ዘፍጥረት 37:3-4
ዘፍጥረት 37:3-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ያዕቆብም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወድደው ነበር፤ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና። በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት። ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንደሚወድደው በአዩ ጊዜ ጠሉት፤ በሰላም ይናገሩትም ዘንድ አልቻሉም።
Share
ዘፍጥረት 37 ያንብቡዘፍጥረት 37:3-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለ ወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወድደው ነበር፤ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም አደረገለት። ወንድሞቹም፣ አባታቸው ከእነርሱ አብልጦ የሚወድደው መሆኑን ሲያዩ፣ ዮሴፍን ጠሉት፤ በቅን አንደበትም ሊያናግሩት አልቻሉም።
Share
ዘፍጥረት 37 ያንብቡዘፍጥረት 37:3-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበር በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት። ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንዲወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ይናገሩትም ዘንድ አልቻሉም።
Share
ዘፍጥረት 37 ያንብቡ