የአዳም የትውልዱ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው። አዳምም ሴትን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወስደ። አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ ሞተም። ሴትም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ፤ ሄኖስንም ወለደ፤ ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ሴትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥራ ሁለት ዓመት ሆነ ሞተም። ሄኖስም መቶ ዘጠና ዓመት ኖረ፤ ቃይናንንም ወለደ፤ ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ አሥራ አምስት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ሄኖስም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምስት ዓመት ሆነ ሞተም። ቃይናንም መቶ ሰባ ዓምት ኖረ፤ መላልኤልንም ወለደ፤ ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ አርባ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ቃይናንም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥር ዓመት ሆነ ሞተም። መላልኤልም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ያሬድንም ወለደ። መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንችም ወለደ። መላልኤልም የኖረበት ዘመን ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ ሞተም። ያሬድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ሄኖክንም ወለደ ያሬድም ሄኖክን ከወለደ በኍላ የኖረው ስምንት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ያሬድም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ሆነ ሞተም። ሄኖክም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ማቱሳላንም ወለደ፤ ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፤ ማቱሳላንም ከወለደ በኍላ የኖረው ሁለት መቶ ዓመት ሆነ ወለደ። ሄኖክም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ። ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና። ማቱሳላም መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ላሜሕንም ወለደ፤ ማቱሳላም ላሜሕን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ማቱሳላም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ ሞትም።

ዘፍጥረት 5:1-27 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የአዳም የዘር ሐረግ ከዚህ የሚከተለው ነው፦ እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረ ጊዜ በራሱ አምሳያ ፈጠራቸው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸው፤ “ሰው” ብሎም ሰየማቸው። አዳም መቶ ሠላሳ ዓመት በሆነው ጊዜ በመልኩና በአምሳያው እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ “ሤት” የሚል ስምም አወጣለት። ከዚህ በኋላ አዳም 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ ዕድሜው 930 ዓመት ሲሆነውም ሞተ። ሴት 105 ዓመት ሲሆነው ሄኖስን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ ሴት 807 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ ዕድሜው 912 ዓመት ሲሆነውም ሞተ። ሄኖስ 90 ዓመት ሲሆነው ቃይናንን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 815 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ ዕድሜው 905 ሲሆነውም ሞተ። ቃይናንም 70 ዓመት ሲሆነው መላልኤልን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 840 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ ዕድሜው 910 ሲሆነውም ሞተ። መላልኤል 65 ዓመት ሲሆነው ያሬድን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 830 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችን ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ ዕድሜው 895 ሲሆነውም ሞተ። ያሬድ 162 ዓመት ሲሆነው ሔኖክን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ ዕድሜው 962 ሲሆነውም ሞተ። ሔኖክ 65 ዓመት ሲሆነው ማቱሳላን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ ሔኖክ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ ዕድሜው 365 እስኪሆነው ድረስ ኖረ፤ ይህን ያኽል ዘመን የኖረውም የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል ነበር፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ወሰደው አልተገኘም። ማቱሳላ 187 ዓመት ሲሆነው ላሜክን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 782 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ ዕድሜው 969 ሲሆነውም ሞተ።

ዘፍጥረት 5:1-27 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የአዳም የዘር ሐረግ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረ ጊዜ በእግዚአብሔር አምሳያ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። በተፈጠሩም ጊዜ “ሰው” ብሎ ጠራቸው። አዳምም መቶ ሠላሳ ዓመት ሲኖር፥ እሱን የሚመስል፥ አምሳያው የሆነ፥ የልጅ አባት ሆነ፤ ሤት ብሎም ስም አወጣለት። ሤትንም ከወለደ በኋላ አዳም ስምንት መቶ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ሤትም አንድ መቶ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሄኖስንም ወለደ፤ ሄኖስን ከወለደ በኋላ ሤት ስምንት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ሤትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ሄኖስም ዘጠና ዓመት ሲሆነው፥ ቃይናንንም ወለደ፥ ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ሄኖስም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምስት ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ቃይናንም ሰባ ዓመት ሲሆነው፥ መላልኤልን ወለደ፥ ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ አርባ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ቃይናንም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥር ዓመት ሆነ፥ ሞተም። መላልኤልም ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ያሬድንም ወለደ፥ መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። መላልኤልም የኖረበት ዘመን ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ያሬድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሄኖክንም ወለደ፥ ያሬድም ሄኖክን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ያሬድም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ሄኖክም ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ማቱሳላንም ወለደ፥ ከዚህ በኋላ ሔኖክ ማቱሳለን ወለደ፥ የእግዚአብሔርንም መንገድ በመከተል 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤። ሄኖክም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ። አካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ፥ እግዚአብሔር ወስዶታልና፥ ሄኖክ አልተገኘም። ማቱሳላም መቶ ሰማኒያ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ላሜሕንም ወለደ፤ ላሜሕን ከወለደ በኋላ ማቱሳላ የኖረው ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ማቱሳላም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ፥ ሞተም።