ዘፍጥረት 41:14-36

ዘፍጥረት 41:14-36 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ትእዛዝ ሰጠ፤ ከእስር ቤትም በጥድፊያ ይዘውት መጡ፤ ጠጕሩንም ከተላጨና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ፈርዖን ፊት ቀረበ። ፈርዖንም ዮሴፍን፣ “ሕልም አይቼ ነበር፤ ሕልሜን ሊተረጕምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም፤ አንተ ግን ሕልም ሲነገርህ የመተርጐም ችሎታ እንዳለህ ሰማሁ” አለው። ዮሴፍም ፈርዖንን፣ “እኔ የመተርጐም ችሎታ የለኝም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ለፈርዖን የሚሻውን ትርጕም ይሰጠዋል” አለው። ከዚህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “በሕልሜ በአባይ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር። ሥጋቸው የወፈረና መልካቸው ያማረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ሲበሉ አየሁ። ከእነርሱም በኋላ፣ ዐቅመ ደካማ፣ መልካቸው እጅግ የከፋና ዐጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም። ዐጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፣ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው። ከዋጧቸውም በኋላ፣ ያው የበፊቱ መልካቸው ስላልተለወጠ እንደ ዋጧቸው ማንም ሊያውቅ አይችልም ነበር፤ ከዚያም ከእንቅልፌ ነቃሁ። “እንደዚሁም፣ በሕልሜ በአንድ የእህል አገዳ ላይ ፍሬአቸው የፋፋና ያማሩ ሰባት እሸት ዛላዎች ወጥተው አየሁ። ቀጥሎም በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ። የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ይህንኑም ለአስማተኞች ነገርሁ፤ ነገር ግን ማንም ሊፈታው አልቻለም።” ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዐይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል። ሰባቱ የሚያማምሩ ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፣ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው። ከእነርሱም በኋላ ዐጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው። “አስቀድሜ ለፈርዖን እንደ ተናገርሁት፣ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን ገልጦለታል። በመላው የግብጽ ምድር እጅግ የተትረፈረፈ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፣ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም። ከጥጋቡ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፣ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል። ሕልሙ ለፈርዖን በሁለት መልክ በድጋሚ መታየቱ፣ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ስለ ሆነ ነው፤ ይህንም እግዚአብሔር በቅርብ ጊዜ ይፈጽመዋል። “እንግዲህ ፈርዖን ብልኅና አስተዋይ ሰው ፈልጎ፣ በመላው የግብጽ ምድር ላይ አሁኑኑ ይሹም። እንደዚሁም በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት፣ አንድ ዐምስተኛው እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ ኀላፊዎችን ይሹም። እነርሱም በሚመጡት የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት ሁሉ ይሰብስቡ፤ በፈርዖንም ሥልጣን ሥር ያከማቹ፤ ለምግብ እንዲሆኑም በየከተማው ይጠበቁ። የሚከማቸው እህል፣ ወደ ፊት በግብጽ አገር ላይ ለሚመጣው የሰባት ዓመት ራብ መጠባበቂያ ይሁን፤ በዚህም ሁኔታ አገሪቱ በራብ አትጠፋም።”

ዘፍጥረት 41:14-36 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ፈር​ዖ​ንም ልኮ ዮሴ​ፍን አስ​ጠ​ራው፤ ከግ​ዞት ቤትም አወ​ጡት፤ ራሱ​ንም ላጩት፤ ልብ​ሱ​ንም ለወጡ፤ ወደ ፈር​ዖ​ንም ገባ። ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “ሕል​ምን አየሁ፤ የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ል​ኝም አጣሁ፤ ሕል​ምን እንደ ሰማህ፥ እንደ ተረ​ጐ​ም​ህም ስለ አንተ ሰማሁ።” ዮሴ​ፍም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከገ​ለ​ጸ​ለት ሰው በቀር መተ​ር​ጐም የሚ​ችል የለም” ብሎ ለፈ​ር​ዖን መለ​ሰ​ለት። ፈር​ዖ​ንም ለዮ​ሴፍ እን​ዲህ አለው፥ “እነሆ፥ በሕ​ልሜ በወ​ንዝ ዳር ቆሜ ነበር፤ እነ​ሆም፥ ሥጋ​ቸው የወ​ፈረ፥ መል​ካ​ቸ​ውም ያማረ ሰባት ላሞች ወጡ፤ በወ​ንዙ ዳር በመ​ስ​ኩም ይሰ​ማሩ ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ፥ የደ​ከሙ፥ መል​ካ​ቸ​ውም እጅግ የከፋ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወ​ንዙ ወጡ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ሁሉ እንደ እነ​ርሱ መልከ ክፉ ከቶ አላ​የ​ሁም፤ እነ​ዚያ የከ​ሱ​ትና መልከ ክፉ​ዎቹ ላሞች እነ​ዚ​ያን የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን ያማ​ሩና የወ​ፈሩ ሰባት ላሞች ዋጡ​አ​ቸው፤ በሆ​ዳ​ቸ​ውም ተዋጡ፤ በሆ​ዳ​ቸ​ውም ውስጥ የገባ እን​ደ​ሌለ ሆኑ፤ መል​ካ​ቸ​ውም በመ​ጀ​መ​ሪያ እንደ ነበ​ረው የከፋ ነበረ፤ ነቃ​ሁም። ዳግ​መ​ኛም ተኛሁ፤ በሕ​ል​ሜም እነሆ፥ የጐ​መ​ሩና መል​ካም የሆኑ ሰባት እሸ​ቶች ከአ​ንድ አገዳ ሲወጡ አየሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ የሰ​ለ​ቱና በነ​ፋስ የተ​መቱ ሌሎች ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤ እነ​ዚያ የሰ​ለ​ቱ​ትና በነ​ፋስ የተ​መ​ቱት እሸ​ቶች እነ​ዚ​ያን ያማ​ሩ​ት​ንና የጐ​መ​ሩ​ትን ሰባ​ቱን እሸ​ቶች ዋጡ​አ​ቸው። ለሕ​ልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ችም ሕል​ሜን ነገ​ርሁ፤ የተ​ረ​ጐ​መ​ል​ኝም የለም።” ዮሴ​ፍም ፈር​ዖ​ንን አለው፥ “የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ደ​ር​ገው ያለ​ውን ለፈ​ር​ዖን አሳ​ይ​ቶ​ታል። እነ​ዚያ ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች እሸ​ቶች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው። ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የወ​ጡት እነ​ዚያ የከ​ሱና መልከ ክፉ​ዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱ​ትና ነፋስ የመ​ታ​ቸው ሰባቱ እሸ​ቶች እነ​ርሱ ራብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ናቸው። ለፈ​ር​ዖን የነ​ገ​ር​ሁት ነገር ይህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ደ​ር​ገው ያለ​ውን ለፈ​ር​ዖን አሳ​የው። እነሆ፥ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ እጅግ ጥጋብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ይመ​ጣሉ፤ ደግ​ሞም ከዚህ በኋላ ሰባት የራብ ዓመት ይመ​ጣል፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ የነ​በ​ረ​ው​ንም ጥጋብ ሁሉ ይረ​ሱ​ታል፤ ራብም ምድ​ርን ሁሉ ያጠ​ፋል፤ በኋ​ላም ከሚ​ሆ​ነው ከዚያ ራብ የተ​ነሣ በም​ድር የሆ​ነው ጥጋብ አይ​ታ​ወ​ቅም፤ እጅግ ጽኑ ይሆ​ና​ልና። ሕል​ሙም ለፈ​ር​ዖን ደጋ​ግሞ መታ​የቱ ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ቈ​ረጠ ስለ​ሆነ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፈጥኖ ያደ​ር​ገ​ዋል። አሁ​ንም ብል​ህና ዐዋቂ ሰውን ለአ​ንተ ፈልግ፤ በግ​ብፅ ምድር ላይም ሹመው። ፈር​ዖን በግ​ብፅ ምድር ላይ ሹሞ​ችን ይሹም፤ በሰ​ባ​ቱም የጥ​ጋብ ዓመ​ታት ከሚ​ገ​ኘው ፍሬ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ከአ​ም​ስት እጅ አን​ደ​ኛ​ውን ይው​ሰድ። የሚ​መ​ጡ​ትን የመ​ል​ካ​ሞ​ቹን ሰባት ዓመ​ታት እህ​ላ​ቸ​ውን ያከ​ማቹ፤ ስን​ዴ​ው​ንም ከፈ​ር​ዖን እጅ በታች ያኑሩ፤ እህ​ሎ​ችም በከ​ተ​ሞች ይጠ​በቁ። በግ​ብፅ ምድር ስለ​ሚ​ሆ​ነው ስለ ሰባቱ ዓመ​ታት ራብ እህሉ ለሀ​ገሩ ሁሉ ተጠ​ብቆ ይኑር፥ ምድ​ሪ​ቱም በራብ አት​ጠ​ፋም።”

ዘፍጥረት 41:14-36 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ትእዛዝ ሰጠ፤ ከእስር ቤትም በጥድፊያ ይዘውት መጡ፤ ጠጕሩንም ከተላጨና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ፈርዖን ፊት ቀረበ። ፈርዖንም ዮሴፍን፣ “ሕልም አይቼ ነበር፤ ሕልሜን ሊተረጕምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም፤ አንተ ግን ሕልም ሲነገርህ የመተርጐም ችሎታ እንዳለህ ሰማሁ” አለው። ዮሴፍም ፈርዖንን፣ “እኔ የመተርጐም ችሎታ የለኝም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ለፈርዖን የሚሻውን ትርጕም ይሰጠዋል” አለው። ከዚህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “በሕልሜ በአባይ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር። ሥጋቸው የወፈረና መልካቸው ያማረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ሲበሉ አየሁ። ከእነርሱም በኋላ፣ ዐቅመ ደካማ፣ መልካቸው እጅግ የከፋና ዐጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም። ዐጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፣ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው። ከዋጧቸውም በኋላ፣ ያው የበፊቱ መልካቸው ስላልተለወጠ እንደ ዋጧቸው ማንም ሊያውቅ አይችልም ነበር፤ ከዚያም ከእንቅልፌ ነቃሁ። “እንደዚሁም፣ በሕልሜ በአንድ የእህል አገዳ ላይ ፍሬአቸው የፋፋና ያማሩ ሰባት እሸት ዛላዎች ወጥተው አየሁ። ቀጥሎም በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ። የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ይህንኑም ለአስማተኞች ነገርሁ፤ ነገር ግን ማንም ሊፈታው አልቻለም።” ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዐይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል። ሰባቱ የሚያማምሩ ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፣ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው። ከእነርሱም በኋላ ዐጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው። “አስቀድሜ ለፈርዖን እንደ ተናገርሁት፣ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን ገልጦለታል። በመላው የግብጽ ምድር እጅግ የተትረፈረፈ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፣ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም። ከጥጋቡ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፣ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል። ሕልሙ ለፈርዖን በሁለት መልክ በድጋሚ መታየቱ፣ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ስለ ሆነ ነው፤ ይህንም እግዚአብሔር በቅርብ ጊዜ ይፈጽመዋል። “እንግዲህ ፈርዖን ብልኅና አስተዋይ ሰው ፈልጎ፣ በመላው የግብጽ ምድር ላይ አሁኑኑ ይሹም። እንደዚሁም በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት፣ አንድ ዐምስተኛው እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ ኀላፊዎችን ይሹም። እነርሱም በሚመጡት የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት ሁሉ ይሰብስቡ፤ በፈርዖንም ሥልጣን ሥር ያከማቹ፤ ለምግብ እንዲሆኑም በየከተማው ይጠበቁ። የሚከማቸው እህል፣ ወደ ፊት በግብጽ አገር ላይ ለሚመጣው የሰባት ዓመት ራብ መጠባበቂያ ይሁን፤ በዚህም ሁኔታ አገሪቱ በራብ አትጠፋም።”

ዘፍጥረት 41:14-36 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ፈርዖንም ልኮ ዮሴፍን አስጠራ ከግዞት ቤትም አስቸኮሉት፤ እርሱም ተላጨ ልብሱንም ለወጠ፥ ወደ ፈርዖን ገባ። ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ ሕልምን አየሁ የሚተረጕመውም አልተገኘም ሕልምን እንደ ሰማህ እንደ ተረጎምህም ስለ አንተ ሰማሁ። ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ ይህ በእኔ አይደለም እግዚአብሔር ግን ለፈርዖን በደኅንነት ይመልስለታል። ፈርዖንም ለዮሴፍ እንዲህ አለው፦ እነሆ በሕልሜ በወንዝ ዳር ቆሜ ነበር፤ እነሆም ሥጋቸውም የወፈረ መልካቸውም ያማረ ሰባት ላሞች ወጡ በመስኩም ይስማሩ ነበር። ከእነርሱን በኍላ እነሆ የደከሙ መልካቸውም እጅግ የከፋ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ በግብፅም ምድር ሁሉ እንደ እነርሱ መልክ ከፍ ከቶ አላየሁም፤ የከሱትና መልከ ክፋዎቹ ላሞች የመጀመሪያዎቹን ወፍራሞቹን ስባት ላሞች ዋጡአቸው፥ በሆዳቸውም ተዋጡ አልታወቀም መልካቸውም በመጀመሪያ እንደ ነበረውም የከፋ ነበረ። በሕልሜም እነሆ የዳበሩና መልካም የሆኑ ሰባት እሸቶች በአንድ አገዳ ሲወጡ አየሁ ከእነርሱም በኍላ እነሆ የደረቁና የሰለቱ በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ስባት እሸቶች ወጡ የሰለቱት እሸቶች ያማሩትን ሰባቱን እሸቶች ዋጡአቸው። ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ የሚተረጕምልኝም አጣሁ። ዮሴፍም ፈርዖንን አለው፦ የፈርዖን ሕልሙ አንድ ነው እግዚአብሔር ሊያደርገው ያለውን ለፈርዖን ነግሮታል። ሰባቱ መልካካሞች ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፥ ሰባቱም መልካካሞች እሸቶች ሰባት ዓመታት ናቸው ሕልሙ አንድ ነው። ከእነርሱም በኍላ የወጡት የከሱትና መልከ ክፋዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፥ የሰለቱትና የምሥራቅ ነፋስ የመታቸው ሰባቱም እሽቶች እነርሱ ራብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ናቸው። ለፈርዖን የነገርሁት ነገር ይህ ነው እግዚአብሔር ሊያደርገው ያለውን ለፈርዖን አሳየው። እነሆ በግብፅ ምድር ሁሉ እጅግ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ ደግሞ ከዚህ በኍላ የሰባት ዓመት ራብ ይመጣል በግብፅ አገር የነበረውም ጥጋብ ሁሉ ይረሳል ራብም ምድርን በጣም ያጠፋል በኍላ ከሚሆነው ከዚያ ራብ የተነሣም በምድር የሆነው ጥጋብ አያታወቅም እጅግ ጽኑ ይሆናልና። ሕልሙም ለፈርዖን ደጋግሞ መታየቱ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀረጠ ስለ ሆነ ነው እግዚአብሔር ፈጥኖ ያደርገዋል። አሁንም ፈርዖም ብልህና አዋቂ ሰውን ይፈልግ በግብፅ ምድር ላይም ይሹመው። ፈርዖን በምድር ላይ ሹማምትን ይሹም በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ፍሬ በግብፅ ምድር ሁሉ ከአምስት እጅ አንደኛውን ይውሰድ። የሚመጡትን የመልካሞቹን ዓመታት እህላቸውም ያከማቹ ስንዴውንም ከፈርዖን እጅ በታች ያኑሩ፥ እህሎችም በከተሞች ይጠበቁ በግብፅ ምድር ስለሚሆነው ስለ ስባቱ ዓመታት ራብ እህሉ ተጠብቆ ይኑር ምድሪቱም በራብ አትጠፋም።

ዘፍጥረት 41:14-36 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ስለዚህ ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት አዘዘ፤ ወዲያውኑ ከእስር ቤት ይዘውት መጡ፤ ጠጒሩን ተላጭቶ ልብሱን ከለወጠ በኋላ ወደ ንጉሡ ፊት ቀረበ። ንጉሡም ዮሴፍን “ሕልም አይቼ ነበር፤ ነገር ግን ማንም ሊተረጒመው አልቻለም፤ አንተ ሕልም የመተርጐም ችሎታ እንዳለህ ሰምቼአለሁ” አለው። ዮሴፍም “ንጉሥ ሆይ፥ እኔ ሕልም የመተርጐም ችሎታ የለኝም፤ ትክክለኛውን ትርጒም ሊሰጥህ የሚችል እግዚአብሔር ነው” አለ። ንጉሡም እንዲህ አለ፤ “በሕልሜ በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር፤ ሰባት የወፈሩና የሰቡ ላሞች ከወንዙ ወጥተው ሣር ሲበሉ አየሁ፤ ቀጥሎም አጥንቶቻቸው እስከሚታይ ድረስ የከሱ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ፤ እንደ እነርሱ የሚያስከፉ ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም። የከሱትና አስከፊ የሆኑት ላሞች በመጀመሪያ የወጡትን ሰባት የወፈሩ ላሞች ዋጡአቸው። ከዋጡአቸውም በኋላ እንደ ቀድሞው የከሱ ስለ ነበሩ፥ እንደ ዋጡአቸው ማንም ሊያውቅ አይችልም ነበር፤ በዚህ ጊዜ እኔ ከእንቅልፌ ነቃሁ። ደግሞም በሕልሜ በአንድ የእህል አገዳ ላይ ሰባት የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች አየሁ፤ ቀጥሎም የቀጨጩና በበረሓ ነፋስ ተመተው የሰለቱ ሰባት የእሸት ዛላዎች ታዩ። የቀጨጩትም ዛላዎች የሚያምሩትን ዛላዎች ዋጡአቸው፤ ያየኋቸውንም ሕልሞች ለአስማተኞች ነገርኩ፤ ነገር ግን ሕልሞቹን ማንም ሊተረጒምልኝ አልቻለም።” ዮሴፍም ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ “የሁለቱም ሕልሞችህ ትርጒም አንድ ነው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ነገር አስቀድሞ ገልጦልሃል፤ ሰባቱ የሚያምሩ ላሞች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ ሰባቱም ያማሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ የሁለቱም ትርጒም አንድ ነው። ከእነርሱም በኋላ የወጡት ሰባት የከሱትና አስከፊዎቹ ላሞች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ እንዲሁም ሰባቱ የቀጨጩና በበረሓ ነፋስ ተመተው የሰለቱ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ የሁለቱም ትርጒም አንድ ነው፤ ይኸውም ሰባት የራብ ዓመቶች ናቸው። ልክ እንደ ነገርኩህ ነው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ነገር አስቀድሞ ገልጦልሃል፤ በመላው የግብጽ ምድር ላይ ታላቅ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመቶች ይመጣሉ። ከዚያ በኋላ ሰባት የራብ ዓመቶች ይመጣሉ፤ ራብ አገሪቱን በብርቱ ስለሚጐዳት እነዚያ የጥጋብ ዓመቶች ይረሳሉ። ተከታዩ የራብ ዘመን እጅግ አሠቃቂ ስለሚሆን የጥጋብ ጊዜ ፈጽሞ እንዳልነበረ ይሆናል። ሕልሙን ደጋግመህ ማየትህ የሚያመለክተው፥ ነገሩ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወሰነና በቅርብ ጊዜም ውስጥ የሚፈጸም መሆኑን ነው። “እንግዲህ ጥበብና ማስተዋል ያለውን ሰው መርጠህ በአገሪቱ አስተዳዳሪ አድርገህ ሹመው፤ በሰባቱ የጥጋብ ዓመቶች አንድ አምስተኛውን ሰብል የሚሰበስቡ ሰዎችን መርጠህ ሹም። እነርሱ በሚመጡት የጥጋብ ዓመቶች ትርፍ የሆነውን ሰብል ሁሉ እንዲሰበስቡ እዘዛቸው፤ በየከተማውም እህል በጐተራ እንዲያከማቹና እንዲጠብቁት ሥልጣን ስጣቸው። ይህም የሚከማቸው እህል በግብጽ ምድር ላይ ወደፊት በሚመጡት ሰባት የራብ ዓመቶች ለአገሪቱ መጠባበቂያ ይሆናል፤ በዚህ ሁኔታ አገሪቱ በራብ ከመጐዳት ትድናለች።”

ዘፍጥረት 41:14-36 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ትእዛዝ ሰጠ፤ ከእስር ቤትም በጥድፊያ ይዘውት መጡ፤ ጠጉሩንም ከተላጨና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ፈርዖን ፊት ቀረበ። ፈርዖንም ዮሴፍን፥ “ሕልም አይቼ ነበር፤ ሕልሜን ሊተረጉምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም፤ አንተ ግን ሕልም ሲነገርህ የመተርጐም ችሎታ እንዳለህ ሰማሁ” አለው። ዮሴፍም ፈርዖንን፥ “እኔ የመተርጐም ችሎታ የለኝም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ለፈርዖን የሚሻውን ትርጒም ይሰጠዋል” አለው። ከዚህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “በሕልሜ በዐባይ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር። ሥጋቸው የወፈረና መልካቸው ያማረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ሲበሉ አየሁ። ከእነርሱም በኋላ፥ ዐቅመ ደካማ፥ መልካቸው እጅግ የከፋና ዐጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም። ዐጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፥ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው። ከዋጧቸውም በኋላ፥ ያው የበፊቱ መልካቸው ስላልተለወጠ እንደ ዋጧቸው ማንም ሊያውቅ አይችልም ነበር፤ ከዚያም ከእንቅልፌ ነቃሁ። እንደዚሁም፥ በሕልሜ በአንድ የእህል አገዳ ላይ ፍሬያቸው የፋፋና ያማሩ ሰባት እሸት ዛላዎች ወጥተው አየሁ። ቀጥሎም በምሥራቅ ነፋስ ተመተው የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ። የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ይህንኑም ለአስማተኞች ነገርሁ፤ ነገር ግን ማንም ሊፈታው አልቻለም።” ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዓይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል። ሰባቱ የሚያማምሩ ላሞች፥ ሰባት ዓመታት ናቸው፥ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው። ከእነርሱም በኋላ ዐጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፥ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው። አስቀድሜ ለፈርዖን እንደተናገርኩት፥ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን ገልጦለታል። በመላው የግብጽ ምድር እጅግ የተትረፈረፈ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፥ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም። ከጥጋቡ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፥ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል። ሕልሙ ለፈርዖን በሁለት መልክ በድጋሚ መታየቱ፥ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ስለሆነ ነው፤ ይህንንም እግዚአብሔር በቅርብ ጊዜ ይፈጽመዋል። እንግዲህ ፈርዖን ብልኅና አስተዋይ ሰው ፈልጎ፥ በመላው የግብጽ ምድር ላይ አሁኑኑ ይሹም። እንደዚሁም በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት፥ አንድ አምስተኛው እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ ኀላፊዎችን ይሹም። እነርሱም በሚመጡት የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት ሁሉ ይሰብስቡ፤ በፈርዖንም ሥልጣን ሥር ያከማቹ፤ ለምግብ እንዲሆኑም በየከተማው ይጠበቁ። የሚከማቸው እህል፥ ወደ ፊት በግብጽ አገር ላይ ለሚመጣው የሰባት ዓመት ራብ መጠባበቂያ ይሁን፤ በዚህም ሁኔታ አገሪቱ በራብ አትጠፋም።”