ዘፍጥረት 42:1-5
ዘፍጥረት 42:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ያዕቆብም በግብፅ የሚሸመት እህል እንዳለ ሰማ፤ ልጆቹንም፥ “ለምን ትተክዛላችሁ?” አላቸው። እንዲህም አለ፥ “እነሆ፥ እህል በግብፅ እንዳለ ሰምቼአለሁ፤ ወደዚያ ውረዱ፤ እንድንድንና በራብ እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን።” የዮሴፍም ዐሥሩ ወንድሞቹ እህልን ከግብፅ ይሸምቱ ዘንድ ወረዱ፤ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም፥ “ምናልባት ክፉ እንዳያገኘው” ብሎአልና። የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡት ጋር ገቡ፤ በከነዓን ሀገር ራብ ነበርና።
ዘፍጥረት 42:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ያዕቆብ በግብጽ እህል መኖሩን ሲሰማ፣ ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “ለምን እርስ በርስ ትተያያላችሁ? በግብጽ እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ከመሞት መሰንበት ይሻላልና ወደዚያው ወርዳችሁ እህል ሸምቱልን” አላቸው። ከዚያም ዐሥሩ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ወረዱ። ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን፣ ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሀት ከወንድሞቹ ጋራ አልላከውም። ራቡ በከነዓንም በመበርታቱ፣ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ከሄዱት ሰዎች መካከል የእስራኤል ልጆችም ነበሩ።
ዘፍጥረት 42:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ያዕቆብም በግብፅ እህል እንዳለ ስማ ያዕቆብም ልጆቹን፦ ለምን እርስ በርሳችሁ ትተያያላችሁ? አላቸው እንዲህም አለ፦ እነሆ ስንዴ በግብፅ እንዲገኝ ሰምቼአለሁ፤ ወደዚይ ውረዱ፥ እንድንድንና እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን። የዮሴፍም አሥሩ ወንድሞቹ ስንዴን ከግብፅ ይሸምቱ ዘንድ ወረዱ የዮሴፍ ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም፦ ምናልባት ክፋ እንዳያግኘው ብሎአልና። የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡቱ ጋር ገቡ በከነዓን አገር ራብ ነበረና።
ዘፍጥረት 42:1-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ያዕቆብ በግብጽ እህል መኖሩን በሰማ ጊዜ ልጆቹን “እርስ በርሳችሁ እየተያያችሁ የምትቀመጡት ለምንድን ነው? በግብጽ አገር እህል መኖሩን ሰምቼአለሁ፤ በራብ እንዳንሞት ወደዚያ ሂዱና እህል ሸምቱልን” አላቸው። ስለዚህ ዐሥሩ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ሄዱ፤ ነገር ግን “ጒዳት ይደርስበታል” ብሎ ስለ ፈራ ያዕቆብ ከዮሴፍ ጋር ከአንድ እናት የወለደውን ልጁን ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ወደ ግብጽ አላከውም፤ በከነዓን ምድርም ራብ ገብቶ ስለ ነበር የያዕቆብ ልጆች ከሌሎች ሰዎች ጋር እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ሄዱ።
ዘፍጥረት 42:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ያዕቆብ በግብጽ እህል መኖሩን ሲሰማ፥ ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “ለምን እርስ በርስ ትተያያላችሁ? በግብጽ እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ከመሞት መሰንበት ይሻላልና ወደዚያው ወርዳችሁ እህል ሸምቱልን” አላቸው። ከዚያም ዐሥሩ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ወረዱ። ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን፥ ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሀት ከወንድሞቹ ጋር አላከውም። ራቡ በከነዓንም በመበርታቱ፥ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ከሄዱት ሰዎች መካከል የእስራኤል ልጆችም ነበሩ።