ኦሪት ዘፍጥረት 5:1-27

ኦሪት ዘፍጥረት 5:1-27 መቅካእኤ

የአዳም የዘር ሐረግ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረ ጊዜ በእግዚአብሔር አምሳያ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። በተፈጠሩም ጊዜ “ሰው” ብሎ ጠራቸው። አዳምም መቶ ሠላሳ ዓመት ሲኖር፥ እሱን የሚመስል፥ አምሳያው የሆነ፥ የልጅ አባት ሆነ፤ ሤት ብሎም ስም አወጣለት። ሤትንም ከወለደ በኋላ አዳም ስምንት መቶ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ሤትም አንድ መቶ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሄኖስንም ወለደ፤ ሄኖስን ከወለደ በኋላ ሤት ስምንት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ሤትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ሄኖስም ዘጠና ዓመት ሲሆነው፥ ቃይናንንም ወለደ፥ ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ሄኖስም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምስት ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ቃይናንም ሰባ ዓመት ሲሆነው፥ መላልኤልን ወለደ፥ ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ አርባ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ቃይናንም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥር ዓመት ሆነ፥ ሞተም። መላልኤልም ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ያሬድንም ወለደ፥ መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። መላልኤልም የኖረበት ዘመን ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ያሬድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሄኖክንም ወለደ፥ ያሬድም ሄኖክን ከወለደ በኋላ ስምንት መቶ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ያሬድም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ሆነ፥ ሞተም። ሄኖክም ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ማቱሳላንም ወለደ፥ ከዚህ በኋላ ሔኖክ ማቱሳለን ወለደ፥ የእግዚአብሔርንም መንገድ በመከተል 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤። ሄኖክም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ። አካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ፥ እግዚአብሔር ወስዶታልና፥ ሄኖክ አልተገኘም። ማቱሳላም መቶ ሰማኒያ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ላሜሕንም ወለደ፤ ላሜሕን ከወለደ በኋላ ማቱሳላ የኖረው ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ። ማቱሳላም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ፥ ሞተም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}